የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  
  HOME
  ቂርቆስ ዜናዎች
  አጫጭር ዜናዎች
  kirkos
  በክፍለ ከተማው የሚሰጡ አገልግሎቶች
  ዜና
  About Kirkos InformationOffice
  ቀበሌዎች
  ዜናዎቻችን
  ቂርቆስ ዜና
ቂርቆስ ዜና


በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያና የህዝብ ግንኙነት የሚዘጋጁ በክፍለ ከተማው የሚካሄዱ የዕለት ተዕለት የተግባር ክንውን ፡ 
መልካም ለ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ አደረሳቹ የቂርቆስ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት ወሳኛ ሥራ ሂደት

Sorry! We have moved! The new URL is: 21/11/2001
መለልካም አዲስ ዓመት

ጳጉሜ 02 2001 ዓ.ም

ዜና ቂርቆስ
የምክክር መድረክ
 
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የጉራጌ ልማትና ባህል የተወላጆች ምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
 
የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክፍለከተማው የህዝብ አደረጃት ም/አማካሪ አቶ ብርሀኑ ታደሰ መድረኩ የጉራጌ ህዝቦች ከገጠር እስከ ከተማ ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ነቅሶ በማውጣት ብሎም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
 
የጉራጌ ህዝቦችን የልማት ፍላጎት እውን ለማድረግ 150 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ የታሰበ ቴሌቶን ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የተናገሩት አቶ ብርሀኑ ለታለመው መልካም ተግባር መሳካት 3 አደረጃጀቶች መመስረታቸውን ገልፀዋል፡፡
 
በተበታተነ መልኩ ከሚደረጉ የልማት ተግባራት ይልቅ በተደራጀ መልኩ መንቀሳቀስ ውጤታማ ያደርጋል ያሉት ደግሞ የጉራጌ ልማትና ባህል የብሔራዊ አስተባባሪ አቶ መላኩ ገዙ የጉራጌ ህዝብ በትምህረት፤በጤና እንዲሁም በሌሎች መሰረተ ልማት ዝርጋታ እጥረት ሳቢያ ተቸግሮ ኖሯል ብለዋል፡፡
 
እሳቸው እንደሚሉት ችግሮቹን ለመፍታት በሁሉም የዓለም ክፍል የሚገኙ የዞኑ ተወላጆች የልማቱ ተሳታፊ በመሆን ለውጥ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
 
የምክክሩ ተሳታፊና የዞኑ ተወላጅ አቶ በላይ ውጂ በበኩላቸው በዞኑ የሚታየው ልማት አናሳ መሆን የብሔሩ ተወላጆች ትክክለኛና ቁርጠኛ ተሳትፎ ባለማድረጋቸው በመሆኑ የተገኘውን አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል፡፡ የልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ የዞኑ ተወላጆችም ለተቀደሰው አላማ እንዲረባረቡ ጠይቀዋል፡፡
 
 
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ነሐሴ 28 2001 ዓ.ም
ዜና ቂርቆስ
የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት ከሰኔ 28 ሲሰጥ የነበረው የበጎ ፈቃደኝነት የክረምት መርሀ ግብር ተጠናቀቀ፡፡
 
በወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት የመርሀ ግብር የክፍለ ከተማው ሴክተር ጽ/ቤቶች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን የትምህርት፤ የጤና እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤቶች በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 
  በዚህም የወጣቶችን በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በመጨመር ከፍተኛ ንቅናቄ ስራ የተሰራ ሲሆን የአቻ ለአቻ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች መሰጠታቸውንና የትምህረት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት ስራ ላይ ተሰማርተው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲደረጉ እንዲሁም የከባቢ አየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በርካታ ችግኞች መተከላቸውን ከየጽ/ቤቶቹ የተወከሉ አካላት ተናግረዋል፡፡
 
 በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃኝነት ስራዎች ላይ በመምህርነት ሲሰራ መቆየቱን የገለፀው ወጣት ተገኝ ፀጋው እንደተናገረው የወጣቶች በጎ ፈቃደኝነት ከአሁን በፊትም የነበረ ቢሆንም እንደአሁኑ ግን የተጠናከረ አልነበረም ብሏል፡፡ ወጣቱ እንዳለው በጎ ፈቃደኝነት ተግባር ተጠናክሮ ቢቀጥል ለሀገራችን ለውጥ ማምጣት እንዲችል ከማድረጉም ባሻገር ወጣቱ አልባሌ ቦታዎች እንዳይውል ያደርገዋል ብለዋል፡፡
 
የወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር ቀጣይነት እንዳለው የተናገረው ደግሞ የክፍለ ከተማው ወጣት አደረጃጀት ፕሬዘዳንት ወጣት ዮናስ ግርማ ነው፡፡ እንደ ወጣት ዮናስ ገለፃ በክረምት የበጎ ፈቃደኝነት ስራዎች በርካታ ወጣቶች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን በጤና ዘርፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡
 
የበጎፈቃደኝነት ተግባር ላይ መሳተፋቸው ያላቸውን ክህሎት የሚያሳይና ወጣቶች በፍቃደኝነት የተመሰረተ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ በማድረግ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል ብሏል፡፡
 
የወጣቶችን ተሳታፊነት ለማረጋገጥ በ5 ዋና ዋና ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ መደረጉን የተናገሩት የክፍለከተማው የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ሎሬንሶ ወጣቶች በችግኝ ተከላ፤በትምህረት፤በስነተዋልዶ፤በሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል፡፡
 
በክረምቱ የመርሀ ግብር 28 ሺ 98 ወጣቶች ተሳታፊዎች እንደነቡ የተናገሩት ኃላፊው ወጣቶች የተጀመረውን መልካም ስራ በመግባባትና በአዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲያጠናክሩት አሳስበዋል፡፡
 
በእለቱ የኤች.አይ.ቪ ኤድስን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያሳይ ሙዚቃዊ ድራማ የቀረበ ሲሆን ለበጎ ፈቃደኝነት ስራው አስተዋፅኦ ላደረጉ ጽ/ቤቶችና ወጣቶች የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
0913049933
 
 
 

 ነሐሴ 28 2001 ዓ.ም

ዜና ቂርቆስ
የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት
 
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት ከሰኔ 28 ሲሰጥ የነበረው የበጎ ፈቃደኝነት የክረምት መርሀ ግብር ተጠናቀቀ፡፡
 
በወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት የመርሀ ግብር የክፍለ ከተማው ሴክተር ጽ/ቤቶች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን የትምህርት፤ የጤና እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤቶች በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 
  በዚህም የወጣቶችን በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በመጨመር ከፍተኛ ንቅናቄ ስራ የተሰራ ሲሆን የአቻ ለአቻ የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች መሰጠታቸውንና የትምህረት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት ስራ ላይ ተሰማርተው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲደረጉ እንዲሁም የከባቢ አየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በርካታ ችግኞች መተከላቸውን ከየጽ/ቤቶቹ የተወከሉ አካላት ተናግረዋል፡፡
 
 በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃኝነት ስራዎች ላይ በመምህርነት ሲሰራ መቆየቱን የገለፀው ወጣት ተገኝ ፀጋው እንደተናገረው የወጣቶች በጎ ፈቃደኝነት ከአሁን በፊትም የነበረ ቢሆንም እንደአሁኑ ግን የተጠናከረ አልነበረም ብሏል፡፡ ወጣቱ እንዳለው በጎ ፈቃደኝነት ተግባር ተጠናክሮ ቢቀጥል ለሀገራችን ለውጥ ማምጣት እንዲችል ከማድረጉም ባሻገር ወጣቱ አልባሌ ቦታዎች እንዳይውል ያደርገዋል ብለዋል፡፡
 
የወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር ቀጣይነት እንዳለው የተናገረው ደግሞ የክፍለ ከተማው ወጣት አደረጃጀት ፕሬዘዳንት ወጣት ዮናስ ግርማ ነው፡፡ እንደ ወጣት ዮናስ ገለፃ በክረምት የበጎ ፈቃደኝነት ስራዎች በርካታ ወጣቶች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን በጤና ዘርፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡
 
የበጎፈቃደኝነት ተግባር ላይ መሳተፋቸው ያላቸውን ክህሎት የሚያሳይና ወጣቶች በፍቃደኝነት የተመሰረተ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ በማድረግ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል ብሏል፡፡
 
የወጣቶችን ተሳታፊነት ለማረጋገጥ በ5 ዋና ዋና ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ መደረጉን የተናገሩት የክፍለከተማው የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ሎሬንሶ ወጣቶች በችግኝ ተከላ፤በትምህረት፤በስነተዋልዶ፤በሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል፡፡
 
በክረምቱ የመርሀ ግብር 28 ሺ 98 ወጣቶች ተሳታፊዎች እንደነቡ የተናገሩት ኃላፊው ወጣቶች የተጀመረውን መልካም ስራ በመግባባትና በአዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲያጠናክሩት አሳስበዋል፡፡
 
በእለቱ የኤች.አይ.ቪ ኤድስን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያሳይ ሙዚቃዊ ድራማ የቀረበ ሲሆን ለበጎ ፈቃደኝነት ስራው አስተዋፅኦ ላደረጉ ጽ/ቤቶችና ወጣቶች የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ነሐሴ 26 2001 ዓ.ም
ዜና
በህፃናት ላይ በሚደርሰው ጥቃት ዙሪያ የተደረገ ውይይት
 
በህፃናት ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ እንደሚሻ ተገለፀ፡፡
 
የቂርቆስ ክፍለከተማ የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ከአዲስ አበባና ከክፍለከተማው ኤች.አይቪ.ኤድስ መከላከልናመቆጣጠር እንዲሁም ከብራይት ፎርችልድረን ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በህፃናት ላይ በሚደርሰው ፆታዊ ጥቃት ዙሪያ የማህበረሰብ ውይይት አካሂደዋል፡፡
 
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለከተማው የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ራሔል ሙሉጌታ እንደተናገሩት በሀገራችን የህፃናትላይ የሚደርሰው ፆታዊ ጥቃት እየተስፋፋ ይገኛል ይህንን አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ለማስቆም የማህበረሰብ ውይይቱ የጉላ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
 
የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ አያሌው በውይይቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ህፃናት የሀገር ተስፋና የትውልድ ተተኪ ናቸው፤ ይሁንና በሚደርስባቸው ፆታዊ ጥቃት ሳቢያ ለኤች.አይ.ቪኤድስ ይጋለጣሉ በመሆኑም የኤች.አይ.ቪኤድስን ስርጭት ለመግታትም ሆነ ህፃናትን ከጥቃት ለመታደግ ህብረተሰቡ ትኩረት ሰጥቶ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
 
የብራይት ፎርችልድረን ዳይሬክተር አቶ ሱልጣን ሙሄ በበኩላቸው በወንድ ህፃናት ላይ የሚደርሰው ፆታዊ ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ይገኛል ይሁንና ለጉዳዩ የተሰጠው ትኩረት ግን አናሳ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም ህፃናት በሚደርስባቸው ጥቃት ሳቢያ የሚጠበቅባቸውን እንዳያበረክቱ አግዷቸዋል ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ለጉዳዩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትኩረት እንዲጡት ጠይቀዋል፡፡
 
በክፍለከተማው የህፃናት መብቶች ማስከበር፤ ድጋፍና እንክብካቤ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ወ/ሮ እየሩሳሌም ሀይሉ እንደተናገሩት የውይይት መድረኩ በህፃናት ጥቃት ዙሪያ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ከመጨመሪም ባሻገር ጥቃቱ እንዲቆም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲደርጉ ያግዛል ብለዋል፡፡
 
በውይይት መድረኩ ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች፤የወጣትና የሴት አደረጃጀቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
0913049933
 
 ነሐሴ 27 2001 ዓ.ም
 
ዜና
 
ትምህርት ጽ/ቤት ጉባኤ
 
 
የቂርቆስ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ዓመታዊ የትምህርት ጉባኤውን አካሄደ፡፡ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም እንደነበረው ተመልቷል፡፡
 
ትምህርት ጽ/ቤቱ ዓመታዊ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት እንደተገለፀው ትምህርት ጽ/ቤት በዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡
 
በእለቱ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ቀበሌዎች ቀበሌ 08/09፣02/03 እና 17/18 ትምህርት ጽ/ቤቶች ዓመታዊ ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
 
የቂርቆስ ክፍለከተማ ትምህርተ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እንደተናገሩት በዓመቱ በትምህረት ጽ/ቤት በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት አበረታች እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በዓመቱ ትምህረትን የሚያቋርጡና የሚደግሙ ተማሪዎች ቁጥር ለመቀነስ በተደረገው ጥረትም ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
 
በዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም አሳይተዋል ተብለው ሪፖርታቸውን ካቀረቡት ቀበሌዎች መካከል የቀበሌ 08/09 ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ብርሀኑ እንደተናገሩት ቀበሌአቸው በክፍከተማ ደረጃ በትምህረት ጥራትፓኬጅ የአንደኝነትን ደረጃ ያገኘ ሲሆን በከተማ ደረጃም በ99 ቀበሌዎች በ2ኛ ደረጃ መቀመጡን ገልፀዋል፡፡
 
 
ከስድስት የትምህርት ጥራት ፓኬጅ አራቱን ተግባራዊ በማድረግ መልካም አፈፃፀም እንዳሳዩ ተናግረዋል፡፡ በዓመቱ በተደረገው ጥረት የሚደግሙና የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር መቀነስ እንደተቻለ የጠቀሱት አቶ ተስፋዬ 14 ከሚሆኑግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከ308 ሺ ብር በሚበልጥ ወጪ አቅም የሌላቸው ተማሪዎች ትምህርት እንዲያገኙ መደረጉን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
ሐምሌ 29 2001ዓ.ም.
ዜና ቂርቆስ
የቀበሌ 05/06/07
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ 05/06/07 አስተዳደር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለተመዘገቡ አበረታች ተግባራት ህዝብን ያሳተፈ ስራ መስራቱ መሆኑን ገለፀ፡፡
            የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው መኮንን እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የተሸለ አፈጻጸም ካስመዘገቡ ቀበሌዎች አንዱ ነው በበጀት አመቱ አበረታች ተግባራት ሊመዘገብ የቻለው ከ700 በላይ ከሚሆኑ በቀበሌው ነዋሪዎች ጋር በዕቅዱ ዙርያ ሰፊ ውይይት መደረጉ ነው፡፡
      ከቀበሌው ነዋሪዎች በተሰነዘሩ የማስተካከያ ሀሳቦች መሰረትም በቀበሌው የሚታየውን ጅምር የመልካም አስተዳደርና የልማት እንቅስቃሴ በማፋጠን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
      እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው አገላለጽ በበጀት ዓመቱ 5 ነባር ፕሮጀክቶችና 2 አዳዲስፕሮጀክቶች የነበሩ ሲሆን ነባር ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን አዳዲስ ፕሮጀክቶችም ግንባታቸው በማፋጠን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
      የቀበሌ ጽ/ቤት ፣ ቤተ-መጻህፍ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር የተገነባው የትምህርት ቤቶች አጥር በበጀት ዓመቱ ከተገባደዱ ፕሮጀክቶች መካከል ተጠቃሾች መሆናቸውን አስታውዋል፡፡
      የህዝብ ንቅናቄን ከመፍጠር አንጻር ሰፊ ስራ መስራቱን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው የወጣትና የሴት አደረጃጀቶችን በመፍጠር በልማት እንቅስቃሴዎች ላይ የራሳቸውን ሚና እንዲያበረክቱ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
      በቀበሌው በሚካሄዱ የልማት ተግባራት ላይ የባለድርሻ አካት ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይጫወታል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በ7 ሚሊዮን ብር ወጪ ህብረተሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካት በመተባበር አከባቢያቸውን ጠጠር ድንጋይ ከማልበስ አንስቶ ለጎርፍ መከላከያነት የሚያገለግሉ ግንባታዎችን ለመገንባት እንቅስቃሴዎችን መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡
      በበጀት ዓመቱ ትኩረት ከተሰጣቸው ስራዎች መካከል የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥን መተግበር መሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው የቀበሌ ጽ/ቤቱን በ አዲስ መልኩ በመገንባትና ያለውን የሰው ሀይል በመጠቀም ለቀበሌው ነዋሪዎች ግልጋሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸው የበጀትና የሰው ሀይል እንዲሁም የግብዓት እጥረቶች እንዳሉ አልሸሸጉም፡፡
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
ሐምሌ 27/2001
ዜና ቂርቆስ
ህዝቡ የሚጠይቃቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቁዎች በመሠረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ የቀበሌዎች ምክርቤት አባላት ሚና የጎላ መሆኑ እንዳለበት ተገለጸ ፡፡
       በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ስድሰት ቀበሌዎች የቀበሌ ም/ቤቶች 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂደዋል፡፡
      በጉባኤዎቹ ላይ እንደገለጸው ህዝቡን በሰላም በልማትና በመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ማድረግ የመንግስት አላማ ሲሆን መንግስትና ህዝብ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሀገራችንን በልማት ጎዳና ተጉዛ ከበለጸጉ ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍ የሁሉም አስተዋጽኦ የጎላ መሆን እንደሚገባው ተመክጸዋል፡፡
      በቀበሌ 01/19 በተካሄደው ጉባኤ ላይ በቀረበው ሪፖርት  እንደተገለጸው በበጀት ዓመቱ አበረታችየሚባል ውጤቶች እንደተመዘገቡና ለህዝቡ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠትም አዲስና የመስረረታዊ አሰራር ሂደት ለውጥ ተግባራዊ መደረጉ ተገጸዋል፡፡
      የሴቶችንና የወጣቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት እንዲችልም የሴቶችና የወጣቶች ፎረሞች እንዲጠነክሩ ጥረት መደረጉ ተገልጸዋል፡፡
      የቀበሌ 15/16 አፈ ጉባኤ አቶ ወርቁ መኮንን ከጉባኤው በኋላ እንደተናገሩት ም/ቤቱየ2001 ዓ/ም መልካም ተሞክሮዎችን በመድገምና ደካማ ጎኖችን በማሻሻል በ2002 ዓ/ም የተሸሉ ግቦችን ለመምታት መነሳሳታቸውን ገልጸዋል ፡፡
      በሁሉም ቀበሌዎች በተካሄዱት ጉባኤዎች የ3ኛውን የም/ቤት ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ለተሳታፊዎቸረ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኃላ የፀደቀ ሲሆን በተመሳሳይየ2001 ዓ.ም ዕቅድ ክንውነን ሪፖርትና የ2002 በጀት ዓመት ዕቅድ ለም/ቤት አባላት ቀርቦ ጸድቋል፡፡
      በተመሳሳይ ጉባኤዎችም በቀበሌ 17/18 በቀበሌ 02/03 እና በቀበሌ 20/21 እንዲሁም በቀበሌ 10 የም/ቤቶች 4ኛ መደበኛ ጉባኤዎች ተካሂደዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
0913-278575

ሐምሌ 27/2001 ዓ.ም.
ዜና ቂርቆስ
የፊትበር መለስተኛ ቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ 540 ተማሪዎችና በተለያየ የትምህርት መስክ አስመረቀ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምርያ የፊት በር መለስተኛ ቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ማዕከል በአምስት የትምህርት መስክ ለ10 ወራት ያሰለጠናቸውን 540 ተማሪዎችን እሁድ ሐምሌ 26/2001 በማዕከሉ ግቢ ውስጥ በደማቅ ስነስርዐት ማስመረቁ ተገለጸ፡፡
      የፊትበር መለስተኛ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ካህ ሳይ ገ/መድህን በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ዛሬ ተቋሙ ለ13ኛ ጊዜ በአምስት የትምህርት መስክ ማለትም በኮንስትራክሽን ፣ በቧንቧ ስራ፣ በኤሌትሪክስቲ ፣ብረታብረት ስራና በአናጺና ቀለምቅብ በርካታ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ማስመረቁን አስታውሰው በአሁኑ ሰዓት መንግስት ወጣቱ ትውልድ ከጥገኝነት ተላቆ ስራ ፈጣሪ በመሆን ለራሱ ፣ ለቤተሰቡ ብሎም ለሀገሩ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ካሉ በኃላ ከዚህ አንጻር ተቋሙ ለ140 ተማሪዎች በወር ለአንድ ተማሪ እስከ 100 ብር ወጪ በማድረግ ለ8 ወራት በማእከሉ ግቢ ውስጥ ለ2 ወር ከግቢ ውጭ የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ ማመቻቸቱን ገልጻዋል፡፡
      የዕለቱ የክብር እንግዳ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቴክነለክና ሙያ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ግደይ አማረ በበኩላቸው በሀገራችን የተጀመረው ቴክኖሎጂ በዚሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ግደይ ወጣቱ ትውልድ ስራ ፈጣሪ እንጂ ስራ ፈላጊ መሆን እንደሌለበት አስገንዝበው ተመራቂዎች ወደ ስራ ሲገቡ ትልቅ ኃላፊነት አእነደሚጠብቃቸው አውቀው ከአሁኑ መዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
      ከተመራቂዎች መካከል ወጣት ሀይሉ አማን ከቆይታው ከተቋሙ ያገኘውን እውቀት ወደ ተግባር ቀይሮ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

      ተመራቂዎችም ቀደም ብለው ከት/ቤቱ ባገኙት ግንዛቤም በህብረት ተደራጅተው ወደ ስራ ለመግባት መዘጋጀታቸውን ወጣቱ ጨምሮ ገልጸዋል፡፡
      በመጨረሻም በትምህርታቸው ላቅ ያለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማራቂዎች ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከአቶ ግደይ አማረ እጅ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
 
ሪፖርተር
አምሳሉ ታደሰ
 
 
22/11/2001
ዜና ቂርቆስ
              በማህበር መደራጀት ትልቅ ሀይል መሆኑ ተገለጸ             
መንግስት በፈጠረው ምቹ የመደራጀት ሁኔታ በመጠቀም በቀበሌ 02/03 የሚገኙ ባምቦ የመኪና እጥበት ሥራ ማህበር አባላት ኑሮአቸው እንደተቀየረ ገለጹ ፡፡
 
ማህበሩ በግንቦት 1996 ዓ/ም አስር አባላት ሆነው በ1000 ብር ካፒታል መንግስት በሰጣቸው የመሥሪያ ቦታ ላይ በመደራጀት የመኪና እጥበት ሥራ ላይ ተሰማሩ ፡፡
 
የማህበሩ ሊ/መንበር ወጣት ድረሰው ጌታቸው እንደተናገረው በየአስፋልት ዳር በተናጠል ይሰሩ የነበሩ አስር ወጣቶች በ1996 ዓ/ም በመደራጀት በ1000 ብር ካፒታል መንግስት በሰጣቸው የሥራ ቦታ ላይ የመኪና እጥበት ሥራ ጀምረው ዛሬ በ2001 ዓ/ም የ50000 ብር ካፒታል ባለቤት ሆነዋል፡፡ ከሚሰሩበት ቦታ ርቀው ውሀ በባልዲ በማጓጓዝ ሲሰሩ የነበሩ ወጣቶች አሁን ግን ከሚያገኙት ገቢ በመቆጠብ ቧንቧ በማስገባት የመስራት አቅማቸውን በማሳደግ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
 
ባለ ራእዩ ወጣት ድረሰው ጌታቸው ስራን ሳይንቁ በርትተው ከሰሩ ከትንሽ ነገር ተነስተው ወደ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል ገልጸው ወጣቱ ተበታትኖ ከመሥራት ይልቅ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እምደሚባለው ተደራጅተው በመስራት ለራስ አልፎ ለሀገር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግሯል፡፡
 
የባንቦ መኪና እጥበት ማህበር ጸሀፊ ወጣት ሲሳይ በላይ በበኩሉ በፊት በተናጠል አስፋልት ዳር መኪና ያጥብ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በማህበር በመደራጀቱ ተጠቃሚ እንደሆነና ከበፊቱ ጋር ሲያስተያይ የቀን ገቢው እንደጨመረ ተናግሯል፡፡ በማህበር መደራጀታቸው ትልቅ ሀይል እንደሆናቸው ወጣቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡
 
የቀበሌ 02/03 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የሥራ ሂደት መሪ አቶ ኢዮብ አለባቸው እንደገለጹት ማህበሩ በትንሽ ካፒታል ተነስተው የተፈጠሩላቸውን ምቹ የመደራጀት ሁኔታዎችን በመጠቀም ዛሬ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ ችለዋል፡፡ ለማህበሩ የብድር አገልግሎት የክትትልና የሙያ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው አቶ ኢዮብ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ኢዮብ ለማህበሩ በሥራው ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለማቃለልና ጥሩ ክትትል እንደሚያደርጉ ገልጸው ማህበሩም ጠንክሮ በመስራት ለሌሎች ወጣቶች አርአያ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
 
አዘጋጅ
አምሳሉ ታደሰ
0911-94-35-70
 
ሐምሌ 22 2001ዓ.ም.
ዜና ቂርቆስ
የቀበሌ 20/21 የስራና ከተማ ልማት ጽ/ቤት
በቂርቆስ ክፍለከተማ የቀበሌ 20/21 ስራና ከተማ ልማት ጽቤት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት አበረታች ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ፡፡
በበጀት ዓመቱ በርካታ የልማት ስራዎች ማከናወናቸውን የገለጹት የቀበሌ 20/21 የስራና ከተማ ልማት ጽ/.ቤት አቶ መንገሻ መስፍን ከተከናወኑት የልማት ስራዎች መከቃከል ሁለገብ የወጣት ማዕከሉ ግንባታ ከ50 በመቶ በላይ ስራው ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች የዋለው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ሲሆን ከ300 በላይ ለሚሆኑ የስራ አጦችም ጊዚያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ገልጻዋል፡፡
በቀበሌው የሚታየውን የመጸዳጃ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ለአራት አባሪዎች መጠቀሚያ የሚሆን መጸዳጃ ቤት ተገንብቶ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችም እድሳት ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡
በክፍለ ከተማው ብሎም በቀበሌው በሚከናወኑ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሚና እንዳለው የተናገሩት ኃላፊው ለሁለገብ የወጣት ማዕከሉ ግንባታ እንዲውል 68 ሺ ብር በማሰባሰብ ገቢ ከማደርጋቸውም ባለፈ የ2 ኪ.ሜትር መንገድ እንዲገነባ አስተዋጽኦ ካደረጉ አካላት መካከል የቀበሌው ነዋሪዎች ተጠቃሾች ናቸው ብሏል፡፡
20 በመቶው የሚሆነው ስራው የተጠናቀቀው የቀበሌው ጽ/ቤት በ2002 የበጀት ዓመት ሊጠናቀቁ ከታቀዱ ተግባራት አንዱ ሲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ለተገነባው መንገድ የመንገድ መብራት ማሰራት ፤8 መጸዳጃ ቤቶችን መገንባትም ፤የፍሳሽ ማወገጃዎችን መገንባትም በዚሁ የበጀት ዕመት ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚሰጡ የልማት ስራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
ሐምሌ 22/2001
ዜና ቂርቆስ
የቀበሌ 13/14 ወጣቶች ወጣት ማዕከል በመገንባቱ ተደሰቱ
    በቀበሌያቸው ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ የወጣት ማዕከል እየተገነባ በመሆኑ መደሰታቸውን በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 13/14 የሚገኙ ወጣቶች ገለጹ፡፡
     በቀበሌው እየተገነባ የሚገኘው ወጣት ማዕከል በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኝ ሲሆን የቀበሌው ወጣቶችም "እኛ ወጣቶች ቤታችንን እንገነባለን" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ጊዝያት የበጎ ፈንድ አገልግሎት በመስጠት በወጣት ማዕከላት ግንባታ ላይ እየተረባረቡ ይገኛሉ ፡፡
በቀበሌው ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የወጣት ማዘውተሪያና ጊዜ ማሳለፊያ የልነበረ ሲሆን አሁን እየተገነባ ያለው ወጣት ማዕከል 2.4 ሚልዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን የኮንፒውተር ማዕከል የስፖርት ማዘውተሪያ፣ ቤተ-መጻህፍትና ሲኒማ ያካተተ እንደሚሆን ታቋል፡፡
የቀበሌው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያሬድ ሀጎስ እንደተናገሩት ማዕከሉ ሲጠናቀቅ በየቀኑ ከ800-1000 የሚደርሱ ወጣቶችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን በአከባቢው የሚታየውን የወጣት መዝናኛ ችግር እንደሚቀርፍ ተናግረዋል ፡፡ ወጣቱም በእኔነት ስሜት ልማት እየተረባረበ ሲሆን በቀበሌው የሚገኙ ወጣቶች "እኛ ወጣቶች ቤታችንን እንገነባለን" በሚል መሪ ቃል ከ200 በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በግንባታው እገዛ እንዳደረጉ አመልክተው በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ያሉ ወጣቶችና ከአደረጃጀት ውጪ ያሉትም ከወጣት ማዕከሉ ግንባታ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ወጣት ዮናስ ማሞ የተባለው የቀበሌው የወጣቶች ፌደሬሽን ሰብሳቢ በበኩሉ ከዚህ ቀደም በቀበሌው ምንም የወጣት መዝናኛ ቦታ እንዳልነበረ ገለጾ ይህ ዘመናዊ ወጣት ማዕከል ተገንብቶ ቢጠናቀቅ የወጣቱን የመዝናኛ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ይቀርፋል ብሏል፡፡
ወጣት ፍጹም ገ/ስላሴ በበኩሉ በቀበሌው ቀድሞ ወጣት ማዕከል ባለመኖሩ አብዛኛው ወጣት ግዜውን አልባሌ ቦታ ያሳልፍ እንደነበር አመልክቶ አሁን እየተገነባ ያለው የወጣት ማዕከል ወጣቱ ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከማስቻሉም በላይ ወጣቶቹ ለተለያዩ ሱሶች እንዳይዳረጉ ይረዳቸዋል ብሏል፡፡
ሪፖርተር
 ታሪኩ እንዳለ
 0913-27-85-75
ሐምሌ 22/2001
ዜና ቂርቆስ
ባምቦ የመኪና እጥበት 50000 ብር ካፒታል ተዘማጭ ማድረጉን ገለጸ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 02/03 ስር የሚገኘው ባምቦ የመኪና እጥበት የህ/ሥራ ማህበር አባላት በማህበር በመደራጀታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
የህ/ሥራ ማህበሩ በ1996 ዓ/ም አስር አባላትን አቅፎ የተመሰረተ ሲሆን መነሻ ካፒታሉም 1000 ብር ነበር፡፡ ይሁንና ወጣቶቹ ጠንክረው በመስራታቸው አሁን ያላቸው ተቀማጭ ካፒታል 50ሺህ ብር መድረሱን ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡
የማህበሩ ሊ/መንበር ወጣት እንዳሻው ጌታቸው እንደተናገረው የማህበሩ አባላት ቀድሞ አብዛኞቹ ሥራ አጥ እንደነበሩ አንዳንዶቹም በተናጠል በመኪና እጥበት ሥራ የተሰማሩ እንደነበሩ አመልክቶ አሁን በማህበር በመደራጀታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
መንግስት በቀረጸው የጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ስትራቴጂ በመታቀፋችን ለውጥ አምጥተናል ያለው ወጣት እንዳሻው ከክ/ከተማና ከቀበሌዎች የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያገኙ አመልክቷል፡፡
ወጣት ሲሳይ በላይ የተባለው የማህበሩ ጸሀፊ በበኩሉ በማህበር ተደራጅተን በመስራታችን የራሳችንን ገቢ ለመፍጠር ችለናል ካለ በኋላ ሌሎች ወጣቶችም ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ ላይ ከሚያባክኑ ሥራ ፈጥረው ቢሰሩ ውጤታማ ሲሆኑ ይችላሉ ብሏል፡፡
በቀበሌ 02/03 የጥቃቀቅንና አነስተኛ የሥራ ሂደት መሪ ወጣት ኢዮብ አለባቸው ስለማህበሩ እንደገለጸው በ1996 ዓ/ም በ10 አባላት የተመሰረተ ሲሆን ከእያንዳንዱ አባል በተዋጣ 1000 ብር ሥራ መጀመራቸውን ገልጾ አሁን ያለበት ደረጃም እስከ 50000 ብር ካፒታል እንዳላቸው ተናግሯል፡፡ የቀበሌው ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤትም የብድር አቅርቦት ከማመቻቸት ጀምሮ የመስሪያ ቦታ መስጠት እንዲሁም በሂሣብ አያያዛቸው ዙሪያም ዘመናዊ እንዲሆን የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚሰጧቸውና በየጊዜውም እንደሚከታተሏቸው ወጣት ኢዮብ ተናግሯል፡፡
 ሪፖርተር
 ታሪኩ እንዳለ
 0913-27-85-75
 
 
ዜና ቂርቆስ
ህገ-ወጥ እርድ
ህገወጥ ተግባራትን በማስቆም ረገድ የህብረተሰቡ ተሳትፎ የላቀ ጠቀሜት እንዳለው ተመለከተ፡፡
 
በቂርቆስ ክፍለከተማ የለገሀር ፖሊስ ጣቢያ የኮሚኒቲ ፖሎሲንግ ኃላፊ ኢኒስፔክተር ዳኜ አለሙ እንደተናገሩት በቀበሌ 15/16 ክልል ውስጥ ቀጠና 3 እና ቀጠና 5 በሚባሉ አካባቢዎች በርካታ ህገ-ወጥ እርዶች ይካሄዳሉ ፡፡ በዚህም ፖሊሶች ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆሞ መሰረታ 5 የታረዱ የበግ ስጋዎች ፤ 9 የበግ ቆዳዎችና 2 በጎች ከነሰ,ፍሳቸው መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡
 
በጸጥታ ጉዳይና ጠቅላላ በቀበሌው በሚካሄዱ ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ ከህብረተሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት መካሄዱን ያስታወሱት ኢንስፔክትሩ እነዚህን ነውጽህናቸው ባልተጠበቀ ቦታዎች የሚታረዱትን ስጋዎች መልሶ ህብረተሰቡን ጉዳት ላይ የሚጥል በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር አብሮ ከስራ ህገ-ወጥ ስራዎችን ማጥፋት ይቻላል ብለዋል፡፡
 
ረዳት ኢንስፔክተር ዳሉ ገብሩ በበኩላቸው በቀን ውስጥ ከ10 እስከ 15 ህገ-ወጥ እርድ እንደሚካሄድ ገልጸው ከደንብ አስከባሪዎችና ህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በቀጣይም በየአከባቢው በመዘዋወር ክትትል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
 
በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የህገ-ወጥ እርድ ቁጥጥር ቡዱን መሪ አቶ ሰይፈ ተክሌ እንደገለጹት ጤንነታቸው በህክምና ባለሙያዎች ያልተረጋገጠና ንጽህናው ባልተጠበቀ ቦታ ላይ የሚታረዱ እንስሳዎችን በአከባቢው ደንብ አስከባሪዎች ከያዙት በኋላ እንሚረከቡት ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ለጤና ጠንቅ የሆኑ ተግባራትን በማሳወቅ እረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
 
21/11/2001
 
ዜና ቂርቆስ
የክ/ከተማው አመራሮች አሻራ ሰጡ፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ የአመራር አካላትና የካቢኔ አባላት በአሻራ የተደገፈ የግብር አከፋፈል ስርዓቱን ለመቀበል አሻራ ሰጡ፡፡
 
የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ አያሌውና ም/ሥራ አስፈጻሚና የማስታወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/እግዚአብሄር ገ/ማሪያም እንዲሁም የክ/ከተማዋ የካቢኔ አባላትና የጽ/ቤት ኃላፊዎች ዘመናዊና በአሻራ የተደገፈ የግብር አከፋፈል ስርዓትን ለመቀበል አሻራቸውን በመስጠት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወስደዋል፡፡
 
የክ/ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲሣይ አያሌው አሻራቸውን ከሰጡ በኋላ እንደተናገሩት በአሻራ የተደገፈ የግብር አከፋፈል ሥርዓት መኖሩ አሰራሩን ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ የግብር ከፋዩን የተሟላ መረጃ ለመያዝ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
 
በአገሪቱ በጣት አሻራ የተደገፈ የግብር አከፋፈል ስርዓት መዘርጋቱ ድግግሞሽን በማስቀረት መንግስት ምን ያህል ግብር ከፋዮች እንዳሉት ከማሳወቁ በተጨማሪ ወደ ግብር አከፋፈል መረቡ የገቡትንና ያልገቡትን ለይቶ ለማወቅ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡
 
የክ/ከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዘንጊያ ካሳ በበኩላቸው በጣት አሻራ የተደገፈ የግብር አሰባሰብ ስርዓት መዘርጋቱ ቀደም ሲል የነበረውን ለአንድ ግብር ከፋይ ከአንድ በላይ ቲን ቁጥር መሰጠቱን አስቀርቶ ለአንድ ግብር ከፋይ አንድ ብቻ ቲን ቁጥር እንዲሰጥ ያስችላል ብለው ሥርዓቱ ማንኛውንም ግብር መክፈል የሚችልና ወደፊት ግብር ሊከፍሉ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡት የግልና የመንግስት ተቀጣሪዎች እንዲሁም በግል ሥራ የተሰማሩትን ያጠቃልላል ብለዋል፡፡ ግብር መክፈል የሚገባቸው ዜጎችም ያለውን ጊዜ በመጠቀም እንዲመዘገቡና አሻራ በመስጠት የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

 ሪፖርተር
 ታሪኩ እንዳለ
 0913-27-85-75
 
21/11/2001
 
ዜና ቂርቆስ
ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አበረታች ተግባር መከናወኑን ገለፀ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ የሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች እንደነበሩ አመለከተ፡፡
 
በመሬት ልማት ባንክ፣ በከተማ ፕላንና የመሬት አጠቃቀም፣በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደርና በመሳሰሉት ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ዘርፎች የተሰጡት አገልግሎቶች አመርቂ እንደነበሩ ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡ 
 
የክ/ከተማው ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሀ ገ/እግዚአብሄር እንደተናገሩት በክ/ከተማዋ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል በክ/ከተማ ደረጃና በቀበሌዎች ግብረሀይል ተቋቁሞ በየጊዜው እየተገናኘ በመወያየት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አመልክተው መሬት ወስደው ግንባታ ያልጀመሩ ባለሀብቶችን በተመለከተም ግንባታ እንዲጀምሩ በማሳሰብ ከባለሀብቱ ጋር ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ዓመትም ከ12000 ካሬ ሜትር በላይ መሬት ለኢንቨስትመንትና ለተለያዩ ልማቶች እንዲውሉ ለሊዝ ጨረታ መቅረቡን ያመለከቱት ሥራ አስኪያጁ በቀጣይ ዙር ለሊዝ የሚቀርብ ከ35 ሄክታር በላይ መሬት ለማዘጋጀት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
 
ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ወደየቀበሌዎች ወርደው ለተገልጋዩ በቅርበት እንዲሰጡ ለማድረግም የG+1 ቪላ ቤት ግንባታ ፈቃድ መስጠትን ጨምሮ የድንበር ይገባኛል ጥያቄና የዕድሳት ፈቃድ የመሳሰሉት አገልግሎቶች ወደ ቀበሌዎች ወርደው አገልግሎቶች እየሰጡ እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡አገልግሎቱ መቼና ደንበኛን ማዕከል ያደረገ እንዲሁም ለማድረግም ፋይሎችና የይዞታ ማህደሮች ወደ ቀበሌዎች እየወረዱ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
 
በውበትና መናፈሻ አገልግሎት ዘርፍም በክ/ከተማው ከሚገኙ የተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በአካባቢያቸው ፓርኮችን እንዲያለሙና አካባቢያቸውን እንዲያጸዱ ከመደረጉ በተጨማሪ የመንገድን ውበት ለመጠበቅም የመንገድ ጠራጊዎችን በመጠቀም የቆሻሻ አወጋገድ አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
 
ሪፖርተር
 ታሪኩ እንዳለ
 0913-27-85-75
21/11/2001
 
ዜና ቂርቆስ
የለውጥ አመራርና የአሰልጣኞች ስልጠና 2ኛ ዙር ተጀመረ
የቂርቆስ ክ/ከተማ በአቅም ግንባታ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በየደረጃው ላሉ ቁጥራቸው 100 ለሚሆኑ አመራሮች ለ6 ቀን የሚቆይ ሁለተኛው ዙር የለውጥ አመራርና የአሰልጣኞች ስልየና በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ተጀመረ፡፡
 
የኮሌጁ ረዳት ፕሮፌሰር መስፍን ለማ እንደተናገሩት ስልጠናው እየተሰጠ ያለው በሁለት ዙር ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ከሐምሌ 13/11/2001 እስከ 17/11/2001 ለአንድ መቶ አመራሮች መሰጠቱን አስታውሰው በሁለተኛ ዙርም ቁጥራቸው ተመሳሳይ ለሆኑ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ እንደ ረዳት ፕሮፌሰር መስፍን ለማ የስልጠናው ዋና ዓላማ ሀገራችን በጀመረችው የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚያስተባብሩት በየደረጃው ያሉ አመራሮች ስለሆኑ በበለውጡ ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉና ለውጡን እውነተኛ በማድረግ ሀገሪቷን ወደ ተሸለ ደረጃ የሚያደርሱ መሆናቸውን ለማብሰርና ለማነሳሳት ጭምር ተብሎ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ከስልጠናው በኋላ ሁሉም አመራር በለውጥ ጎዳና ላይ ገብቶ የነበረውን የአፈጻጸም ክፍተት በማስተካከል ብዙዎችን አሳታፊ በማድረግ ከሚጠበቀው በላይ መሥራት እንደሚችሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ ያላቸውን እንነት ገልጸዋል፡፡
 
በሀገራችን ለለውጥ መነሳሳትና ቁርጠኝነት ይታያሉ፡፡ ግን መነሳሳትና ቁርጠኝነት ብቻ ብዙ ሊያራምደን አይችልም ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር መስፍን ለማ ዋናው ነገር አጋዥ አቅም በመፍጠር አመራሮች ውጤታማ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን በየጊዜው ቢመረመር በቃል ቁርጠኛ የሆኑበትን በተግባር ለማሳየት እንደዚህ ዓይነቱ ስልጠና አስፈላጊ ነው፡፡
 
ከሰልጣኞች መካከል የቀበሌ 11/12 የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ት ቤዛዊት አወቀ ስልጠናውን አስመልክቶ አስተያየት እንደሰጡት ስልጠናው ከመጀመሪያ ሁለት አሳታፊ የነበረና ከዚህ ስልጠና ያገኙትን ዕውቀት ወደ ሥራ ገበታቸው ሲመለሱ ወደ ተግባር ለመቀየርና ሌሎች ሠራተኞች ውስጥም ለማንጸባረቅ ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
 
የፍትህና ህግ ጉዳዮች ጽ/ቤት ደንብ ማስከበርና መቆጣጠር ወሳኝ የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ በእውቀቱ ገበየሁ በበኩላቸው የስልጠናው መክፈቻ ጥሩ እንደነበረ ገልጸው ይህ ስልጠና ለአመራሩ የአመራር ክህሎቱን በየጊዜው በማዳበር የተሰጠውን ሥራ በብቃት ማስኬድ ይረዳል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ በዕውቀቱ እንደተናገሩት ሁሉም ሰልጣኝ ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል በሥራ ማሳየት አለበት ብለዋል፡፡
 
20/11/2001
 
ዜና ቂርቆስ
በቂርቆስ ክፍለከተማና አፍሮ ዳን ኃላፊነቱን የተወሰነ ማህበር አዘገጅነት በነሐሴ መጨረሻ ለሚካሄደው የእግር ጉዞ 60 ቲ-ሸርቶችን ለመሸጥ ለየቀበሌዎቹ ስራ ማከፋፈል ተጀመረ፡፡
 
በክፍለከተማው መለስተኛ ስቴድዮምና በቀጣይም ወጣት ማዕከላትን ለመገንባት የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አንዱ የእግር ጎዞ ማድረግ ነው ያሉት የክፍለከተማው የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ሎሬንሶ ለእግ ጉዞው የሚያስፈልገውን ቲ-ሸርቶች በመሸጥ በሚገኘው ገቢ ስቴድዮሙን በመገንባት በከተማው ብሎም በክፍለከተማው የሚታየውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ እጥረት በእጅጉ ሊቀንሰው ይችላል ብሏል፡፡
 
ኃላፊው በንግግራቸው እንዳመለከቱት ክፍለከተማዋ የአዲስ አበባ ማእከል እንደመሆንዋ ያላትን ገጽታ በመቀየር ረገድ ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ የባለሀብቱንም ሆነ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡
 
ለእያንዳንዱ ቀበሌ በጠቅላላው 5000 ተ-ሸርቶችን በመረከብ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሸጠው ያሰረክባሉ ተብሎ እንደሚገመት የገለጹት ኃላፊው መለስተኛውን ስቴዲዮም ለመገንባት 5 የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት መካከል ቲ-ሸርቶቹን መሸጥና በሚገኘው ገቢ የስፖርት ማዘውተሪያውን እውን ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
 
ቲ-ሸርቶቹን የተረከቡት የቀበሌ 01/19 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለሙ አሰፋና የቀበሌ 10 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት ቀኖ በበኩላቸው ሊገነባ የታሰበው ስቴዲዮም በክፍለ ከተማዋ የሚገኙትን በርካታ ወጣቶች በአልባሌ ስፍራዎች እንዳይውሉ ከማድረጉም ባሻገር የስፖርት ማዘውተርያ እጥረት እንደሚያቃልል ጠቁሟል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚዎቹ ከሌሎች ባለሀብቶችና የባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተረከባቸውን ተ-ሸርቶች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ሸጦ ለማስረከብ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
 
17/11/2001 ዓ.ም.
ዜና ቂርቆስ
 
የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
 
 
የቂርቆስ ክፍለከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2001 የበጀት ዓመት ከ660 ሚሊዮን 18ሺ 700 ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
 
በክፍለከተማው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዘንጊያ  ካሳ እንዳብራሩት በጽ/ቤቱ ከሚከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል የገቢ ግብር አሰባሰብ ነው፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ ሊሰበሰብ ከታቀደው 694 ሚሊዮን 320 ሺ ብር 660 ሚሊዮን 18 ሺ 700 ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 95 በመቶ ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡
 
በከፍተኛ ደረጃ ገቢ ይሰበሰባል ተብሎ እሚገመተው ከክፍለከተማ ገቢዎች መምሪያና ከቀበሌዎች መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው በዚህም 315 ሚሊዮን 195 ሺ 517 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 427 ሚሊዮን 827 ሺ 700 ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 135 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስገንዝበዋል፡፡
 
እንደ ኃላፊው ገለጻ በዋና ስራ አስፈጻሚ የሚመራ የገቢ ዳሳሽ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሁሉም የሚመለከታቸው የገቢ ግብር የሚሰበስቡ መ/ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ለሚፈጠሩ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ ተወስዷል ብለዋል፡፡
 
የገቢ አሰባሰቡን በተፈለገው ደረጃ ለማስኬድ ከቀበሌዎች ጋርና በከፍተኛ ደረጃ ግብር ከሚሰበስቡ የክፍለከተማው 4 ጽ/ቤቶች ጋር በጊ አሰባሰቡ ዙሪያ ግምገማ እንደሚያካሂድ ነው የገለጹት፡፡
 
የግብር ከፋዩን ግንዛቤ ለመጨመር ቅስቀሳ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ኃለፊው በተደረገው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በተጨማሪ እሴት ታክስ 600 ግብር ከፋዮችን ለማስመዝገብ ታቅዶ ከ420 በላይ ግብር ከፋዮች መመዝገባቸውን አስረድተዋል፡፡
 
ቀድሞ ለአንድ ጉዳይ በ4ና ከዘያ በላይ ቢሮዎች ጋር መመላለስ ይጠይቅ እንደነበረ አስታውሰው በጽ/ቤቱ በመተግበር ላይ ያለውን የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥን ተከትሎ ጉዳያቸውን በአንድ ቦታ በመጨረስ ተገልጋዮች እንዳይንገላቱ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
 
በ2002 የበጀት ዓመትም ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀው ለገቢ አሰባሰብ መጠናከር የግብር ከፋዩንም ሆነ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ርብርብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
 
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያ ጽ/ቤት
 
ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ
  16/11/2001
 
ዜና ቂርቆስ
      
በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበሌ 11/12 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአሻራ የተደገፈ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት በመጀመሩ በመገባደድ ላይ ባለው የበጀት ዓመት የግብር አሰባሰብ ሥራ ከታቀደው 80 በመቶ የሚሆነውን ማከናወን እንደቻለ የጽ/ቤቱ የግብርና ታክስ አሰባሰብ ኦፊሰር አቶ አምባቸው ዓለሙ አስታወቁ፡፡
አንዳንድ የቀበሌው ተገልጋዮች ከዚህ በፊት የነበረውን አገልግሎት ከአሁኑ ጋር ሲያነጻጽሩት ቀደም ሲል መመላለስና ብዙ መጉላላት የነበረ ሲሆን አሁን ግን መንግስት በዘረጋው የለውጥ መስመር ቀናት የሚፈጁት በደቂቃ ተስተናግደን ወደ የግል ሥራችን መመለስ ችለናል ብለዋል፡፡
 
እንደዚሁም በአሻራ የተደገፈ የግብር አከፋፈል የሚለይበት ዘመናዊና የመለያ ቁጥር ድግግሞሽን ማስቀረት የሚችል በፎቶግራፍ፣ በጣት አሻራ እንዲሁም ስምን ከነአያት መመዝገብ የሚችል አዲስና ቀልጣፋ አሰራር እንደሆነ ከኮፒከት መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት የመጡት የአሻራ ባለሙያዎች ቡድን መሪ አቶ ሶሪ ዳድ ገልጸዋል፡፡
 
በተጨማሪም አሻራ ለመስጠት የመጡት ነጋዴዎችና የመንግስት ሠራተኞች በበኩላቸው ግብር ከአሁን በፊትም እንከፍላለን ይህን የተለየ የሚያደርገው ግን ሙሉ መረጃን በዘመናዊ መልክ መመዝገብ የሚችል እንደሆነ ገልጸው ነው፡፡ ግብር መክፈል ለሀገር ልማት ግንባታ እስከሆነ ጊዜ ድረስ የሚደገፍና ጥሩ አካሄድ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
 
በሌላ መልኩ አንዳንድ ግለሰቦች በዚህ በአሻራ መነሳት ዙሪያ የተሳሳተ ግንዛቤ ያላቸው በመሆኑ በሥራችን ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ ስለሆነ መገናኛ ብዙሀንና የሚመለከታቸው የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ይገባቸዋል በማለት ባለሙያዎቹ አሳስበዋል፡፡
 
በመጨረሻም የቀበሌ 11/12 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስዩም ሽመልስ ወደ ሙሉ ትግበራው ከመግባታችን በፊት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ጽ/ቤቶች የተለያዩ ችግሮች እንደነበሩና አሁን ግን ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሄ በመፈለግ በሁሉም ጽ/ቤቶች የተሻለና ቀለቀጣፋ አገልግሎት ለተገልጋዮች መስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡
 
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  
  ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
መምረጥ የዜግነት መብት ነው!
 
Facebook 'Like' Button  
 
 
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free