ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
አቶ ቢያ ራያ ዋና ስራ አስፈጻሚ
የሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት
1. የሠራተኛ ዝውውር
· የዝውውር ማስታወቂያ ወጥቶ የአመልካቾች ምዝገባ ያደርጋል፣
· ተመዝጋቢዎችን በመስፈር መሠረት መለየት፣
· የተለዩትን በሚወጣው መስፈርት መሠረት ማወዳደርና አሸናፊን መለየት፣
· የዝውውር ውጤት ተገልጾ ተዘዋዋሪው ክሊራንስ እንዲያመጣ ይደረጋል፣
· የምደባ ደብዳቤ ተስጥቶ ሥራ እንዲጀመር ይደረጋል፣
2. ድልድልና ምደባ
· የድልድል ወይም ምደባ ደብዳቤ ይቀርባል፣
· ተደልዳዩ ወይም ተመዳቢው አስፈላጊውን የቅጥር ማስረጃችን እንዲያመጣ ይደረጋል፣
· የሕይወት ታሪክ
· የጤናና የፖሊስ ሰርተፍኬት ወይም ተደልዳዩ ቋሚ ሠራኛ ከሆነ ማህደሩን እንዲያመጣ ወይም እንዲያሟላ ይደረጋል፣
3. የሰው ኃይል ማሟላት ቅጥር፣
· የቅጥር ማስታወቂያ በመረጃ መረብ መልቀቅ በማዕከላዊ ቦታዎች መለጠፍ፣ በፕሬስ እንዲወጣ ማድረግ፣
· በማስታወቂያው መሰረት ምዝገባ ማድረግ፣
· መስፈርቱን የሚያሟሉ(የተሻሉ) አመልካቾችን መለየት፣
· የተመለመለ ዕጩዎች ጥሪ ይደረጋል፤
· ፈተና ተዘጋጅ ይሰጣል፣ የፈተናው ውጤት ይታረማ፣ ውጤቱ ተለይቶ ቃለ ጉባኤ ተዘጋጅቶ ይፈረማል
· የውድድር ውጤቱ ማስታወቂያ ይለጠፋል ለአሸናፊዎች ጥሪ ይቀርባል፤
4. ኮንትራት /ጊዜያዊ ቅጥር
የኮንትራ ቅጥር ስምምነት ለኮሚሽን መላክ
· የቅጥር ማስታወቂያ በመረጃ መረብ መልቀቅ በማዕከላዊ ቦታዎች መለጠፍ፣ በፕሬስ እንዲወጣ ማድረግ፣
· በመዝገባው መሠረት ማጣራትና ዕጩዎችን መመልመል እንዲሁም ጥሪ ማድረግ
· ፈተና አዘጋጅተን መፈተን
· የውድድር ውጤት በማስታወቅያ መለጠፍ
· አሸናፊውን ውል በመስሞላት የቅጥር ደብዳቤ መስጠትና ወደ ሥራ ማሰማራት፣
- የኮንትራት ቅጥር ማራዘም
- የኮንትራት ቅጥር ማራዘም ጥያቄ ይቀርባል
- የኮንትራት ቅጥር ማራዘም ቅድመ ሁኔታዎች በሰው ኃይል አስተዳደር ማሟላትና ማረጋገጥ፣
- የኮንትራት ጥያቄ ስምምነት በመስጠት ውል በማስገባት፣
6. የትምህርትና ሥልጠና ዕጩ ምልመላ፣
· ትምህርትና ሥልጠና ዕድሎች ማስታወቂያ ወጥቶ ምዝገባ ይደረጋል፣
· ከተመዘገቡት ውስጥ አሸናፊውን ለመለየት በመስፈርቱ መሠረት ውድድር ይደረጋል፣
· አሸናፋ ተለይቶ በvirtual team ይወሰናል፣
· አሸናፊው ዕጩ ለሰው ኃብት ሥራ አመራር የሥራ ሂደት ይላካል፣
· ለሥልጠና የተመረጡት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው ውል እንዲፈርሙ ተደርጎ እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡
7. የደረጃ እድገት
· የደረጃ ዕድገት መስታወቂያ አዘጋጅቶ ማውጣት፣
· ተወዳዳሪዎችን መመዝገብና የማያሟሉትን መለየት፣
· ፈተና አውጥቶ መፈተንና አርሞ ውጤቱን በማጠቀለል ቃለ ጉባኤ አዘጋጅቶ ይፈርማል፤
· በውድድሩ ውጤት መሠረት አሸናፊው እንዲቀርቡ ተደርጎ የደረጃ ዕድገት ደብዳቤ ተዘጋጅ ይሰጣል፣
· ለሠራተኛው የሥራ ትውውቅ ተደርጎ ሥራ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡
8. የሰው ኃይል ማስተዳደር፣ ማብቃትና ማትጋት፣
ልዩ ልዩ ፈቃዶች
· በሥራ ሂደቱ ኃላ የተፈረመ የፍቃድ መጠየቂ ቅጽ ተሞልቶ ይቀርባ፣
· ማህደር /ማስረጃ/ ተጣርቶ የፈቃድ ወረቀት ተሞልቶ ይሰጣል፤
9. የደመወዝ ጭማሪ
· በመስፈርቱ መሠረት የደመወዝ ጭማሪ የሚያገኙትን ሠራተኞች ማጣራት ተደርጎ ይለያል፣
· የደመወዝ ጭማሪ ደብዳቤ በኦፊሰር ተዘጋጅቶና ተፈርሞ ለሠራተኛው እንዲደርስ ይደረጋል፣
10. ዲሲፕሊን አፈጻጸም
· የሥራ ሂደት ባለቤት የዲስፕሊን ክስ ከማረጃ ጋር ለደጋፊው የሥራ ሂደት ያቀርባል፣
· የሥራ ሂደቱ የክስ ቻርጅን ጽፎ ለዲሲፕሊን ኮሚቴ ያቀርባል፣
· ኮሚቴው ጉዳዩንነ አይቶ /መርምሮ/ ውሳኔ ይሰጣል፣
· የተሰጠው ውሳኔ ከቃለጉባኤ ጋር በደጋፊው የሥራ ሂደት ቀርቦ የሥራ ሂደቱ የውሳኔን ደብዳቤ ለሠራተኛውና ለሚሠራበት የሥራ ሂደት ኃላፊ እንዲደርስ ተደርጎ ተግባራዊ ይደረጋል፣
አገልግሎት ማቋረጥ
11. በገዛ ፈቃድ ማቋረጥ
· ለቃቂው ለሥራ ሂደቱ ኃላፊ ማመልከቻ ያቀርባል፣
· የሥራ ሂደቱ ኃላፊ በማመልከቻው ላይ ውሳኔ ሰጥቶ ለደጋፊው የሥራ ሂደት ያስተላፋል፤
· ሠራተኛው ክሊራንስ እንዲጨርስ ይደረጋል፣
· የሥራ ልምድና መልቀቂያ ተጽፎና ተፈርሞ ለሠራተኛው ይደርሳል፣
12. ከሥራ ገበታ በመጥፋት
· የሥራ ሂደቱ ባለቤት ሠራተኛው ለ3 ቀናት ሳያሳውቅ ከቀረ ለደጋፊ የሥራ ሂደት ያሳውቃል፣
· ለሠራተኛው የመጀመርያ ይጥሪ ማታወቂያ ይወጣል፣
· በመጀመርያ ጥሪው ካቀረበ ሁለተኛ ማስታወቂያ ይወጣል፣
· በጥሪው ካቀረበ ሰራተኛው እንዲሰረዝ ይደረጋል
13. በጡረታ ማቋረጥ
· ሠራተኛው ጊዜው ከደረሰ ወይም በገዛ ፈቃዱ ለመውጣት ወይም በሞት ከተለየ ማመልከቻ ሲቀርብ ማስረጃው እንዲጣራ ይደረጋል፣
· ማስረጃው የሚፈቅድለት ከሆነ ያለውን እረፍትና ጥቅማጥቅም እንዲወስድ ይደረጋል፣
· ለጡረታ አስፈላጊ የሆኑ ቅጾች ተሞልተውና ፀድቀው ለማህበራ ዋስትና ይላካል፣
14. የማስረጃ ጥያቄ/ የሥራ ልምድ ፣ ለዋስትና ወዘተ…/
· ማስረጃው የጠየቀው ሰራተኛ ማህደር/መረጃ/ይጣራል፤
· የጠየቀው መረጃ ተዘጋጅ ይሰጣል፣
· በጥሪው ካቀረበ ሰራተኛው እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡