2
.2 የአገልግሎቶች ዝርዝር አፈፃፀም
2.1.የዲዛይን ሥራ
የጥናት ሥራ
ለቤት ልማት የሚውል LDP እና NHD ጥናት TOR በራስ ኃይል በማዕከል በ6 ቀናት
ያከናወናል ለቤት ግንባታ የሚሆን ቦታ በመጠየቅና በመረከብ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ
በ33 ቀናት ያካሂዳል
የዲዛይን ጨረታ በውድድር
ዲዛይኑ በጨረታ ለማሰራት ተወዳዳሪዎች በመጥራት የጨረታ ሰነድ ይሸጣል ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ አርክቴክቸራል ዲዛይንና የህንፃው ሞዴል ጥናት በመቀበልና በማወዳደር አሸናፊውን ለይቶ የመሸለም ሥራ ይከናወናል፡፡ ከአሸናፊውም ጋራ በመነጋገር የዋጋ ድርድር በማድረግ የክፍያ ሂደት ይወሰናል፡፡
ውለታና አስተዳደር
በድርድር ስምምነት ላይ የተደረሰበትን የገንዘብ መጠን በመጥቀስና የስምምነት ምላሽ በመቀበል የውለታ ሰነድ በ3ቀን አዘጋጅቶ ውል በመዋዋል ሰነዱ ለሚመለከታቸው ሁሉ ይበተናል በውለታው ዝርዝር መሠረት በ27 ቀናት የተሰራው የመጨረሻ (Final design) ዲዛይን ሥራ በማፅደቅና በመረከብ ያስተዳድራል፡፡
በቅድመ ብቃት መስፈርት (Pre qualification Criteria)
ቅድመ ብቃት መስፈርት በአማራጭነት በመውሰድ ለዚሁ ተግባር ማስፈፀሚያ
ጥናት ለማድረግ TOR በ3 ቀናት ውስጥ በማዘጋጀት የጨረታ ሒደት ይከናወናል፡፡ በዚህም የጨረታ ሰነድ በበቂ ኮፒ ተዘጋጅቶ የጨረታ ማስታወቂያው በኢሜልና ፋክስ በአንድ ቀን ያሠራጫል፡፡ የጨረታ ሂደቱ ሥርዓት ተጠብቆ አሸናፊውን ይለያል፣ ቅሬታም ካለ ተቀብሎ ተገቢውን መልስ በመስጠት የጨረታ ሰነዱን አፅድቆ የአሸናፊው ሰው ስምና ያሸነፈበት ዋጋ ለአሠሪው መ/ቤት ተገልፆ ስምምነቱን ምላሽ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡
የውለታ ሂደት
ከዚህ በኃላ ለአሸናፊው ማለፉንና ውለታ መዋዋል መቻሉ ይገለፃል
አሸናፊውን ተጫራች ከተለየና ከታወቀ በኃላ የውለታ ሰነድ በበቂ ኮፒ በማዘጋጀት የውለታ ሰነዱ ይፈርማል፡፡ ለሚመለከታቸው መ/ቤቶችም በደብዳቤ ያሠራጫል፡፡ ተግባሩም በ1ዐ ቀናት ይከናወናል
የዲዛይን ዝግጅት
ዲዛይን በሚዘጋጅለት ህንፃ ለእያንዳንዲ ሰው የሚደርሰውን ቤት ካርታና ፕላን መዘጋጀቱ በመጀመሪያ ደረጃ ዲዛይን ይገመገማል እንዲሁም የመጨረሻው ስትራክቸራል ዲዛይን፣ ኤሌክትሪክና ሳኒተሪ ዲዛይን በተጨማሪም የሥራ ዝርዝር (BOQ) እና የመጨረሻ ደረጃ ዲዛይንና በቤቶች ልማት የሚገነቡትን የቤቶች ቲፖሎጂ ካርታ ይዘጋጃል፡፡ ይህ ሥራ በ3 የዲዛይን ጨረታና ውለታ ኦፊሰሮች በ8 ቀናት ተጣርቶ ይጠናቀቃል፡፡
2. የቤቶች ልማት የግንባታ ሥራ
የጨረታ ሂደት በኮንትራት / በቅድመ ብቃት መሥፈርት/
ይህ ተግባር ክ/ከተማ የሚከናወን ሲሆን አሠራሩም የጨረታ ዶክመንት /ዲዛይን/ የተሟላ መሆኑን ያጣራል፣ የጨረታ ሰነዶችን በበቂ ኮፒ በማዘጋጀት የተጫራቾች ደረጃና የፕሮጀክት ጊዜን በመወሰን፣ የጨረታ ማስታወቂያ በኢሜልና በፋክስ ያሣውቃል የጨረታ ሠነድ በመሸጥ፣ በመቀበል፣ በመክፈትና አሸናፊውን በመለየት ለአሠሪው መ/ቤት የአሸናፊውን ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ስምና ያሸነፈበትን ዋጋ በመግለጽ ምላሹን ይቀበላል፡፡
ይህ በ8 ቀናት ይከናወናል
የውለታ ሂደት
ይህ ተግባር ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱን በማሣወቅ ምላሹን በመቀበል ውለታ ያፈራርማል፣ ለአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተወሰኑትን ሥራዎች ለይቶ በማሣወቅ የኮንትራት ውል ይፈጽማል፣ እንዲሁም በህብረተሰቡ ተሣትፎ የሚሸፍኑትን ለይቶ በማሣወቅ ኮንትራት ውል ይፈጽማል፡፡ ይህ ሥራ በሁለት የግንባታ ጨረታና ውለታ ኦፊሰሮች በ 4½ ቀናት ተሠርቶ ይጠናቀቃል፡፡
ሣይት ርክክብ
ይህ ተግባር የሥራ ተቋራጩ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና፣ የፕሮጀክት መርሀ-ግብር፣ የፕሮጀክት መሀንዲስ የት/ትና የሥራ ልምድ መረጃ (CV) በአንድ ቀን እንዲቀርብና ተገምግሞ እንዲፀድቅ ያደርጋል፣ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ በ4 ሰዓት ውስጥ ይመደባል፣ ዕለትና ሠዓት ተወስኖ የሚመለከታቸው አካላት በርክክቡ ላይ እንዲገኙ በ 1ቀን በደብዳቤ ያሣውቃል፣ በርክክብ ሂደቱ ላይ የተገኙ ተወካዮች በተዘጋጀው ቅፅ ላይ ከፈረሙ በኃላ በ2ቀን በደብዳቤ ለሚመለከታቸው አካላት ይበትናል፡፡
የግንባታ ቁጥጥር በኮንትራት፡-
የግንባታ ቁጥጥር የሥራ ሂደት በዕለቱ በቦታው ያሉ ሁኔታዎች በመመዝገብ በቀረበው ሣይት ፕላን መሠረት ወሰኑን ያረጋግጣል፣ የተመደበው መሀንዲስ የቁጥጥር ሥራ መርሀ-ግብር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ ያደርጋል፣ ተቋራጩ ባቀረበው የሥራ ፕሮግራም መሠረት እንዲከናወን ያደርጋል፣ በግንባታ ወቅት ለሚነሱት ጥያቄዎችና ግድፈቶች በደረጃው ምላሽ ይሰጣል፣ በሣይት ቡክ የሰፊረውን እርማት ወዲያው ለቢሮው ያሣውቃል፣ የግንባታው ሥራ ጥራትና ደረጃውን ጠብቆ በዲዛይኑና በሥራ ዝርዝሩ መሠረት እንዲካሄድ ያደርጋል፣ በቤቶች ልማት የተገነቡትን ቤቶች ዕጣ ለደረሰው ለእያንዳንዱ ባለቤት በስሙ ካርታና ፕላን መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፡፡ ይህ ሥራ በአራት የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ኦፊሰሮች እና በስምንት የቤት ልማት አስተዳደር መለስተኛ ኦፊሰር በ12 ቀንና በ7 ሰዓት ተሠርቶ ይጠናቀቃል፡፡
2.2 የፕሮጀክት አፈፃፀም ሪፖርት፡-
ይህ ተግባር በክ/ከተማ የሚከናወን ሲሆን አሠራሩም ሣምንታዊ፣ ወርኃዊ፣ የሩብ ዓመት የግማሽ ዓመትና የአመት ሪፖርቶችን በ2 ሰዓት በማዘጋጀት ያቀርባል፡፡ ሪፖርቶቹን፣ በደረጃው መገምገም ለሚመለከተው አካል በ7ቀን ያሣውቃል፣ የተፈጠረ የሥራ ዕድልን መረጃ በመያዝ በ2ቀን ሪፖርት ያቀርባል፡፡
2.6 ክፍያ መፈፀም
የሚቀርበውን የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ትክክለኛነት በመመርመር በ4ሰዓት ያረጋግጣል፣ በቀረበው የቅድሚያ ክፍያ መሠረት የቅድሚያ ክፍያ ሰነድ በ4ሰዓት በማዘጋጀት ለአሠሪው መ/ቤት በ1ሰዓት ለክፍያ ይልካል፣ የለቀማ ሥራ (Take off) እና የስፍር ምስክር ወረቀት በ7ቀን ውስጥ በማዘጋጀት ይፈራረማል፣ የሚቀርበውን የክፍያ መርምሮ የክፍያ የምሥክር ወረቀት (Payment Certificate) በ12ሰዓት ውስጥ ያዘጋጃል፣ የተዘጋጀውን የክፍያ ሰነድ ኮንትራክተሩና ሱፐርቫይዘሩ በሰባት ቀን ውስጥ አፅድቆ ለአሠሪው መ/ቤት ለክፍያ ይልካል በግልባጭ ለሚመለከተው ያሣውቃሉ፡፡ የሥራ ተቋራጩ የመጀመሪያ ርክክብ ሲጨረስ አጠቃላይ የክፍያ ሰነድ በ4ሰዓት አዘጋጅቶ ሲያቀርብ፣ የክፍያ የምስክር ወረቀት መያዠና ተቀናናሽ በሰነዱ እንዲያያዙ በማድረግ የርክክብ ቅፅና የተዘጋጀው የክፍያ ሰነድ ለአሰሪው መ/ት ለክፍያ ይልካልየርክክብ ቅፅ ተዘጋጅቶ የሚመለከታቸው ሁሉ ከፈረሙ በኃላ የለውጥ ሥራ፣ የፕሮጀክት ጊዜ ማራዘሚያ፣ የይገባኛል ጥያቄዎችንና ሌሎችንም አካቶ ክፍያ ምሥክር ወረቀት ጋር በማቅረብ ለክፍያ ይልካል፣ የመጨረሻ ርክክብ/ በውለታ ሠነዱ በተቀመጠው /ጊዜው ሲጠናቀቅ የመያዣ ክፍያ እንዲፈፅም የክፍያ ሰርተፍኬት አዘጋጅቶና በመ/ቤቱ አፅድቆ ለአሠሪው መ/ቤት ይልካል፡፡
2 2.6 የለውጥ ሥራ
ዳዛይን በ1ዐዐ% ጥራት ስለሚሰራ የለውጥ ሥራ (Variation) አሰተናገድም ፡፡ ይሁንና በአስገዳጅ ሁኔታ እስከ 5% የለውጥ ጥያቄ በመቀበል ሲቻል የለውጡ ተገቢነት ተመርምሮ የዋጋ ተመን ሥራ በ12 ሰዓት ይሰራል፡፡
2.7 የጊዜ ማራዘሚያ አሣማኝ በሆነ ምክንያት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራሠሚያ ጥያቄ ሲያቀርብ ጥያቄው በመገምገም ትክክለኛነቱ ተረጋግጦ በ6ቀን ውሣኔ ይሰጥበታል፡፡
2 2.8 የርክክብ ሂደቶች
ግንባታው ተጠናቆ የርክክብ ጥያቄ ሲቀርብ በውለታ ጊዜው መጠናቀቁን በ3½ በማረጋገጥና በቦታው በግንባር በመገኘት የመጀመሪያ ርክክብ ይፈፀማል፡፡ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኃላ የግንባታው ጥራት ታይቶ ማስተካከያ ተደርጐበት /ጐድለቶች ከተከሰቱ/ በ2ቀን ውስጥ የመጨረሻው ርክክብ ይፈፀማል፡፡ ይሁንና የግንባታው ባለቤት ግንባታው ሣይጠናቀቅ ለሥራ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሥራ ተቋራጩን በማሣወቅ በ1ዐ ሰዓታት የከፊል ርክክብ ሊያደርግ ይችላል፡
3 አስተዳደር ሥራ
3.1 የመንግስት ቤት ማከራየት
የመኖሪያና የንግድ ቤት ኪራይ በቀበሌ ይሠራል፡፡ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ሲቀርብ ጥያቄውን ተቀብሎ በ15 ደቂቃ ይመዘገባል፣ የምዝገባ ካርድም ይሠጣል፡፡ ክፍት ቤት ሲገኝም በምዝገባው ቅደም ተከተል ቤቶችን፣ በአንድ ሰዓት ይመድባል፤ ምደባው በግልፅ ስለመከናወኑ ተጠቃሚው እንዲያውቅ ያደርጋል፣ በምደባ ቤት የደረሰው ግለሰብ በ½ሰዓት
ውል ከሞላ በኃላ ቤቱ በሚገኝበት ሠፈር በአካል በመገኘት ከጐረቤት ጋር በጋራ የሚጠቀምባቸውን በመግለፅና በማስተዋወቅ በ2½ ሰዓት የቁልፍ ርክክብ በማከናወን ቤቱን ያከራያል፣ ኮፒውን ለኪራይ አሰባሰብ ለገቢ ሰብሣቢ መ/ቤት በ½ሰዓት ይልካል፡፡ ተከራይ ስለመሆናቸው የሚገልፅ መታወቂያ ይሠጣል፡፡
የንግድ ቤት ኪራይ በጨረታ የሚከናወን ስለሆነ የጨረታ ሰነድና ማስታወቂያ በ1ሰዓት ያዘጋጃል፣ ለተጫራቾች ጥሪ ያደርጋል፣ ሰነድ ለ5 ቀን ይሸጣል፣ ጨረታ ይከፍታል የጨረታ ሰነድ ይገመግማል የተሟላው ካልተሟላው ሰነዱን ይለያል አሸናፊውን ይለያል ውጤቱ ለህዝብ በ1ቀን ግልፅ ያደርጋል፡፡ ቅሬታ ካለ ቅሬታውን መርምሮ በ½ሰዓት መልስ ይሰጣል ከአሸናፊው በሰዓት ውል ይዋዋላል ውሉ ለገቢ ሰብሣቢ መ/ቤት ያስተላልፋል፡፡ ተከራይ ስለመሆናቸው የሚገልፅ መታወቂያ አዘጋጅቶ ይሠጣል፡፡
3.2. የኪራይ ገቢ አሰባሰብ ክትትል
ከቀበሌ ገቢ ሰብሣቢ መ/ቤት የመጣለትን ደረሰኝ ተቀብሎ በ5 ደቂቃ ይመዘግባል፣ ከዋናው ሰነድ ጋር ያገናዝባል ስህተት ሲያገኝ እርምት በ½ሰዓት ይሰጣል ያልከፈሉትን በውላቸው መሠረት እንዲከፍሉ ይጠይቃል፣ ካልከፈሉ ውላቸው በ1ቀን ውስጥ እንዲቋረጥና ቤቱ ለአዲስ ተከራይ እንዲከራይ ያዘጋጃል፡፡
3.3. ውል ማደስ
ውል በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ በየቀበሌው በ½ሰዓት ይታደሣል፡፡ ውል መታደሱ በተከራዩ መታወቂያ ይሞላል፡፡ በወጣው ፕሮግራም መሠረት ያልመጡትን በደብዳቤ ጥሪ ያደርጋል፡፡ በተፈቀደው ጊዜ ውሉን ያላደሰ በፍላጐቱ እንደተወ ወይም እንደሌለ ተቆጥሮ ውሉ ይቋረጣል፡፡ ቤቱ ለኪራይ ይዘጋጃል፡፡
3.4. የመንግስት ቤት ጥገና
ተከራይ ጥገና ጠያቂዎች ባሉበት ቀበሌ የቅርፅና የቁሣቁስ ለውጥ ሣይደረግበት በራሣቸው ወጪ እንዲጠገኑ ግዴታ አስገብቶ በ½ሰዓት ለእድሣት ፈቃድ የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፡፡ የእድሣት ማመልከቻ ያስሞላል፡፡ የስምምነት ሰነድ ያስፈርማል፡፡
3.5. በህገወጥ የተያዘ ቤት ማስለቀቅ
ይህ ተግባር የሚሰራው በቀበሌ ደረጃ ሲሆን በህገወጥ የተያዘ ቤት በክትትልና በጥቆማ ሲደረስበት ለፖሊስና ለደንብ አስከባሪ በ1ሰዓት ውስጥ በማሣወቅና ጊዜውን በመወሰን ህገ ወጥ ግለሰቡ በ½ሰዓት ከቤቱ በማስለቀቅ፤ ቤቱን ለአዲስ ኪራይ ያዘጋጃል፡፡
3.6. የደንበኛ ቅሬታ መቀበል
የደንበኛ ቅሬታ በቀበሌ፣ በክ/ከተማና በማዕከል ይስተናገዳል ከደንበኛ የሚቀርበው ጥያቄ በመቀበል ይመራመራል፣ ተገቢው መልስም ግማሽ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይሠጣል፡፡
3.7. የተከራይ ልዩ ልዩ ጥያቄ
የቀበሌ ቤት ተከራዮች የሚያቀርቡት የመብራት፣ የውኃ፣ የአበልና የመሣሰሉት ጥያቄዎችን በመቀበልና ከማህደራቸው ጋር በማገናዘብ ለጠየቁት ጉዳይ በ½ሰዓት ውስጥ የድጋፍ ደብዳቤ /መልስ/ ይሠጣል፡፡
3.8. የመኖሪያ ቤት ወደ ንግድ ቤት ለውጥ ጥያቄ
ይህ ተግባር የሚከናወነው በቀበሌ ሲሆን ጥያቄው ሲቀርብ ለንግድ ሥራ አመቺ መሆኑን ይረጋገጣል፡፡ አመቺ ሆኖ ሲያገኘው የለውጥ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ የስም ክፍያ ከፍሎ ሲመጣ ቤቱ በካሬ ሜትር ተለክቶ የኪራይ መጠን ይመደባል፣ አዲስ ውል ተዘጋጅቶ ውል ይፈፀማል፡፡ ነባሩ ውል ይሠረዛል ወይም በመኖሪያነት የሚያገለግል ቀሪ ቤት ካለ ተከፍሎ ውሉ ወቅታዊ ይደረጋል ገቢ ሰብሣቢ መ/ቤት አዲሱ ውል በነባሩ እንዲተካና በዚሁ መሠረት ኪራይ እንዲሰባሰብ የማስታወቅ ሥራ በአንድ ሰዓት ውስጥ ይከናወናል፡፡
3.9. የእቅድ ዝግጅት
በቀበሌ እቅዱ መሠረት የሚያደርግበት TOR በ2ሰዓት ውስጥ ያዘጋጃል፡፡ ለዕቅድ ዝግጅት የሚውሉ መረጃዎች በ1ሰዓት ውስጥ ተሰባስቦ የመረጃው ትንተና ጥንቅርና የዕቅድ ረቂቅ በ2ቀን ውስጥ ይከናወናል፡፡ ረቂቁ ዕቅድ ሠራተኛው ተችቶትና ተወያይቶበት በ1ቀን ውስጥ ይፀድቃል፡፡
በክ/ከተማና በማዕከል
በ2ሰዓት ውስጥ TOR ሲያዘጋጅ ለዕቅድ የሚያስፈልገው መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተንና ረቂቅ የዕቅድ ሰነድ በ5 ቀን ውስጥ ያዘጋጃል፡፡ ሠራተኛው ለ½ ቀን ከተወያየበት በኃላ የቀረበውን አስተያየትና የቀበሌዎችን የክ/ከተሞች ዕቅድ በ5 ቀን ውስጥ በማጠቃለል ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሰራጫል፡፡
3.10. የሪፖርት ሥራ
ሪፖርት በቀበሌ ለሣምንታዊ በ½ሰዓት፣ ለወርኃዊ በ2 ሰዓት፣ ሩብ ዓመት በ½ቀን፣ የግማሽና የዘጠኝ ወር በ6 ሰዓትና የዓመት ሪፖርት በ1ቀን ያዘጋጃል፡፡ በክ/ከተማ የሣምንት ሪፖርት በ2ሰዓት/ ወርኃዊ በ1ቀን፣ ሩብ ዓመት፣ ግማሽ ዓመትና የዘጠኝ ወር በ2ቀን እና የዓመት በ3 ቀን ያዘጋጃል፣ ያጠቃልላል በማዕከል የሣምንቱ ሪፖርት በሁለት ቀንና የዓመት በ3 ቀን ያዘጋጃል፣ ያጠቃልላል
3.11. መረጃ ማደራጀት
የተወረሱ ቤቶች፣ መንግስት የገነባቸው ቤቶች በመኖሪያና በንግድ ቤት፣ ኪራያቸው ያጠናቀቁና ውዝፍ የኪራይ ዕዳ ያለባቸው፣ የታደሰና ያልታደሰ ውል፣ አበል የሚከፈልባቸው ፣ ማካካሻ ቤት ጉዳይ፣ ዝርዝር በእያንዳንዱ ቀበሌ መረጃው ተሟልቶ ይያዛል፡፡ መረጃው 2ዐ ደቂቃ ውስጥ ወቅታዊ ይደረጋል፡፡ በክ/ከተማና በማዕከል መረጃዎች በ½ቀን ይጠቃለላሉ፡፡ በክ/ከተማው የተጠቃለለው ወደ ማዕከል የመስተዳድሩ የመንግስት ቤት መረጃ በ½ቀን ያጠቃልላል፣ አትሞም ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፡፡
3.12የኮንደሚንየም ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ማካሄድና ወቅታዊ ማድረግ
የኮንደሚንየም ቤት መዝገባ በቀበሌ ይከናወናል፡፡ ማስታወቂያ በ½ሰዓት አዘጋጅቶ ጥሪ ያደርጋል የበፊተኛው መረጃ ከክ/ከተማ ተቀብሎ መኖር አለመኖሩን በ5 ደቂቃ ያረጋግጣል፣ ምልክት ያደርጋል፣ አዲስ ተመዝጋቢ በ1ዐ ደቂቃ ይመዘግባል ካርድ ይሰጣል ከቀበሌ ተመዝግቦና ወቅታዊ ተደርጐ የመጣ መረጃ በክ/ከተማ በኩል በ½ቀን ወደ መረጃ ቋት እንዲገባና ወቅታዊ እንዲሆን ያደረጋል፡፡ ክ/ከተሞች ወቅታዊ ያደረጉት ወደ ማዕከል ይላካል፣ ማዕከልም ከክ/ከተማ ያገኘውን መረጃዎች አጠቃሎ በ1ቀን በመረጃ ቋት ይይዛል፡፡
3.13የኮንደሚንየም ቤቶች ወደ ግል ማስተላለፍ
የኮንደሚንየም ቤቶች ወደ ግል የማስተላለፍ ሥራ በማዕከልና በክ/ከተማ ይተገበራል፡፡ ቅድመ ዕጣ ተግባራት ማለትም የተገነቡ ቤቶች መረጃ ማደራጀት በ2ቀናት፣ የቤቶች ዋጋ ወቅታዊ ማድረግ ጥናት በ1ዐቀናት፣ የማስተላለፍ መመሪያ ማሻሻልና ማዘጋጀት፣ የጨረታ ሰነድና መመሪያ ማዘጋጀት ጥናት በ15 ቀናት፣ ለዕጣ አወጣጥ የሚረዱ ኮምፒዩተሮች ማዘጋጀት፣ ማስገምገም፣ ታዛቢዎች መጥራት፣ ዕጣው የሚወጣበት ቀን ለህዝብ በመገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ፣ ዕጣ ማውጣትና ታትመው በወጡ የዕድለኞች ሥም ዝርዝር መፈረም የዕድለኞች ዝርዝር በጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣ የማድረግና በመስተዳደሩ ድረገፅ የዕጣ ዕድለኞች መልቀቅ ሥራ በ5 ቀናትበማዕከል ይከናወናል፡፡
ዕጣ የደረሣቸው እድለኞች የሚስተናገዱበት ቀን መደልደል ደንበኛ ይዞ የመጣውን መረጃዎች ማገናዘብና ማጥራት፣ በ2ዐ ደቂቃ ውል መዋዋል፣ ካርታና ዕዳና እገዳ ዝግጅት በ4ዐ ደቂቃ፣ መረጃው በ1ዐ ደቂቃ ወደ ባንክ ማስተላለፍና ውሉ ሲመጣ ደግሞ መዝግቦ ቁልፍ የማስረከብ ሥራ በ3ዐ ደቂቃ በክ/ከተማ ይከናወናሉ፡፡
3.14 የሙያ እገዛ
ቤት ልማትን በተመለከተ ከግለሰብ ከድርጅቶችና ከሴክተር መ/ቤቶች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በ1ሰዓት ውስጥ መልስ ይሠጣል፣ ያማክራል፣ ጥናት የሚያስፈልጋቸው ከሆነም ተጠንቶ መልስ ይሰጥበታል፡፡ ይህ ሥራ በማዕከልና በክ/ከተማ ይከናወናል፡፡
3.15 በልማት ለሚነሱ ተከራዮች የኮንደሚንየም /ነባር የኪራይ ቤት መስጠት
ተግባሩ በክ/ከተማ የሚከናወን ሆኖ ደንበኛው /ባለጉዳዩ/ በቅድሚያ በልማት ምክንያት ከሚከራዩበት ቤት መፈናቀላቸውን ያረጋግጣል፣ ተመጣጣኝ ነባር የኪራይ ቤት የቤተሰብ ብዛትና የነባሩ ቤት ይዞታ ያገናዘበ ከተቻለ በነበረበት ቀበሌና ክ/ከተማ ካልሆነ በሌሎች ክ/ከተሞች ተፈልጐ በ5 ሰዓታት ይሰጠዋል፡፡ ነባር ቤት ባልተገኘበት ሁኔታ የኮንደሚንየም ቤት አሠጣጥ አሠራሩን ተከትሎ ይሰጠዋል፡፡
3.16 የጥናት ሥራ
እንደ ኪራይ ተመን ማስተካከያ የመሣሰሉት አነስተኛ ጥናቶች በክ/ከተማ ይጠናሉ፡፡ ሌሎች ጥናቶች ማለትም
Ø የኀ/ተሰቡ ቤት የመሥራት አቅምና ፍላጐት ለማወቅ የሚደረግ ጥናት በ6ዐ ቀናት፣
Ø ዝቅተኛው ኀ/ተሰብ ክፍል የቤት ባለቤት የሚያደርግጥናት በ45 ቀናት
Ø ለቤት ግንባታ የሚውል እገዛ ለማግኘት የማያስችል ፕሮጀክት ማዘጋጀትበ3ዐ ቀናት፣
Ø ለቤት ልማት የሚውል ድጋፍ (fund) ከአገር ውስጥና ከውጭ ማፈላለግ በ3ዐ ቀናት፣
Ø የተገኘው ድጋፍ ለኀ/ተሰቡ የሚደርስበትንና ብድር የሚመለስበትን ስልት ማጥናት በ2ዐ ቀናት፣
Ø የቤት ፖሊሲ፣ ደንብና መመሪያዎች ማግኘት በ45 ቀን
Ø በቤት ልማት ለሚሰማሩ አካላት የሚያበረታታ የህግ ማዕቀፍ ማጥናት በ3ዐ ቀናት
Ø ባለቤት የሌላቸው ቤቶች ለማስተዳደር የሚያስችል ጥናት በ1ዐ ቀናት፣
Ø የኮንደሚንየም ቤቶች ሥራ ክትትል፣ ግምገማ ጥናት በ1ዐ ቀናት፣
Ø የኮንደሚንየም ቤቶች መሸጫ ዋጋ ወቅታዊ የማድረግ ጥናት በ1ዐ ቀናት ወዘተ
በማዕከል ይጠናሉ፡፡ እነዚህ ጥናቶች ለማከናወን መረጃዎች ይሰባሰባሉ፣ ይደራጃሉ፣ ይተነተናሉ፣በመጨረሻም በተዘጋጁት የጥናት ውጤቶች አስተያየትና ትችት ተሰጥቶባቸውና ውሣኔ እንዲያርፍባቸው ተደርጐ ለተግባር ይዘጋጃሉ
3.17 ባለቤት የሌላቸው ቤቶች በባለቤትነት ማስተዳደር
መረጃዎች ይቀበላል፣ አጣርቶ ትክክለኛነታቸውን በ1ቀን ያረጋግጣል ተፈላጊው ጥናት በ5ቀናት አካሂዶ፣ የውሣኔ ሃሣብ ያቀርባል በመጨረሻም ውሣኔ ተሰጥቶበት ቤቶቹ ወደ መንግስት እጅ እንዲዛወሩ ተደርጐ ይመዘገባሉ፡፡ ቤቶቹ ባለው ህግ መሠረት እንዲተዳደር ውሣኔው ከማዕከል ወደ ቀበሌ እንዲወርድ ይደረጋል፡፡ ክ/ከተማው እንደያውቀው ኮፒ ይደርሰዋል
3.18 ነባር የመንግስት ቤቶች ወደ ግል የማስተላለፍ ሥራ
ደረጃቸውን የጠበቁ በመንግስት የተገነቡ ቤቶች ወደ ግል የማስተላለፍ ሥራ በማዕከል የሚከናወን ሆኖ በቂ ጥናት ተደርጐ ለሽያጭ ዝግጁ ይደረጋሉ፡፡ የሚተላለፉበት ሞዳሊቲ ተጠንቶ ይወሰናል፡፡ በውሣኔው መሠረት የቤቶች ሽያጭ በ12 ቀን ሲከናወን ውል የመዋዋልና የቁልፍ ርክክብ ሥርዓት ይካሄዳል፡፡
3.19 ትክክለኛ የቤት መረጃ /ጥቆማ/ መቀበል
ከህግ ውጪ የተያዙ የመንግስት ቤቶች ከኀ/ተሰቡ መረጃ ሲቀርብ መረጃውን መመዝገብ፤ የመረጃ አቅራቢው ስም በመመዝገብ በመረጃው ዙሪያ ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ መረጃዎችን መመርመር፤ ከህግ ጋር ማገናዘብ፣ ማጥናትና የውሣኔ ሀሳብ ማቅረብ፣ ውሣኔ ተሰጥቶበት ለተግባራዊነቱ ማዘጋጀት፤ መረጃ ላቀረበው ዜጋ ቤት ልማት በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ማበረታቻ መስጠት፡፡ ተግባሩ በቀበሌና በክ/ከተማ በ4 ቀን ይከናወናሉ፡፡