የጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና የሥራ ሂደት
ሀ. ራዕይ
የአዲስ አበባ ከተማ በንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ባለጸጋ የአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ሆና ማየት ነው፡
ለ. ተልእኮ
በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የዘርፉ አንቀሳቃሳችና አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡትን ለማስፋፋት ለማጠናከርና ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ እንዲቻል የሚመለከታቸውን አጋርና ተባባሪ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበርና በማቀናጀት ቴክኒካዊና ሙያዊ ድጋፍ በመስ-ት ዘርፉን ለስራ አጥነትና ድህነት ቅነሳ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር ማስቻል ነው፡፡
ሐ. ዓላማ
በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ እያደገ የመጣውን የተገልጋዩን ህብረተሰብ ፍላጐት ለማርካት አሁን ያለውን የአሠራር ሂደት በመቃኘት አዲስ የስራ ሂደት መቅረ}ና የስራ ሂደቱን አደረጃጀት መወሰን ነው፡፡ በተጨማሪም አዲሱን የስራ ሂደት ተግባራዊ ለማድረግ የአፈጻጸም ማንዋል/Operational Manual/ እና የቡድን ቻርተር/Team charter/ ማዘጋጀት ነው፡፡
ሀ. ደንበኞች
· በቴክኒክና ሙያ ት/ቤቶች በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ወጣቶች
ሴቶች
· የተለያዩ ሙያዎች ያሏቸውና በስራ ላይ ያሉ አንቀሳቃሾች
· በስራው ለመሰማራት ፍቃደኛ የሆኑ አካል ጉዳተኞችና ሌሎች ስራ ፈላጊዎች ናቸው፡፡
ለ. አጋር አካላት
· የአነስተኛ ብድር አቅራቢ ተቋማት
· የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ
· ጤና ቢሮ
· የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ
· ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት
· ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
· የፌደራል ጥ/አ/ን/ሥ/ል ኤጀንሲ
· መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (ILO, UNIDO,GTZ)
· ምርታማነት ማሻሻያ ማዕከል /Productivity improvement center/