የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  
  HOME
  ቂርቆስ ዜናዎች
  አጫጭር ዜናዎች
  kirkos
  በክፍለ ከተማው የሚሰጡ አገልግሎቶች
  ዜና
  About Kirkos InformationOffice
  ቀበሌዎች
  ዜናዎቻችን
  ቂርቆስ ዜና
ቂርቆስ ዜናዎች
የቂርቆስ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

 
17/09/03
አስተማማኝ የሆነ የአካባቢ ደህንነትን በመፍጠር ዘላቂ የሆነ ልማትን ማምጣት
ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ተጠየቀ፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ አስተማማኝ የሆነ የአካባቢ ደህንነትን በመፍጠር ዘላቂ የሆነ ልማትን ማምጣት ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ተጠይቋል፡፡
በክ/ከተማው ለሚገኙ የተለያዩ የንግድ፣ የሀይማኖት፣የኢንዱስትሪ፣ ጋራዥና ት/ቤቶች ለተውጣጡ ብዛታቸው 300 ለሚደርስ አካላት በተፈጥሮ ሀብትና አረንጓዴ ቦታዎች ያሉባቸው ችግሮች፣ በአካባቢ ብክለትና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ህጎችና ደንቦች ምን እንደሚመስሉና በመፍትሄዎቻቸው ዙሪያ መወያየታቸውን ለማየት ተችሏል፡፡
የክ/ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጊዜያዊ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ደሞዝ እንዳሉት የተለያ የንግድ ተቋማት ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው በዋነኛነት ለማሳወቅ ነው፡፡ ነባሮቹም ፕሮጀክቶች የአካባቢ ጥበቃ ኦዲት እንዲያቀርቡ ለማስቻልና ለሁሉም አካላት ይህን ግንዛቤ በመፍጠር ቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲቻል የተፈጠረ መድረክ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በቀጣይ ሰኔ ወር እንደመሆኑ መጠን ለአካባቢ ውበትም ጥበቃ በጎ ተፅዕኖ የሚኖራቸው አገር በቀል ዕፅዋትን በመትከል ህብረተሰቡም የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ያገኘናቸው መ/ር ጌዲዮን ሽፈራው እንዳሉት አሁን ባለው ስርዓተ ት/ት ውስጥ የአካባቢ ጥበቃን ያካተተ ሲሆን በት/ ቤቶች ብዙ መስራት እንደሚቻል ተማሪውን አሳታፊ በሆነ መልኩ ማንቀሳቀስ ከተቻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለዋል፡፡ አክለውም አሁን አሁን በከተማዋ እየጎላ የታየውን የድምጽ ብክለት ከወዲሁ መግታት ካልተቻለ ስር የሰደደ የማህበረሰብ ችግር ሊሆን ስለሚችል ሁሉም አካል ለመፍትሄው ቢሰራ ጥሩ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ተሳታፊዎቹ በችግሮቹ ዙሪያ የመፈውትሄ ሃሳባቸውን ማቅረብ ችለዋል፡፡
ሪፖርተር
ግርማ ዓለማየሁ
የቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
23/04/2003
 
በመስቀል አደባባይ የፎቶ ኤግዚቪሽን ተከፈተ፡፡
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ የአዳራሽ ፎቶ ኤግዚቪሽን በመስቀል አደባባይ ተከፈተ፡፡
በአዳራሽ ፎቶ ኤግዚቪሽኑ ስነ ስርዓት ላይ ለተገኙ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ኮሙኒኬሽነን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማይ ብርሃነ የፎቶግራፍ ኤግዚቪሽኑ ዓላማ ህዝቡ በራሱ ተሳትፎ የሚካሄደውን የልማት እንቅስቃሴ ውጤት እንዲመለከት፣ በሌላ በኩል አጠቃላይ የአስተዳደሩን የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎችን በውል ተገንዝቦ ካስተዳደሩ ጎን በመቆም የበለጠ ልማቱ እንዲቀጣጠል የበኩሉን እንዲወጣና ለተሻለ ተሳትፎ እንዲነሳሳ ለማነቃቃት ጭምርም እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
 አቶ ግርማይ አክለውም የፎቶግራፍ ኤግዚቪሽኑ ከገና በዓል ጋር ተያይዞ በኤግዚቪሽን ማዕከል የንግድና ባዛር ኤግዚቪሽን እየተካሄደ ባለበት ወቅት የተከፈተ በመሆኑ ጎብኚው የክፍለከተማው ነዋሪ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ወጪ ያለውም በርካታ የከተማችን ነዋሪም የጎበኘዋል ተብሎ ይጠበቃል ካሉ በኋላ በዝግጅቱ ተሳትፎ ያደረጉትን አካላትና ድርጅቶች አመስግነዋል፡፡
በአዳራሽ ፎቶ ኤግዚቪሽኑ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ሎዳሞ በበኩላቸው፡-
ኤግዚቪሽኑ የክ/ከተማውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አጉልቶ ያወጣ በመሆኑ ከሺ ቃላት አንድ ፎቶ እንዲሉ ነውና በአስተዳደሩ ምን እንደተሰራና እየተሰራ
እንዳለ ለህብረተሰቡ ትልቅ ግንዛቤ ያስጨብጣል፡፡ ከዚህ ባሻገር ህዝቡ ከመንግስትና ከአስተዳደሩ ጋር ያለውን ቁርኝት የበለጠ ያጠብቃል፡፡
ስለሆነም ሊበረታታ ይገባል፡፡ 
 
በተለይም ለአዳራሽ ፎቶ ኤግዚቪሽኑ የተመረጠው ጊዜና ቦታ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ህዝብ እንዲመለከተው የሚያስችል በመሆኑ በዚህ በኩል የክ/ከተማው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አርቆ አስተውሏል ማለት ይቻላል፡፡
እንዲህ ዓይነት ፎቶ ኤግዚቪሽን ሁሉም ክ/ከተሞች ተቀናጅተው ቢያካሂዱት ደግሞ የበለጠ ጥሩ ይሆናል የሚል አመለካከት አለኝ ብለዋል፡፡
ሪፖርተር
መኮንን ነጋሽ
                            22/04/2003
ለምክር ቤት አባላት በክትትልና ድጋፍ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
 
የቂርቆስ ክ/ከተማ አፈጉባኤ ጽ/ቤት ከክ/ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለክ/ከተማው ም/ቤት አባላት በክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡
ስልጠናው ስለሚኖረው ፋይዳ የም/ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሀዱሽ ኃይሌ ሲገልፁ ፡-
የም/ቤት አባላት የህዝብ ሉዓላዊነት ዋና መገለጫዎች መድረኮች ናቸው፡፡ በዚህም ምክር ቤቶች የወከሉትን ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍላጎቶች ማንፀባረቅ አለባቸው፡፡ ይህን ኃላፊነት ለመወጣት ደግሞ በየሴክተሩ ያሉ ዕቅዶችን መፈተሸ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደ አስፈላጊነቱም ድጋፍ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህን ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ደግሞ አቅምን ማጎልበት አንዱ መሰረታዊጉዳይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በም/ቤቱ ሁለት አደረጃጀቶች ኦሉ፡፡ የቡድንና የኮሚቴ አደረጃጀት፡፡
እስከያዝነው ሁለተኛ ሩብ ዓመት የፍትህ፣ ሰላም ፀጥታና መልካም አስተዳደር ኮሚቴ፣ የጤና ኮሚቴ፣ የዲዛይን ግንባታና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ኮሚቴ፣ የባህልና ቱሪዝም እና የኮሙኒኬሽን ኮሚቴ አርአያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል፡፡
የእነዚህን ኮሚቴዎች ተግባር በተሞክሮነት ወስዶ ሁሉም የም/ቤት አደረጃጀትና ኮሚቴዎች በተወከሉባቸው ዙሪያ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለተያያዝነው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬት የድርሻቸውን እንዲወጡ አቅም ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡
የክ/ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምላኩ ተበጀ በበኩላቸው፡
 
 
 
 
 
 
ስልጠናው የም/ቤት አባላት በሂደት በሚኖራቸው ሚና ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀው የም/ቤት አባላት የወከሉት የህብረተሰብ ክፍል አለ፡፡ ይህን የወከሉትን ህብረተሰብ የማገልገል ኃላፊነት ደግሞ አለባቸው፡፡ ከዚህ አኳያ ምክር ቤቱ በራሱ አሰራር ቡድኖችና ኮሚቴዎችን አደራጅቷል፡፡
እነዚህ ቡድኖችና ኮሚቴዎች የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንዲያመጡ አቅጣጫ ማሳየትና ክትትልና ድጋፍ እንዴት ማድረግ ይችላሉ ?   ምን ምን ላይ ማተኮር አለባቸው ? በሚሉ ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ለማስያዝ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡ በዚህም ክትትልና ድጋፍ ማለት ምን ማለት ነው እንዴት መከታተል ይቻላል? ስንከታተል የትኞቹን መርሆዎች መከተል አለብን በሚሉትና በሌሎችም ርዕሶቹ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓልብለዋል፡፡
ሪፖርተር
መኮንን ነጋሽ
ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም

የመምህራን ስልጠና

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ለሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በስራ አመራር፤በተከታታይ ምዘና፤ በአክሽን ሪሰርች እንዲሁም ቢኤስሲና ቢፒር አተገባበር ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃ/ስላሴ ፍሰሀ እንደተናገሩ የሀገራችን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ትምህርትን ቁልፍ የሆነውን ሚናውን መጫወት ሲችል ነው፡፡

ይህ ሊሆን የሚችለውም መምህራን ዘመኑ የሚጠይቀውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ትውልድ ተረካቢ ዜጋን ማፍራት ሲችሉ መሆኑን የገለፁ ኃላፊው ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ተግባር ላይ ሊያውሉት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነ ማሪም አረጋዊ በበኩላቸው የስልጠናው ተሳታፊ መምህራን በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ በማድረግ የተማሪዎቻቸውን ብቃት ሊጎለብቱት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊ መምህራን ስለስልጠናው በሰጡት አስተያየት ደግሞ ስልጠናው የመምህሩንና ተማሪዎችን ብቃት የሚፈትሽና ለውጤት የሚያበቃና የመምህሩን የአመራር ሰጪነት ብቃትም የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

 ጥቅምት 16 ቀን 2003 ዓ.ም

 የንባብ ባህላችንን ማሳደግ እንዳለብን ተጠቆመ

  በቂርቆስ ክ/ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ልማታዊ ባህልን የማበልፀግ ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪነት በንባብ ባህላችን ዙሪያ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በባህል ጥናትና ምርምር ኬዝቲም የተጠና የጥናት ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት፡፡

የጥናቱ አቅራቢ ወ/ሮ ፈለሰወርቅ አስራት እንዳሉት በየጊዜው ከሚመጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር እራሳችንን አስታርቀን ለማስጓዝና በቂ ግንዛቤ ለማግኘት ይቻል ዘንድ የንባብ ባህላችን ማሳደግ እንዳለብን፡፡

ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ በአብዛኛው የላይብረሪ ተጠቃሚዎች ተማሪዎች እንደሆኑና ይህም ቁጥራቸው በፈተና ሰሞኖች ከፍ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ እንደሚል ነው፡፡ የሴቶች ተሳትፎን በተመለከተ ደግሞ ጥናቱ እንደሚያሳየው በአብዛኛው የንባብ ባህላቸው ዝቅተኛ እንደሆነና ለዚህም ምክንያት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል በአብዛኛው ከት/ቤት መልስ ሴቶች የሥራ ጫና ስለሚበዛባቸውና እንደልብ ላይብረሪ የመጠቀም ፈቃድ ከቤተሰቦቻቸው ስለማያገኙ እንደሆነ ነው ጥናቱ ያስቀመጠው፡፡

የውይይቱ ተሳታፊና የወረዳ 11 የባህል ጥናት ፕሮሞሽን ላይብረሪ ክለርክ የሆኑት ወ/ሮ ሲቲ መሐመድ እንደተናገሩት በአብዛኛው ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ በተማሪዎች ረገድ የፈተና ሰሞንን ብቻ አማክሎ የማንበብ ልማድ እንዳለና ይህንንም ልማድ ለማስቀረትና በቀጣይ ወጥ የሆነ የንባብ ልማድ ለማዳበር ይቻል ዘንድ እንደነዚህ ያሉ ውይይቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የምክር ቤት አባላት እና የየወረዳዎች ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡

 ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ጥቅምት 15 2003 ዓ.ም

የሙያ ፈቃድና ሬጉላቶሪ ዋና የስራ ሂደት ስልጠና ሰጠ

 ሆቴሎች፤ሬስቶራንቶች፤ምግብ ቤቶችና ሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት አሰጣጥ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የሙያ ፈቃድና ሬጉላቶሪ ዋና የስራ ሂደት በስሩ ለሚገኙ ሆቴሎች፤ሬስቶንቶችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተወካዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ንፅህና ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

 ስልጠናውን የሰጡት ፍሌቨር ሼፍስ ግሩፕ አባላት ሲሆኑ ስልጠናው ያተኮረው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ የሚሰጡት ግልጋሎት ጥራቱን የጠበቀና ለተገልጋይ ምቹ እንዲሆን ለማስቻል ነው፡፡

 

በክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የሙያ ፈቃድ ሬጉላቶሪ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኃ/ማሪያም እንዳሻው የስራ ሂደቱ በየደረጃው ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሙያ ፈቃድ ከመስጠት ባሻገር አገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያሻሽሉ የማስተማርም ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

 ስልጠናው በሙያ ብቁ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተናግረዋል፡፡የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናው ቀጣይነት ቢኖረው መልካም ነው፤ስልጠናው የምንሰጠው አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ያስችላል፤የአገልገሎት ሰጪ ተቋማቱ ሲገነቡ የሚሰጡትን አገልግሎት መሰረት ባደረገ መልኩ ቢሆን የሚሉ ሀሳቦችን ተቅሰዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ጥቅምት 15 2003 ዓ.ም

የጥ/አ/ል/ኢ/ጽ/ቤት የ2003 የስትሪንግ ኮሚቴ ዕቅዱን አወያየ

  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት በ2003ዓ.ም የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የስትሪንግ ኮሚቴ ዕቅድ ዙሪያ ከክፍለተማው ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያየ፡፡

  እቅዱን ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ያቀረቡት በክፍለከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የስልጠናና ንግድ ልማት አገልግሎት ባለሙያ አቶ ዳንኤል ታዬ እንደተናገሩት ዕቅዱ የኢንዱስትሪ መሰረት የሆኑትን የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ወደ ተሻለ አቅጣጫ ለመምራት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

  በዚህም የስራ ዕድል በመፍጠር፤ልማታዊ ባለሀብቶችን በማበራከትና ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማረጋገጥ ያስችላል ነው ያሉት፡፡

  በእቅዱ የተለያዩ የስትሪንግ ኮሚቴዎችን በማስተባበር ከ16 ሺ ለሚበልጡ ነባርና አዲስ አንቀሳቃሾች የአመለካከትና የክህሎት ስልጠና ለመስጠት ታቅዷል እንደ አቶ ዳንኤል ገለፃ፡፡

በክፍለከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሻፊ በበኩላቸው የእቅድ ውይይቱ በዘርፉ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በመገምገምና ዘርፉን ወደተሻለ ደረጃ ለማብቃት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

አንቀሳቃሾችም ሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለዕቅዱ ስኬታማነትና ለኢንዱስትሪው እድገት መረጋገጥ ከክፍለከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ጽ/ቤት ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

                      ጥቅምት 10 ቀን 2003 ዓ.ም.

 

በኩፍኝ ክትባት ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

     በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዋና የሥራ ሂደት በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጠ፡፡

      ስልጠናውን የሰጡት በጤና ጽ/ቤት የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ እንድሪያስ አልጋነህ እንደተናገሩት ሥልጠናው የተዘጋጀው በኩፍኝ፣ በልጅነት ልምሻ ፣ ቫይታሚን ክትባቶችና የአንጀት ትላትል መድኃኒት ለህፃናት ለመስጠት እንዲያስችል ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ ነው፡፡

      እንደ አቶ እንድርያስ ገለፃ የኩፍኝ ክትባቱን የሚወሰዱት እድሜያቸው እስከ አራት ዓመት የደረሱ ህፃናት ሲሆኑ በሽታው በህፃናት ላይ ከሚያደርሰው በሽታ ለመከላከል የሚያስችለውን ግንዛቤ በመውሰድ ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በመሆን እንዲያስተምሩ ያስችላል ብለዋል፡፡

      የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ደግሞ የጤና ተቋማቱ የሚመጡ በርካታ እናቶችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን በማስከተብ በሽታው ህፃናቱን እንዳያጠቃ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

       ሰልጣኞች ህብረተሰቡ ለህፃናት ልጆቹ የኩፍኝ ክትባቱን እንዲያገኙ በማድረግ አንድም ህፃን ሳይከተብ እንዳይቀር የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ከመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

 ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ብሩክ ሎቤ

 ጥቅምት 10/2003

በሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ላይ ስልጠና ተሰጠ
  በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች በመንግሥት ሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ላይ በቂ ግንዛቤ በማስጨበጥ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ማስቻል እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
  በቂርቆስ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የአቅም ግንባታ ጽ/ቤትና የሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደቶች ለክ/ከተማው አመራሮች ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው የተሰጠው ለክ/ከተማው የካቢኔ አባላትና የሥራ ሂደት አስተባባሪዎች ሲሆን ስለሰው ኃይል ዕቅድ ክፍት የሥራ መደቦችን በሠራተኞች ስለማስያዝና በመንግስት ሠራተኝነት በመቀጠር ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡

 የክ/ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ባለፈው ዓመት መጨረሻና በተያዘው ዓመት መጀመሪያ ላይ ሰራተኞች ከግንዛቤ ማነስ የተነሳ ሥነ - ምግባር ጉድለት ተከስቶባቸዋል፡፡ በሰራተኛ መተዳደሪያ ደንብ አዋጅ ቁጥር 6/2002 የተዘጋጀው ስልጠናም የሠራተኞቹን የግንዛቤ ችግር ይቀርፋል ብለዋል፡፡

 በዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ያሬድ ለገሰ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላት በሠራተኞ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ግልፅ ግንዛቤ ኖሯቸው ሠራተኞቻቸውን በአግባቡ እንዲመሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

 በአዲስ አበባ አስተዳደር ወጥቶ ያፀደቀው የሰራተኛ መተዳደሪያ ደንብ አዋጅ ቁጥር 6/2002 ን ለሰራተኛው ጋር በማስዋወቅ የሙከራ ቅጥር የውስጥ ዝውውር የደሞዝ መቋረጥንና የዓመት ፍቃድን በተመለከተም ሰልጣኞቹ በቂ ግንዛቤ ይኖራቸዋል ያሉት ደግሞ በክ/ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተገኝ ተመቻች ናቸው፡፡

ሪፖርተር

ታሪኩ እንዳለ

  09/02/2003

 የጤና ኤክስቴንሽን ሞዴሎች ተመረቁ

ጤና ኤክስቴንሽን በሞዴልነት የተመረጡ አባወራዎች የቤተሰቦቻቸውንና የራሳቸውን ጤና በመጠበቅ የጤና ኤክስቴንሽነ  ፕሮግራምን ስኬታማ ለማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 6 ጤና ጽ/ቤት ለ4 ወራት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ዙሪያ ያሰለጠናቸውን ከ245 በላይ ሞዴሎችን አስመረቀ፡፡

 በገነት ሆቴል አዳራሽ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የወረዳው ጤና ጽቤት ኃላፊ አቶ መትከል ገ/መድህን እንደተናገሩት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ሞዴል የተባሉት ቤተሰቦች የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ጤና በመጠበቅ ፕሮግራም ስኬታማ ለማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡

 በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጥበቃ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር ዶ/ር ንግስቲ ተስፋዬ በበኩላቸው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በገጠር ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡ በገጠር የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋፋትም ፕሮግራሙን በከተማ  ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል፡፡

 የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተጠባባቂ ኃላፊ ወ/ሮ ፋንቱ ፀጋዬም በከተማችን ብሎም በአገራችን ከሚከሰቱ የበሽታ ዓይነቶች ከ60 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት በመከላከል ማስወገድ የሚችሉ ናቸው፡፡  በሽታዎቹን ለመከላከልም ከተለያዩ ኮሌጆች በነርስነት ሙያ የሰለጠኑና በተለያዩ ተቋማት በነርስነት ሲያገለግሉ የነበሩ ባለሙያዎችን ለተጨማሪ ሶስት ወራት በማሰልጠን ፕሮግራሙን እንዲተገብሩ ተደርጓል፡፡ በጤናው ሴክተር የሚስተዋለውን የግንዛቤ ችግር በመቅረፍም ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል ብለዋል ወ/ሮ ፋንቱ፡፡

 ከተመራቂ ሞዴሎች አንዳንዶቹ እንደተናገሩት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ ያገኙት ስልጠና ብዙ ግንዛቤ ፈጥሮላቸዋል፡፡ ወደፊትም ከቤታቸው እስከ ጎረቤታቸው የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር

ታሪኩ እንዳለ

                            ጥቅምት 04 2003 ዓ.ም

ቅርሶች አስፈላጊው ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተጠቆመ

በሀገራችን የሚገኙ ቅርሶች አስፈላጊው ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት በክፍለከተማው የሚገኙ ቅርሶችን በቅርስነት ማስመዝገብ ስለሚኖረው ጠቀሜታ በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ባህልና ቱሪዝም ሰራተኞችና የተለያዩ የቅርስ አስተዳዳሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የቂርቆስ ክፍለከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ገብሩ አስካል እንደተናገሩት በተለያዩ አጋጣሚች የሚመዘገቡ ቅርሶች የቀደምት ታሪክን ለመጪው ትውልድ ለማስተማርና የህዝቦችን የባህል ትስስር ለማጠናከር የላቀ አስተዋፅኦ አለው፡፡

የቱሪዝም ሀብት ለሀገር የምጣኔ ሀብታዊ እድገት የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት የስራሂደት አስተባባሪው ቅርሶች የጋራ ሀብቶች መሆናቸውን ማስተማርና ከሚጎበኘው የቱሪዝም ሀብት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

 በየአካባቢው የሚገኙ ቅርሶችን በቅርስነት በማስመዝገብና አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያገኙ ማስቻል የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ድርሻ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ኃላፊነት እንደሆነ ነው አቶ ገብሩ ያስገለዘቡት፡፡

 ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

0913049933

 ጥቅምት 02 2002 ዓ.ም

 

የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አበረታች ውጤት አሳየ ተባለ

 በከተማ የተጀመረው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ተጨባጭ ለውጦችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
  የቂርቆስ ክ/ከተማ የካቢኔ አባላት በጤና ኤክስቴንሽን የሰለጠኑ ሞዴል አባወራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም ሞዴል የተባሉት ቤተሰቦች ከጤና ኤክስቴንሽን ትግበራ አንፃር አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገልፃDል፡፡
 ከጉብኝቱ በኋላ የክ/ከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ጥበቡ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዲመለከቱት በክ/ከተማው በሚገኘ አስራ አንዱም ወረዳዎች ሞዴል አባወራዎች ተለይተው ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሰልጣኞቹ ባገኙት ስልጠና መሠረትም ከቤታቸው አያያዝ ጀምሮ አካባቢያቸውን ንፅህና በመጠበቅ የበሽታ መከላከሉን ተግባር አጠናክረው ይዘውታል፡፡
   በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በሽታ መከላከል ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ተሾመ በበኩላቸው በከተማ ደረጃ የተያዘው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ውጤታማ እየሆነ ይገኛል፡፡ በጉብኝቱ የተመለከቷቸው ሞዴል ቤተሰቦችም የዚህ ማሳያ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
 የጤና ኤክስቴንሽን ሞዴል ቤተሰቦች በበኩላቸው ፕሮግራሙን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመሩ ወዲህም በጤናቸውና በቤተሰቦቻቸው ጤና ላይ መሻሻልን እያሳየ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
  ሞዴል ቤተሰቦቹ የቆሻሻ ውኃ ማስረጊያ ጉድጓድ በመቆፈርና ከመፀዳጃ ቤት መልስ የእጅ መታጠቢያ በማዘጋጀትና የቤትና የአካባቢ ንፅህና በመጠበቅ አበረታች ተግባር እየፈፀሙ እንደሚገኙ ከጉብኝቱ ለመመልከት ተችሏል፡፡  
ሪፖርተር

ታሪኩ እንዳለ 0913278575

መስከረም 29/2003

በቢኤስ ሲ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ቢ ፒ አርን ከውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት ቢ ኤስ ሲ ጋር አቀናጅቶ ተግባራዊ በማድረግ ቁልፍ የለውጥ ተግባራትን ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ተገለጸ፡፡

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 8 አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ለወረዳው አመራሮችና ሰራተኞች በውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት ቢ ኤስ ሲ ዙሪያ ለሁለት ቀናት የቆየ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ሲጀመር የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘርዓይ ካህሳይ እንደተናገሩት በመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ የተገኘውን ውጤት በውጤት ተኮር የምዘና ስርዓቱ በማስደገፍ በከተማ ደረጃ የተያዙትን ቁልፍ ተግባራት ማሳካት ይቻላል፡፡ እያንዳንዱ የተቋሙ ሰራተኛ የሚያመጣው ድምር ውጤትም ተቋሙን የሚለውጥ በመሆኑ ሁሉም ሰራተኛ በለውጥ መሳሪያዎች ዙሪያ ግልጽ ግንዛቤ ሊይዝ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የወረዳው ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ቱጂ በበኩላቸው በመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጡ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡ ውጤት ተኮር የመዘና ስርዓቱ ደግሞ ስራዎችን ቆጥሮ የሚሰጥና ቆጠጥሮ የሚረከብ በመሆኑ ስራዎችን በመመዘን ውጤትን መለካት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

አቶ ይልማ ካህሳይ የተባለው የስልጠናው ተሳታፊ የውጤት ተኮር የምዘና ስርዓትን በተመለከተ የተሰጠው ስልጠና ሰፊ ግንዛቤ እንደፈጠረለት ይናገራል፡፡ ፈጻሚዎች በሚያመጡት የአፈጻጸም ውጤት ተቋማቸውን ከመለወጥ ባለፈ ሰራተኞች ራሳቸውን እንደሚጠቅሙ መገንዘቡን ተናግሯል፡፡

ወ/ሮ ህይወት አለሙ በበኩላቸው በመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጡ የተገኘውን ውጤት በውጤት ተኮር የምዘና ስርዓቱ አስደግፎ ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻል መገንዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

   ሪፖርተር

ታሪኩ እንዳለ

0913278575

መስከረም 28 2003 ዓ.ም

የጥቃቅንና አነስተኛ

 በቂርቆስ ክፍለከተማ የወረዳ 10 ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የ2003ዓ.ም ዕቅዱን በስሩ ለሚገኙ አንቀሳቃሾች አስተዋወቀ፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ የራሳቸውን እቅድ ለማውጣት የሚያስችላቸውን ግንዛቤም አስጨብጧል፡፡

 ጽ/ቤቱ እቅዱን ለአንቀሳቃሾ ባስተዋወቀበት ወቅት እንደተገለፀው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርታማነታቸውን በ60 በመቶ እንዲያሳድጉ ማድረግ፤ለምርት ጥራት ተወዳዳሪነት ስልጠናዎችን መስጠት፤ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር የሚና ለ45 ኢንተርፕራይዞች የገቢያ ትስስር በመፍጠር 1.5 ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲጊኙ ማስቻል ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ውስጥ ሊያከናውናቸው ካቀዳቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

 አንቀሳቃሾች በበኩላቸው በአስተዳደሩ ሊሰሩ የታቀዱት ተግባራት ጥሩ ቢሆኑም ተጋነዋል፤ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ለማስተካከል ምን ታስቧል፤የክትትልና ድጋፍ ስርዓቱም ሊስተካከል ይገባል የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡

 የአስተዳደር አካላቱ በሰጡት ምላሽ ሞዴል አንቀሳቃሾችን በመለየትና ተሞክሯቸውን እንዲያስፋፉ በማድረግ ሌሎች እንዲማሩባቸው በማድረግ፤አንቀሳቃሾች የቁጠባ ባላቸውን እንያዳብሩ በማድረግና በገቢያ ተወዳዳሪ እንሆኑ ማድረግ ለ2003 የታቀደውን እቅድ ተፈፃሚ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡

 

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

0913049933

መስከረም 28 2003 ዓ.ም

ሙስናን ከምንጩ በማድረግ መልካም አስተዳደርና ልማት ማፋጠን እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በክፍለከተማው ለሚገኙ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች በሙስና ወንጀሎችና ተጠያቂነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የንቃተ ህግና ምክር መስጠት ንዑስ የሥራ ሂደት የህግ ምክር ኦፊሰር አቶ መኮንን ብርሀኑ እንደተናገሩት ስልጠናው የተዘጋጀው የሙስና ምንነትና ተፈፅሞ ከተገኘ ሊያስከትለው ስለሚችለው ህጋዊ ቅጣት  ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ ነው፡፡

በክፍለ ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት ንቃተ ህግና ምክር መስጠት ንዑስ የስራ ሂደት የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የሙስናን አስከፊ ገፅታ በማሳየት ወንጀሉ ከሚስከትለው አደጋ እንዲርቁ ለማስቻል ስልጠናዎችን ይሰጣል እንደ አቶ መኮንን ብርሀኑ ገለፃ፡፡

በስልጠናው የተሳተፉ የስራ ሂደት አስባባሪች ሙስናን በመከላከል ረገድና በስራቸው ለሚሰሩ ሰራተኞችም በማሳወቅ ሊከላከሉት ይገባል ነው ያሉት፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

0913049933

መስከረም 23/2003
የነጋዴ ፎረም ተመሰረተ
ህገወጥ ንግድን በመከላከል ዘመናዊ ንግድ ለማስፈንና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እንዲፈጠር ነጋዴዎች በህብረት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ነጋዴዎች የነጋዴዎች ፎረም መስረተዋል፡፡ ፎረሙ ሲመሰረት የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ሰይፈ እንደተናገሩት በአንዳንድ ነጋዴዎች ዘንድ እየተስተዋለ የሚገኘውን የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ያለአግባብ የመበልፀግ ፍላጎትን በመከላከል ዘመናዊ ንግድ ለማስፈን የነጋዴዎች ፎረም መመሰረት አስፈልጓል፡፡
ፎረሙ ከተመሠረተ በኋላም የህብረተሰቡን መሰረታዊ ፍላጎትን ተከትሎ አቅርቦትን በማስተካከል ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረትን በመከላከልና ጥራት ያለው ምርት ለተጠቃሚው በማቅረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የወረዳው ንግድና ኢንዱስት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወ/ሰንበት በበኩላቸው የነጋዴዎች ፎረም መመሰረቱ ለተጠቃሚው ህብረተሰቡና ለነጋዴው እንዲሁም ለመንግስት የሚሰጠው ጠቃሜታ የጎላ ነው፡፡
አንዳንድ የጉባኤው ተሳታፊዎች ባነሱት ጥያቄው ፎረሙ ተጠሪነቱ ለማን ነው? በቅርቡ የሚከታተለው አካል ማን ነው? የራሱ አድራሻ ይኖረዋል ወይ የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ዳንቾ ጥያቄውን ሲመልሱ እንደገለፁት ከከተማ እስከ ወረዳ የሚቋቋሙት የነጋዴዎች ፎረሞች በየደረጃው ለሚገኙ የንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ተጠሪ ይሆናሉ፡፡ ፎረሞቹን በቅርብ በመከታተል አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረጉ ሥራም ጽ/ቤቱና አስተዳደሩ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡
በወረዳ ደረጃ የተመሰረተውን የነጋዴዎች ፎረም እንዲመሩም አስራ ሶስት አባላትን ያቀፈ የአመራር ቡድን ተዋቅሯል፡፡    
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
መስከረም 23/2003
በከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
በቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ አመራሮች በከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በምስራቅ ጎህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ ስልጠናው ሲጀመር የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ካሰች ጥበቡ እንደተናገሩት የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በክ/ከተማው ከተጀመረ ወዲህ የተግባርና የንድፈ ኃሳብ ትምህርት የቀሰሙ አባወራዎች ለምርቃት ደርሰዋል፡፡ይሁንና በክ/ከተማው ውስጥ ባሉ አስራ አንድ ወረዳዎች እያንዳንዱ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ማስመረቅ የሚገባው ስድሳ ሞዴል አባወራ ቢሆንም አንዳንድ ወረዳዎች ከተቀመጠው አሃዝ እጅግ ዝቅተኛ ቁጥር ያለቸው ሞዴሎችን ያስመርቃሉ፡፡ለዚህም ነው በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በመወያት የነበሩ ክፍተቶችን አበጥሮ በማውጣት በቅንጅት ለመስራት ስልጠናው የተዘጋጀው፡፡
ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩት አቶ ዓለም ሰብስቤ የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ፐሮግራም ዓላማ ግብና አተገባበርን የሚመለከት ሰፊ ማባራሪያ ሰጠጥተዋል፡፡
በስልጠናው ከተሳተፉ አመራሮች አንዳንዶቹ በእስካሁን ክንዋኔ የነበረው ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራቱ ሁኔታ እንብዛም ያልተጠናከረ እንደነበር አመልክተው ስልጠናው የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት በኩል የተሸለ አቅም ለመፍጠር እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይም የክ/ከተማው ዋንስራ አስፈጻሚ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡የከተማ ጤና አክስቴንሽን ፕሮግራም በከተማ ደረጃ እንደቁልፍ ተግባረር ከተያዙት ዘርፎች አንዱ ነው ያሉት አቶ ቢያ ዜጎች ጤናቸው ተጠብቆ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ መንግስት ያስቀመጠው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም አመራሩ ሊረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
ሪፖርተር
መኮንን ነጋሽ
0913047596
መስከረም 22 2003ዓ.ም
በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
በ2002 በጀት ዓመት የነበሩ የአፈጻጸም ማነቆዎችን በመለየት በ2003 በጀት ዓመት የተሳካ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በየደረጃው የሚገኙ ፈጻ㔫ሚዎች የጋራ ግንዛቤ ሊይዙ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
 በቂርቆስ ክ/ከተማ የሚገኙ የወረዳና የክ/ከተማ የማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች ግምገማዊ ስልጠና ተጀምሯል፡፡
 ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የሰራዊት ግንባታ የፕላንና መረጃ አሰጣጥና የመሬት ልማት ዘርፎች የትኩረት አቅጣጫዎቹ ናቸው፡፡
 በሺመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውይይቱ ሲካሄድ እንደተገለጸው በከተማው በ2002 በጀት ዓመት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የነበሩ ማነቆዎችን በመለየት የጋራ አስተሳሰብ ይፈጠራል፡፡ የቀጣይ 2003 ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዕቅድም ለፈጻሚዎች ቀርቦ በውይይት ያዳብሩታል፡፡
 በክ/ከተማው በሚካሄደው የሁለት ቀናት ግምገማዊ ስልጠና በመጀመሪያና በሁለተኛ ዙር ስልጠናዎች ያልተሳተፉ የክ/ከተማ ፈጻሚዎችና የየወረዳዎቹ ግንባር ቀደም ሰራተኞች የተሳተፉበት ሲሆን በጥቅሉም አንድ መቶ አርባ ስድስት ያህል ፈጻሚዎች ስልጠናውን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል
በቀጣይነትም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በ4ኛ ዙር ስልጠና እንደሚሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
   ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
0913278575
መስከረም 16 2003 ዓ.ም㗹㗹
የቢስሲ ስልጠና
 በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ10 አቅም ግንባታ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ አመራሮች በሚዛናዊ የስራ አመራር ውቴት ምዘና ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
 ስልጠናው የተሰጠው በወረዳው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት አስተባባሪነትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ግንባታ ቢሮ በተጋበዙ አሰልጣኞች አማካኝነት ነው፡፡
 የወረዳው ም/ወና ስራ አስፈፃሚና የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀጎስ እንደገለፁ ስልጠናው የወረዳው ጽ/ቤት አመራሮች የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናን ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በቀላሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ያስችላል፡፡
 የውጤት ምዘና ስርዓቱ ቀድሞ የነበረውን የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ እንደሚያጠናክረው ገልፀው ሰራተኞች ተቆጥሮ የሚሰጣቸውን ተግባራት የመተግበር አቅማቸውን የሚመዝን አሰራር ነው ብለዋል፡፡
 ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ለሌሎች በማስተላለፍና በመተግበር ሀገሪቷ ለምትጠብቀው ለውጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
መስከረም 16 2003 ዓ.ም㗹㗹
የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር
 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በኦሮሚኛ ቋንቋ ለ3 ወራት ያለጠናቸውን 100 የቋንቋ ተማሪች በሰርተፊኬት አስመረቀ፡፡
 የምርቃት ስነስርዓቱ በሴንትራል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት የክፍለ ከተማው ተጠሪ አቶ ጀባ አዱኛ እንደተናገሩት የቋንቋንና ባህልን በማስፋፋትና በማሳደግ ረገድ የተለያዩ ቋንቋዎችን ማስተማር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
 የኦሮሚኛንም ሆነ ሌሎች የሀገራችን ቋንቋዎችና ባህልን በማስፋፋት ረገድ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ እንደሚያስፈልግ ነው የጠቆሙት፡፡
 የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ተወካይ አቶ አህመድ አብዱልሀሊም በበኩላቸው በሀገራችን ቋንቋን እንደልብ መናገር አስቸጋሪ እንደነበር አስታውሰው ቋንቋውን ወጣቶች ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ለማስተማር በመቻላቸው አድንቀዋል፡፡
 በእለቱ በብሔሩ ተወላጆች ግጥሞች የቀረቡ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪች የሰርተፊኬት ሽማት ተሰጥቷል፡፡
 ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
መስከረም 16 2003 ዓ.ም
የሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ለክፍለከተማ ጽ/ቤት ሃላፊዎች በሴቶች ልማትና ለፓኬጅን አስተዋወቀ
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ስርዓት ጾታን 㜎ማስረፅ ወሳኝ የስራ ሂደት ለክፍለከተማ ጽ/ቤት ሃላፊዎች በሴቶች 㜎ልማትና 㜎ለፓኬጅን አስተዋወቀ፡፡
የፓኬጁን ዝርዝር መግለጫ ያቀረቡት በክፍለ ከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ስርዓተ ፆታን የማስረፅ ወሳኝ የስራ ሂደት ባለቤት ወ/ሮ መሰረት አቡዬ                እንደገለፁት ፓኬጁ እያንዳንዱ ጽ/ቤት እቅድ ሲያወጣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ባማከለ መንገድ መሆን አለበት፡፡
 እንደ ወ/ሮ መሰረት ገለፃ የሴቶችን ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በኤች.አይ.ቪና በስነተዋልዶ በትምህርት፤በቤቶች ልማት ፕሮጅቸቶችና በተለያዩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 የውይይቱ ተሳታፊችም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ነው ያረጋገጡት፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
መስከረም 15 2002ዓ.ም
የእቅድ ውይይት ከወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተደረገ
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የየወራዳዎቹ አስተዳደር አካላት በ2003 ዕቅድና በ5 ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽ ዕቅድ ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡
በየወረዳዎቹ በቀረቡት የ2003 ዕቅድ ላይ እንደተገለፀው ሀገሪቷ ልታሳካ ያቀደችውን የ5ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ስኬታማነት በየወረዳዎቹ የሚታቀዱ ዕቅዶችን ተግባራዊ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡
በ2003 በጀት ዓመት አስተዳደሩ ሊያሳካቸው ከአቀዳቸው ቁልፍ ተግባሮች መካከል ትምህርት፤ጤና፤ጥቃቅንና አነስተኛና ሌሎች የለውጥ ተግባራት እንደሆኑ በውይይት መድረኮቹ የተገለፀ ሲሆን ለተግባራዊነቱ ደግሞ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ እንደሚጠይቅ ነው የተጠቆመው፡፡
ከነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት ደግሞ መንግስት በየደረጃው በሚያወጣቸው ዕቅዶች ላይ ህብረተሰቡን ማወያየቱ ሊጠናከር ይገባል፤አስተዳዳሩ በወረዳው የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከህብረተሰቡ ጋር ለመቅረፍ መንቀሳቀስ ይኖርበታል የሚሉና በየዘርፉ የሚታዩ የልማት ተግባራትን ህብረተሰቡን በማስተባበር ማሰራት አለበት የሚሉት ሀሳቦች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 የየወረዳዎቹ አስተዳደር አካላትም በመሬት፤ገቢና በሌሎች ዘርፎች ላይ የሚታዩ ኪራይሰብሳቢነት እንቅስቃሴዎችን ከነዋሪዎቹ ጋር በጋራ ሆኖ ለመቅረፍ እንደሚሰራ ነው ያረጋገጡት፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
  መስከረም 13 2002 ዓ.ም
ወረዳ 8 የአጎዛ ገቢያ ማህበር አባላት በመተዳደሪያ ደንብ ተወያዩ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የአጎዛ ገቢያ ማህበር አባላት የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ተወያይተው አፀደቁ፡፡
የአጎዛ ገቢያ ማህበር ከ300 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን የማህበሩ አባላት በጋራ ሆነው ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን በማሰባሰብ ለጋራ አላማ የሚንቀሳቀሱበት ነው፡፡
የመተዳደሪያ ደንቡ በቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው ማህበሩ አባላቱ ዘመናዊ የገንዘብ አያያዝ ስርዓት እንዲከተሉ ያስችላል፡፡ ቁጠባን ባህል ያደረገ የንግድ ስርዓት እንዲከተሉም እንዲሁ፡፡
በእለቱ መተዳደሪያ ደንቡ ላይ መሻሻል የሚገባቸውን ደንቦች በማሻሻልና ውይይት በማድረግ ያፀደቀ ሲሆን በገቢያ ስፍራዎች ላይ ለሚፈጠሩ የዝርፊያና የፀጥታ ችግሮች የፀጥታ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል፡፡
 ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
መስከረም 13 2002 ዓ.ም
የቱሪዝም ቀን በትምህርት ቤቶች ተከበረ
በቂርቆስ ክፍለከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዓለማአቀፍ የቱሪዝም ቀንን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበሩ፡፡
በተባበሩት መምህራን ት/ቤት በዓሉ ሲከበር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት የአለም ቱሪዝም ቀን የተለያዩ መፈክሮችን በማንገብ በዓለም ለ31ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡
የዘንድሮው በዓልም ቱሪዝምና ብዝሃ ህይወት በሚል መሪ መፈክር እየተከበረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በዓሉ በክፍለ ከተማው ደረጃ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 17 በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
 ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች በመሆናቸው ብዝሃ ህይወትን በመንከባከብ ቱሪዝምን እንዲያጎለብቱ በሀገርህን እወቅ እና በባህላዊ ዘርፎች ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ኃላፊው፡፡
በጠመንጃ ያዥ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዓሉ ሲከበር መምህርት ሰውነት ወጋሪ እንደገለፁት በዓሉን በትምህርት ቤቶች ማክበር ያስፈለገው ተማሪዎች የኃላፊነት ስሜት ተሰምቷቸው ብዝሃ ህይወትንና ቱሪዝምን እንዲያጎለብቱ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ ነው፡፡
በበዓሉ ላይ የተሳተፉ አንዳንድ ተማሪዎች በበኩላቸው ተማሪዎች ከስር ግንዛቤ ይዘው ማደጋቸው በአካባቢ ጥበቃና በብዝሃ ህይወት እንክብካቤ የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜናም በቂርቆስ ክፍለከተማ የወረዳ 10 ጽ/ቤት ሰራተኞች የዓለም የቱሪዝም ቀንና የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አክብረዋል፡፡
በዓሉ በትምህርት ቤቶቹና በወረዳው ሲከበር በበዓሉ መሪ መፈክር መሰረት የችግኝ ተከላና እንክብካቤ የተካሄደ ሲሆን የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽንም ለእይታ ቀርቧል፡፡

21/04/2003

የተማሪዎች ፓርላማ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በሚገኘው የትንሳኤ ብርሀን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ፓርላማ ምርጫ ተካሄደ፡፡
 የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አሰፋ ብርሀኑ እንደተናገሩት ይህ የተማሪዎች ምርጫ ለሁለት ሳምንታት ያህል በ5ኛና በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ቅስቀሳ እያካሄዱ የቆዩ ሲሆን ዋና አላማውም ተማሪዎች በስነ-ዜጋና ስነምግባር ትምህርታቸው ታግዘው ዴሞክራሲያዊ ባህል እንያዳብሩ እና በትምህርት ሰዓት ያላቸውን ስለምግባር አስተካክለው ለማህበረሰቡ አርአያ እንዲሆኑ የተዘጋጀ ነው፡፡
 የምርጫው ተወዳዳሪ የሆነችው ተማሪ ቃልኪዳን ወርቁ እንደገለፀችው ደግሞ በስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር አስተባባሪነት መዘጋጀቱ በትምህርት ቤቱ ቆይታችን በጥሩ ስነ-ምግባር ታንፀን ለሌሎች ትምህርት ቤቶች ምሳሌ እንሆናለን ስትል ተናግራለች፡፡
 ሌላዋ የትምህርት ቤቱ የምርጫ አስተባባሪ የነበረችው አለማሽ ኪዳነ በበኩሏ ይህ አይነቱ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በትምህርት ቤቱ የተካሄደ ሲሆን ምርጫ መዘጋጀቱ ለትምህርታችንም ሆነ ለወደፊት ሕይወታችን ጠቃሚ በመሆኑ መንግስት በትምህርት ቤት ውስጥ ክበባት እንዲስፋፉ እና ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ቢያደርግ መልካም መሆኑን ገልፃለች፡፡
 ሪፖርተር
አስመላሽ እያሉ
 20/04/2003
የስፖርት ውድድር
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የዓመታዊ የስፖርት ውድድር በምድር ባቡር ሜዳ አካሄደ፡፡
 በስፖርት ውድድሩ ወጣቶች፣ አዋቂ ሴቶችና የትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡
የወረዳ 10 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስቻለው አስፋው በውድድሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ውድድሩ ከህዳር 4 ጀምሮ በድምቀት ሲካሄድ መቆየቱን ተናግረው ስፖርትን በወረዳው ከማስፋፋት በተጨማሪ ወረዳውን ወክለው በክ/ከተማ ደረጃ የሚወዳደሩ ስፖርተኞችን የመምረጥ ዓላማ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ በወረዳው የሚገኘው ማስውኹ ስፖርት ቡድን የማርሻል አርት ትርዒት ያቀረበ ሲሆን የታዳጊ ወንዶች የእግር ኳስና በአዋቂ ሴቶች መካከል የገመድ ጉተታ ውድድሮች ተካሂዷል፡፡
 በወጣት ወንዶች በስፖርት ጋዜጠኛው ኢብራሂም ሻፊ የሚመራው ኢብራሂምና ልጆቹ የእግር ኳስ ቡድን ኢንተር ስፖርትን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፎ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
 በመጨረሻም የቂርቆስ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ለአሸናፊ ቡድኖች፣ ለተወዳዳሪዎችና ልዩ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ግለሰቦች የዋንጫና የሰርተፊኬት ሽልማት ሰጥተዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
                       
20/04/2003
ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ቢሮ የተዘረፉ ንብረቶችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡
 
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ቢሮን በመስበር የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የዘረፈ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ መያዙን የቂርቆስ ክ/ከተማ ካዛንቺስ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡
 
የጣቢያው ወንጀል ምርመራ ሰራተኛ ዋና ሳጅን ስንታየሁ አረጋ፡፡
 
ዘራፊው ለጊዜው ሮጦ ካመለጠ ግብረአበሩ ጋር በመሆን ታህሳስ 18 ቀን 2003 ዓ/ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት አካባቢ በሶስት ሻንጣ የተሞላ ዕቃ ይዘው ሲጓዙ ለወንጀል መከላከል ተግባር በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ጥርጣሬ መያዙን ገልፀዋል፡፡
 
የምርመራ መዝገቡን የያዙት ዋና ሳጅን ስንታየሁ አረጋ አክለው እንደገለፁት የፓርቲው ጽ/ቤት የጥበቃ ሰራተኛ የነበረው የአምሳ ዓለቃ ነጋሽ ሀብታሙ ለጊዜው ካመለጠው ግብረ አበሩ ጋር በመሆን የጽ/ቤቱን ቢሮዎች ሰብሮ በመግባት ግምታቸው 165 ሺህ 262 ብር የሆነ 1 ቪዲዮ ካሜራ፣ 1 ፕሮጀክተር፣ 1 ፕሪንተር፣ 4 ዴል ኮምፒዩተር፣ 2 ማይክራፎን፣ 1 ስካነርና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያዎች በሻንጣ ሸሽገው ለመጥፋት ሲሞክሩ በአባላቱ ጥርጣሬ እጅ ከፍንጅ ተይዟል ብለዋል፡፡
 
በእለቱ በወንጀል መከላከል ተግባር ላይ ተሰማርተው ንብረቱን ከዘረፉ ያዳኑት ኮንስታብል ሸምሱ መሀመድና ኮንስታብል ታምራት ዲሞሬ መሆናቸውን የገለፁት መርማሪዋ ዘራፊዎቹ ንብረቱን ጥለው ለመሰወር ያደረጉትን ጥረት ለማክሸፍ በተደረገ ግብግብ ኮንስታብል ታምራት ዲሞሮ ሶስት ቦታ የመፈንከት አደጋ ደርሶበት በህክምና ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
 
ንብረታቸው ከዘረፋ የዳነላቸው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዱ ዓለም አራጌ በዕለቱ እስከ 12 ሰዓት ድረስ ቢሯቸው እንደነበሩና ለዕለቱ የጥበቃ ተረኛ ለነበረው
ለአምሳ ዓለቃ ነጋሽ ሀብታሙ ግቢውን አስረክበው መሄዳቸውን ጠቁመው ከክፉ ይታደገናል ብለው የቀጠሩት የጥበቃ ሠራተኛ ይህን ወንጀል በመፈፀሙ በእጅጉ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዱአለም አራጌ ንብረቶቹን ከዘራፊዎች ለማስጣል   ሲባል በተፈጠረ ግብግብ የፖሊስ አባሉ በመጎዳቱ የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀው የፀጥታ ኃይሉ ህይወቱን እስከመስዋዕት አድርሶ ንብረቶቹን እና ዘራፊዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ላከናወነው አኩሪ ተግባር ያለኝን አድናቆት፣ አክብሮትና ፍቅር ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ሪፖርተር
መኮንን ነጋሽ
0913047596
17/04/2003
 
 
የትግራይ ሴቶች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ አካሄደ፡፡
የዕለቱን ጉባኤ ለተሰዉ ጀግኖች ሰማእታት ሻማ በማብራት ስነ-ስርዓት የተጀመረ ሲሆን በክ/ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተወልደ ፀሐይ  ስነ-ስርዓቱን መርተዋል፡፡
 
የቂርቆስ ክ/ከተማ የትግራይ ተወላጅ የአመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ቀና የስብሰባውን ዓላማ ሲገልፁ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ይሄ ኮሚቴ እንደነበር አስታውሰው ነገር ግን አሁን በተጠናከረ ሁኔታ ድርጅታዊ አወቃቀሩን በጠበቀ መልኩ ለማስኬድ ይቻል ዘንድ በመጀመሪያ በየወረዳው የተመረጡ 5 አመራር በመሾም 50 ተወካዮች ደግሞ በወረዳ ደረጃ ተውጣጥቶ የሚካሄድ ኮንፍራንስ መሆኑን ነው የተናገሩት በቀጣይም የትግራይ ሴቶች ማህበር ምን ይመስል ነበር ከዚህ ቀደም ከዚህስ በኋላ እንዴት መሄድ አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር በክ/ከተማ ደረጃ 7 ሰባት ያሉት የአመራር ኮሚቴ እና በተጨማሪም 50 ተወካዮችን በመምረጥ የዕለቱ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡
 
መደራጀት ኃይል ነው በሚል መርህ በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ላይ በቀጣይ የተጠናከረ አካሄድ እንዲኖር አባላቱ ቃል ገብተዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ብሩክ ሎቤ
 
17/04/2003
 
 
ዜና ቂርቆስ
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር የሚገኙ ከ183 በላይ የሆኑ ከመንግስትና ከግል ተቋማት የተውጣጡ የጥበቃ አባላትን አስመረቀ፡፡
 
በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ክፍል ኃላፊ አቶ ይደጎ ስዩም በወረዳ 9 ወጣት ማዕከል የስብሰባ አዳራሽ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት በወንጀል መከላከልና በአካባቢ ጥበቃ የሰለጠኑት ተመራቂዎች ወንጀልን ከመከላከል አንጻር ሌላ ተጨማሪ 183 አጋር የፖሊስ አባላት እንዳፈሩ ነው የገለፁት፡፡
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ኦፊሰርና የስልጠናው አስተባባሪ የሆኑት ም/ሳጂን እንዳልካቸው መኮንን በበኩላቸው እንደተናገሩት በተለያዩ ተቋማት ጥበቃ የሆኑት ከ183 በላይ የሆኑ ሰልጣኞች በስልጠናው ወቅት የፍተሻ፣ የንብረት አጠባበቅ፣ ፈንጂ ማምከን፣ በአካባቢ ፀጥታ አጠባበቅ እና በህገ-መንግስት ዙሪያ ሲሰለጥኑ ቆይተው መመረቃቸውን ነው የተናገሩት፡፡
 
በምርቃት ወቅት ያገኘናቸው በዕለቱ ተመራቂ የሆኑት አቶ ገበየሁ ታደሰ እንደተናገሩት ስልጠናው በወንጀል አፈጻፀምና ንብረት አጠባበቅ ረገድ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ግንዛቤ ከማስፋት አኳያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው በቀጣይ ወደ ተግባር ለመለወጥ መዘጋጀታቸውን ነው የገለፁት፡፡
 
በተመሳሳይም በምርቃቱ ወቅት ያገኘናቸው ሌላኛዋ ተመራቂ ወ/ሮ ትዕግስት ብሩ በበኩላቸው በስልጠናው ወቅት ብዙ ግንዛቤ እንደጨበጡ ገልፀው በቀጣይም ከልምድ በመላቀቅ ባገኙት እውቀት ወደ ተግባር እንደሚለውጡት ነው የተናገሩት፡፡
 
ሪፖርተር
ብሩክ ሎቤ
የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና ስልጠና ለመምህራን እየተሰጠ ነው፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ መምህራን ሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና አስመልክቶ በፕላዝማ የተደገፈ የ2 ቀናት ስልጠና እየወሰዱ ነው፡፡
የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነማሪያም አረጋዊ እንደተናገሩት ስልጠናው እየተሰጠ የሚገኘው ለ1426 መምህራን ነው፡፡
የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናው በየትምህርት ቤቱ መሰራቱን የገለፁት ኃላፊው ግቦችን ለማሳካት እያንዳንዱ መምህር የሚሰራቸውን ተግባራት በዝርዝር ቆጥሮ የሚመዘግብበት ሲሆን ተግባርን የመለካት ስራውንም ቀላል ያደርገዋል ብለዋል፡፡
 
የትምህርት ጥራት ፓኬጁን ውጤታማ ለማድረግ የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናው የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው ከመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጡ ጋር በማጣመርና የውጤት ምዘናውን ተግባራዊ በማድረግ ለፓኬጁ ስኬታማነት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት አቶ ኪዳነማሪያም አረጋዊ፡፡
ሰልጣኝ መምህራን ከስልጠናው ያገኙትን ትምህርት በግብዓትነት ተጠቅመው ለለውጡ ስኬታማነት የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡
 
በእለቱ መምህራን ለውጡን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች የቡድን ውይይት አድረገዋል፡፡
 
ታህሳስ 14 ቀን 2003 ዓ.ም.
 
ለጤና ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡
      በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች በክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው ሥልጠና ላይ ከተለያዩ ጤና ጣቢያ የተውጣጡ ነርሶች፣ ሐኪሞች፣የጤና መኮንኖች እንዲሁም በህክምና አሰጣጥ የስራ ሂደት ዉስጥ ላሉ ባለሙያዎች በተጨማሪም በጽ/ቤት ደረጃ ለእነዚህ ክፍል ሱፐርቫይዘሮች የተዘጋጀ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡
      በክፍለ ከተማው የጤና ጽ/ቤት የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ዋና የሥራ ሂደት ባለሙያ የሆኑት ወንድማገኝ ገ/ማርያም የሥልጠናውን ዓላማ አስመልክቶ እንደተናገሩት ይህ ሥልጠና የተዘጋጀው በሥራው ላይ የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ሠልጣኞች በት/ቤት ቆይታቸው ወቅት ያገኙዋቸው፤ ወደ ሥራው ዓለም ከመጡ በኋላ ይበልጥ ሊያውቋቸውና ሊስተውሏቸው ይገባል ተብለው በተመረጡ ትምህርቶች ላይ የማንቅያ ሥራ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
      በሥልጠናው ላይ ተጋባዥ እንግዳ እና አሠልጣኝ የሆኑት በአዲስ አበባ ፋርማሲ ት/ቤት መምህርና በጥቁር አንበሳ የመድኃኒት መርጃ ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም አበበ በበኩላቸው እንደተናገሩት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር ለ3ተኛ ጊዜ የተዘጋጀ እንደሆነ አስታውሰው ከመድኃኒት ትክክለኛ አጠቃቀም ጋር በተያዘ የሚመጡ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚወሰዱ እርምጃዎችን አስመልክቶ ለሠልጣኞች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡
      በጋንዲ ሆስፒታል ለ8 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በቆየው በዚሁ ሥልጠና ላይ ከ107 በላይ ሠልጣኞች እንደተሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
 
ሪፖርተር
ብሩክ ሎቤ
13/04/2003
 
የፌደራሊዝም ስርዓት
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ተማሪዎች የፌደራሊዝም ስርዓት በህዝቦች መካከል እኩልነትን እንደፈጠረ ገለፁ፡፡
 
በፊቸር ታለንት አካዳሚ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ዳናዊት አትክልት የፌደራሊዝም ፅንሰ ሐሳብን በሀገራችን ያለውን እይታ አስመልክቶ እንደተናገረችው አገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በንጉሳዊ አመራርና በወታደራዊ አመራር ስትተዳደር እንደነበር አስታውሳ አሁን ግን በአንድነት፣ ህብረትና ያልተማከለ አስተዳደር መርህነት መመራት መጀመሯንና ይህም የፌደራሊዝም ውጤት እንደሆነ ነው የተናገረችው፡፡
 
የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ራኬብ ነጋሽ በበኩሏ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ እና እነዚሁ ብሄር ብሄረሰቦች ማህበራዊ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ መብቶቻቸው ተጠብቆ በእኩልነት ይተዳደሩ ዘንድ እንዳስቻላቸው ነው የገለፀችው፡፡
 
በተጨማሪም የዚሁ የፊቸር ታለንት አካዳሚ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ነቢል ንጉሱ በበኩሉ እንደተናገረው ፌደራሊዝም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና የፌደራል መንግስት አስተዳደራዊ እርከን በማስቀመጥና ድርሻቸውን ከመለየት አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የተናገረው፡፡
 
ሪፖርተር
ብሩክ ሎቤ

13/04/2003

 

የፌደራሊዝም ስርዓት

በቂርቆስ ክ/ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ተማሪዎች የፌደራሊዝም ስርዓት በህዝቦች መካከል እኩልነትን እንደፈጠረ ገለፁ፡፡

በፊቸር ታለንት አካዳሚ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ዳናዊት አትክልት የፌደራሊዝም ፅንሰ ሐሳብን በሀገራችን ያለውን እይታ አስመልክቶ እንደተናገረችው አገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በንጉሳዊ አመራርና በወታደራዊ አመራር ስትተዳደር እንደነበር አስታውሳ አሁን ግን በአንድነት፣ ህብረትና ያልተማከለ አስተዳደር መርህነት መመራት መጀመሯንና ይህም የፌደራሊዝም ውጤት እንደሆነ ነው የተናገረችው፡፡

የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ራኬብ ነጋሽ በበኩሏ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ እና እነዚሁ ብሄር ብሄረሰቦች ማህበራዊ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ መብቶቻቸው ተጠብቆ በእኩልነት ይተዳደሩ ዘንድ እንዳስቻላቸው ነው የገለፀችው፡፡

በተጨማሪም የዚሁ የፊቸር ታለንት አካዳሚ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ነቢል ንጉሱ በበኩሉ እንደተናገረው ፌደራሊዝም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና የፌደራል መንግስት አስተዳደራዊ እርከን በማስቀመጥና ድርሻቸውን ከመለየት አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የተናገረው፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

                                                13/04/2003

የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እየተሰጠ ነው

በቂርቆስ ክፍለከተማ ስራአስኪያጅ ጽ/ቤት የውዝፍ ይዞታዎችና ሬጉላራይዜሽን ፕሮጀክት የአገልግሎት ክፍያቸውን ለሚከፍሉ ባለይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እየሰጠ መሆኑን ገለፀ፡፡

የውዝፍ ይዞታዎችና ሬጉላራይዜሽን ፕሮጀክት ዴስክ ኃላፊ አቶ በእውቀቱ ተፈሪ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን እየሰጠ የሚገኘው የሀይለስላሴ ካርታ ለነበራቸው፤ደብተር ለነበራቸውና ደብተርና ካርታ ለሌላቸው ባለይዞታዎች ነው፡፡

ለ136 ባለይዞታዎች ካርታ ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ 45ቱ ባለይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጣቸው በካቢኔ ማፀደቁን ተናግረዋል፡፡

 በዚህም እስከ አሁን ባለው ሂደት ከ15 የሚበልጡ ባለይዞታዎች የአገልግሎት ክፍያቸውን በመፈፀም ካርታቸውን በመውሰድ ላይ ናቸው ነው ያሉት፡፡

ባለይዞታዎቹ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ባለመያዛቸው በካርታቸው ከባንክ መበደር፤ ቤታቸውን መሸጥ መለወጥና የግንባታ ፈቃድ አውጥተው ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ አስታውሰው ካርታ ማግኘታቸው ይህንን ችግር በማቀለል ንብረታቸውን የማስተዳደር መብታቸውን ያረጋግጥላቸዋል ብለዋል፡፡

የይዞታ ማረጋገጫ ካርታቸው ከተቀበሉ ባለይዞታዎች መካከል አቶ ተስፋዬ በለጠ የተባሉ ባለይዞታ በበኩላቸው ካርታው የባለቤትነት ማረጋገጫ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀው የአገልግሎት አሰጣጡም በተሻለ መልኩ ቢጠናከር መልካም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ታህሳስ 12 2003ዓ.ም

150 የጤና ኤክስቴንሽን ሞዴል አባወራዎች ተመረቁ

በቂርቆስ ክፍለከተማ የወረዳ1 ጤና ጽ/ቤት ለተከታታይ አራት ወራት ያሰለጠናቸውን 150 ሞዴል አባዎራዎችና እማወራዎች አስመረቀ፡፡

የምርቃት ስነስርዓቱ በኦሮሚያ ምክርቤት አዳራሽ በተካሄበት ወቅት ተገኝነተው ንግግር ያደረጉ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር አለማየሁ ተገኑ እንደተናገሩ ተመራቂ ሞዴል አባዎራዎች በሰለጠኑበት ሙ ህብረተሰቡን በማገልገል በጤናው ዘርፍ ለውጥ እንዲሚጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ህብረተሰቡምከሞዴል አባዎራዎቹ የሚሰጠውን ትምህርት በመቀበል ጤናማና አምራች ዜጋ ሆኖ ለ5ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬታማነት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ሚኒስትሩ ያመለከቱት፡፡

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ፋንታዬ በለጠ በበኩላቸው ተመራቂዎች ለአራት ወራት ሰልጥናችሁ ለዚህ ቀን በመብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ለፕሮግራሙ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ተመራቂዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ካሰች ጥበቡ እጅ ተቀብለዋል፡፡

ከሽማልቱ በኋላ ያነጋገርናቸው ሞዴል አባወራ አቶ ወ/ሰንበትና እማወራ ወ/ሮ ጀሚላ ሱልጣን በሰጡት አስተያየት ስልጠናው እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ሌሎች አባዎራዎችና እማወራዎች ስልጠናውን በመከታተል በየአካባቢያቸው ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ታህሳስ 10 ቀን 2003 ዓ.ም.

 

 በህዝብ ተሳትፎ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ተሠራ

 

ህብረተሰቡ በአቅሙና በጉልበቱ በየአካባቢው የሚታዩ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት ከመንግሥት ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ነዋሪዎች የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ አስገንብተዋል፡፡

80 ሺ ብር ወጪ ተደርጎ የተሠራውና 400 ሜትር ርዝማኔ ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ 24.666 ከህዝቡ የተዋጣ ሲሆን በአካባቢ የሚገኙ የመካነ ኢየሱስ፣ ሕይወት ብርሃን እና ሌሎች የህብረተሰብ አካላት የቀረውን ወጪ እንደሸፈኑ ነው የተነገረው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ በተመረቀበት ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳ 8 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘርዓይ ካህሳይ እንደተናገሩት መንግሥት የህብረተሰቡን አቅምና ጉልበት በመጠቀም የነዋሪዎችን ችግር ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ መገንባቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህ የተጀመረውን የልማት ሥራ ለማስቀጠል ህብረተሰቡ ርብርብ እንዲያድግም ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

የክፍለ ከተማው ዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቃሲም ተሾመ በበኩላቸው ቦዩ ከመሥራቱ በፊት ከፍተኛ የፍሳሽ ችግር እንደነበረ አስታውሰው የፍሳሻ ማስወገጃ ቦይ መሥራቱ ለአካባቢው ንፅህና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየትም አካባቢው ከፍተኛ የፍሳሽ አወጋገድ ችግር እንዳለበት ተናግረው ከመንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተግበር በየአካባቢው የሚታዩ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት መሰል የልማት ሥራዎችን ለማከናወን እንደተዘጋጁ አረጋግጠዋል፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ታህሳስ 09 ቀን 2003 ዓ.ም.


በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የችቦ መቀባበል ሥነ - ሥርዓት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

 

     የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አዲስ እንደመሆኑ መጠንና ከዚህ በፊት ተሞክሮ ባለመኖሩ በዚህም የተነሳ ሰፊ እና ቀጣይነት ያለው የማህበረሰብ ንቀናቄ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ በየደረጃው ያለው አመራር ፕሮግራም እንደ ቁልፍ ተግባር ተገንዝቦ ተግባርና ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ ህብረተሰቡም የፕሮግራሙን ጠቀሜታ ተገንዝቦ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ለማስቻል የዛሬው መድረክ እንደተዘጋጀ ነው የተገለፀው፡፡

      በገነት ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ በተዘጋጀው በነባር ማለትም በመጀመሪያ ዙር ሞዴል አባዎራዎችና በቀጣይ ዙር እጩ ሞዴል አባወራ ተመራቂዎች መካከል በተካሄደው የችቦ መቀባበል ሥነ - ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲ/ር ካሰች ጥበቡ እንደተናገሩት በመጀመሪያ ዙር በተመደቡ ባለሙያዎች የመነሻ ጥናት ከሰበሰቡ፣ ከተነተኑ እና ካጠናቀሩ በኋላ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ዕቅድ በማዘጋጀትና ሞዴል ቤተሰቦችን በመመልመል 2480 የመጀመሪያው ዙር ሞዴል ቤተሰቦችን አስመርቀናል ብለዋል፡፡

      በክፍለ ከተማው ጤና ጸ/ቤት የተሰሩው ሥራዎች የታዮ ለውጦችን ኤች አይ ቪ ኤድስን አስመልክቶ ለተሳታፊው ቀርቧል፡፡ በመጨረሻም በሥራው ከፍተኛ ተሳትፎ ላደረጉ አካላት የማበረታቻ ሽልማት በክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ በሆኑት በአቶ ቢያ ራያ አማካይነት ተሰጥቷል፡፡ የኤች አይ ቪ ቀንን አስመልክቶ የችቦ ማብራትና የፎቶ ኢግዚቪሽን ተካሂዷል፡፡

 

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ታኅሣስ 03  ቀን 2003 ዓ.ም.

 

የስፖርት መክፈቻ ውድድር ተካሄደ

 

በየትምህርት ቤቱ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ታዳጊ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችሉ ተገለፀ፡፡በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ዓመታዊ የስፖርት መክፈቻ ውድድር አካሂዷል፡፡

 

የስፖርት ውድድሩን በንግግራቸው የከፈቱት የወረዳ 5 ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ብርሀኑ እንደተናገሩት በየጊዜው የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ሀገሪቱን በተለያዩ መድረኮች የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያስችላሉ፡፡

 

ተመሳሳይ የስፖርት ውድድሮች ሳይቆራረጡና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በስፋት እንዲቀጥሉም ነው ዋና ስራአስፈፃሚው ያሳሰቡት፡፡

 

የስፖርት ውድድሩ በ5 የስፖርት ዓይነቶች እየተካሄደ እንደሆነ የተናገሩ ደግሞ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተፈራ ጎበና ናቸው፡፡

 

እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ በትምህርት ቤቶቹ መካከል የሚካሄዱት ውድድሮች እግርኳስ፤መረብ ኳስ፤አትሌቲክስ፤ጠረጴዛ ቴኒስና ቅርጫት ኳስ ውድድሮች ናቸው፡፡

 

ስፖርት ውድድሮቹ እስከ ታህሳስ መጨረሻ እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት ኃላፊው በሚደርጉ ውድድሮች አማካኝነት ለከተማና ሀገር አቀፍ ውድድሮች ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ያስችላል ብለዋል፡፡

 

ወላጆችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ስፖርቱን ለማሳደግ እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያጠናክሩት ጠይቀዋል፡፡

ታህሳስ 4 2003 ዓ.ም

የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን መሰረቱ

 

የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ገቢያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንሚጫወቱ ተገለፀ፡፡በቂርቆስ ክፍለከተማ የሚገኙ አስራአንዱም የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን  መሰረቱ፡፡

 

የዩኒየን ምስረታው በወረዳ9 ወጣት ማዕከል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት የክፍለከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ሎሬንሶ እንደተናገሩት የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን መመስረታቸው በየማህበራቱ የሚገጥማቸውን ችግሮች በጋራ ለመቅረፍ ያስችላል፡፡

 

ዩኒየኑ ሲመሰረት ለ5 ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

 

የዩኒየኑ መስራች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ስለሺ ሻረው በበኩላቸው ዩኒየኑ የተመሰረተበት ዋና አላማ የህብረት ስራ ማህበራቱ በተናጠል ከሚዲርጉት የስራ እንቅስቃሴ ይልቅ በጋራ እንዲሰሩ ከማድረጉም ባሸገር ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

 

ለሸማቾቹ ማህበረሰብ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ አገልግሎት በመስጠት ዩኒየኑ ወደ ላቀ አምራችነትና አቅራቢነት እንዲሸጋገሩም ያስችላል ነው ያሉት፡፡

 

በእለቱ ዩኒየኑ የሚመራባቸውን የንግድ እቅድና መተዳደሪያ ደንብ ያቀረበ ሲሆን ከማህበሩ አባላት ጋር ውይይት ከተካሄደበት በኋላ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

ታህሳስ 4 2003 ዓ.ም

 

 

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ት/ቤቶች ለተውጣጡ የሚኒ - ሚዲያ አባላት በዜና ዘገባ እና በፊቸር ራይቲን አፃፃፍ ዙሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጠ ፡፡

 

 

በምሥራቅ ጎህ ት/ቤት በክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማይ ብርሃነ እንደተናገሩት ጥራት ያለው መረጃ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ብሎም ለህብረተሰቡ ለማድረስ የሚኒ - ሚዲያ አባላት ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው በመግለፅ ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ አቅርቦት ለማሟላት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ቢያንስ ጠቅለል ያለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ ይህ ሥልጠና እንደተዘጋጀ ነው የተናገሩት፡፡

የሥልጠናው አቅራቢና በክፍለ ከተማው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች በሁነት ማደራጀትና የገፅ ለገፅ ግንኙነትና የመንግስት የፕሬስ ሥራዎች ቡድን ዋና አዘጋጅ የሆኑት አቶ መኮንን ነጋሽ ለሰልጣኞች በጋዜጠኝነት ሙያ አመሰራረትና አመጣጥ፣ በጋዜጠኝነት ሥነ - ምግባር፣ በዜና ዘገባ አፃፃፍ እና በፊቸር ራይቲንግ ዙሪያ ለሠልጣኞቹ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

በሥልጠናውም ከህዝብና ከመንግሥት ት/ቤቶች የተውጣጡ ከ40 በላይ ሠልጣኞች መገኘታቸው ታውቋል፡፡

 

 

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ 

ታኅሣስ 02 ቀን 2003 ዓ.ም.

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በBSC እና ፋክስ አውቶሜሽን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

 በክፍለ ከተማ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት አማካኝነት በግብርና መሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ እንደተገለፀው ከዚህ ቀደም በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የICT ባለ ሙያዎች መካከል             4 ሠልጣኞች ተመርጠው በBSC እና ፋክስ አውቶሜሽን ዙሪያ እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ይኸውም ሥልጠና በእነዚህ ሠልጣኞች አቅራቢነት የተዘጋጀ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

በክፍለ ከተማው የICT ባለሙያ እና የሥልጠናው አቅራቢ የሆኑት                  አቶ እምሩ ፈለቀ የሥልጠናውን ዓላማ አስመልክተው እንደተናገሩት ይህ ሥልጠና አመራሩ በBSC እና ፋክስ አውቶሜሽን ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል የተዘጋጀ እንደሆነ በመግለፅ የBSC እና ፋክስ አውቶሜሽንን ምንነትና የአሠራርና አተገባበር ሂደቱን ለሠልጣኞች አብራርተዋል፡፡

የክፍለ ከተማ አቅም ግንባታ ኃላፊ የሆኑት አቶ አምላኩ ተበጀ በበኩላቸው እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው ደረጃ ከህዳር 15 ጀምሮ አጠቃላይ ክፍለ ከተማውና በየወረዳው የሚገኙ መስሪያ ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ በይፋ መሻገራቸውን አስታውሰው የዛሬውም ሥልጠና የዚሁ ቀጣይ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

በሥልጠና ወቅት በBSC እና ፋክስ አውቶሜሽን ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረክ ተገቢውን ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

 

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ  

 

 

ህዳር 30 ቀን 2003 ዓ.ም.

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ባህልና ቱሪዝም ቡድን የየወረዳዎቹን ኮሙኒኬሽንና ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶች እንቅስቃሴ ጎበኘ

  በዕለቱ ቡድኑ የወረዳ 1፣ 2 እና 3 ኮሙኒኬሽን እና ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶችን የ2003 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን የገመገመ ከመሆኑ በተጨማሪ በታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እና የየጽ/ቤት ኃላፊዎቹ አሉብን ባሏቸው ችግሮች ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
  የጽ/ቤት ኃላፊዎቹ ላነሷቸው የባለሙያ እጥረት መንግሥት ለእያንዳንዱ ጽ/ቤት ከአምናው የተሻለ ሊያሰራ የሚቻል በጀት የመደበ በመሆኑ ያለውን የባለሙያ እጥረት ከየወረዳዎቹ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር መቅረፍ እንደሚቻል አመላክቷል፡፡

በሌላም በኩል የየወረዳው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በየወሩ መጽሔት ለማውጣት መሞከራቸው አበረታች ቢሆንም የሚያወጡት መጽሔት የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ስፖንሰሮችን አበራክቶ በመጽሄቱ ላይ በማስተዋወቅ ጠንከር ያለ ሥራ መሠራት እንዳለበት አስገንዝቧል፡፡

በስፖንሰሮች አማካኝነት ወረዳ 2 ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ቤተ መጽሐፍትን ከፎቶ ለማደራጀት፣ የወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ደግሞ ቪዲዮ ካሜራ ለመግዛት ያደረጉት ጥረት የሚበረታታና ለሌሎችም አርአያ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ከተማችን አዲስ አበባ ለተያያዘችው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬቱ በተለይም የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤቶች መረጃዎችን በወቅቱ ወደ ሕዝቡ በማድረስ የልማት ሰራዊትን ማበራከት ስለሚጠበቅባቸው ከዚህ በበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከአደራ ጭምር አሳስቧል፡፡

 ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ህዳር 30 ቀን 2003 ዓ.ም.

 የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የኮሙኒኬሽንና ባህልና ቱሪዝም ቡድን የየወረዳዎቹን ኮሙኒኬሽንና ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶች እንቅስቃሴ ጎበኘ

በዕለቱ ቡድኑ የወረዳ 1፣ 2 እና 3 ኮሙኒኬሽን እና ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶችን የ2003 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን የገመገመ ከመሆኑ በተጨማሪ በታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እና የየጽ/ቤት ኃላፊዎቹ አሉብን ባሏቸው ችግሮች ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

የጽ/ቤት ኃላፊዎቹ ላነሷቸው የባለሙያ እጥረት መንግሥት ለእያንዳንዱ ጽ/ቤት ከአምናው የተሻለ ሊያሰራ የሚቻል በጀት የመደበ በመሆኑ ያለውን የባለሙያ እጥረት ከየወረዳዎቹ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር መቅረፍ እንደሚቻል አመላክቷል፡፡

 በሌላም በኩል የየወረዳው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በየወሩ መጽሔት ለማውጣት መሞከራቸው አበረታች ቢሆንም የሚያወጡት መጽሔት የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ስፖንሰሮችን አበራክቶ በመጽሄቱ ላይ በማስተዋወቅ ጠንከር ያለ ሥራ መሠራት እንዳለበት አስገንዝቧል፡፡

 በስፖንሰሮች አማካኝነት ወረዳ 2 ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ቤተ መጽሐፍትን ከፎቶ ለማደራጀት፣ የወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ደግሞ ቪዲዮ ካሜራ ለመግዛት ያደረጉት ጥረት የሚበረታታና ለሌሎችም አርአያ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ከተማችን አዲስ አበባ ለተያያዘችው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬቱ በተለይም የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤቶች መረጃዎችን በወቅቱ ወደ ሕዝቡ በማድረስ የልማት ሰራዊትን ማበራከት ስለሚጠበቅባቸው ከዚህ በበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከአደራ ጭምር አሳስቧል፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ህዳር 28 ቀን 2003 ዓ.ም.

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 ም/ቤት 3ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ

ጉባዔውን አካሄደ

የም/ቤቱን ጉባዔ በንግግር የከፈቱት የወረዳው ም/ቤት አፈ - ጉባዔ          ክብርት አዳነች እንደተናገሩት በየደረጃው የተቋቋሙ ም/ቤቶች የህብረተሰቡን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

በዕለቱ በወረዳው በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው የም/ቤቱ ጉባዔ ላይ ተገኝተው የወረዳውን የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ ክንውን ያቀረቡት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው መኮንን እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ በአብዛኛው ዕቅዱን በተገቢው ሁኔታ ለመተግበር መቻሉንና አንዳንድ በሥራ ላይ የታዩ ክፍተቶችንም በቀጣይ በመለየት የማሻሻል ሥራ እንደሚሠራ ነው የገለፁት፡፡

በቀረበው ቃለ - ጉባዔ ላይም በመወያየት የማፅደቅ ሥነ - ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ በቀጣይም ምን መሥራት አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ለም/ቤቱ አባላት ቀርቦ በስፋት በመወያየት ፀድቋል፡፡ በተጨማሪም በወረዳው በልማት የተሠሩ ሥራዎችና ቀጣይ በሕዝብ ተሳትፎ ሊሠሩ የታቀዱ የልማት ሥራዎችን ለም/ቤቱ በማቅረብ በአብላጫ ድምፅ በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

 ህዳር 20 ቀን 2003 ዓ.ም.

         የቦሌ ማተሚያ ቤት ሠራተኞች የብአዴን 30ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን አከበሩ

 በታላቅ መስዋዕትነትና ትግል የተገኘውን ሰላምና ዲሞክራሲ ወደ ልማት ሊቀይሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቦሌ ማተሚያ ቤት ሠራኞች የብአዴን 30ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የብአዴን ኢህዴግ በትግል ታሪክ እና በ5 ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዙሪያ ከቦሌ ማተሚያ ድርጅት አባል የሚጠበቅ ሚና በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡

ለሰማዕታቱ መታሰቢያ የህሊና ፀሎትና የሻማ ማብራት ሥነ - ሥርዓት በድርጅቱ ሠራተኞች ተካሂዷል፡፡

በድርጅቱ የሠራተኛ ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ እርዚቁ መሐመድ እንደተናገሩት ብዙዎች የተሰውለት ዓላማ በብዙ ትግል ዛሬ ለደረሰንበት የልማትና የመልካም አስተዳደር እንድንደርስ እንዳስቻለን ገልፀው በቀጣይም የድርጅቱ ሠራተኞች ይህንን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ድል ከመንሳት አኳያ መንግሥት ባዘጋጀው የልማትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመሳተፍ የበኩላቸውን ለመሥራት እንዲነሳሱ ጥሪያቸዉን ያስተላለፉት፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

                                               ህዳር 20 ቀን 2003 ዓ.ም.

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የአገርህን እወቅ ክበባት በቱሪዝም ዙሪያ የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጠ

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት በክፍለ ከተማው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የአገርህን እወቅ ክበባት ተወካዮች ስለ ቱሪዝም ምንነት፣ በቱሪዝም ውስጥ ስለሚሳተፉ አካላትና በሰው ሰራሽ ቱሪዝም መስህብና ተፈጥሮአዊ የቱሪዝም መስህቦች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ገብሩ አስካል እንደተናገሩት የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካባቢውን ብሎም አገሩን ከማወቅ አንፃር እንዲህ ዓይነት ክበባትን መቋቋም እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው፡፡ ተማሪዎች ከፅንስ ሃሳብ ባለፈ በተግባር አካባቢያቸውንና አገራቸውን ማወቃቸው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነው ያስረዱት፡፡

ከተለያዩ ተሳታፊዎች ከኑሮ ውድነት አኳያ የአገርህን እወቅ ክበባት ህልውና ጥያቄ ውስጥ እየገባነው ለሚሉትና ሌሎች መሰል ጥያቄዎች ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ እንደሚያመቻች ቃል ገብተዋል፡፡

ስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት ወ/ሮ ቆንጅት ሥዩም እንደተናገሩትን የአገርህን እወቅ ክበባት በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ መካከል ያለውን የወንድማማችነት ቅርርብ ከማጎልበት አንፃርና የአካባቢ ግንዛቤን ከማጎልበት  ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የገለፁት፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

 ህዳር 15 ቀን 2003 ዓ.ም.


በአስጎብኝነት ሥነ - ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ላሉ አስጎብኝዎች የአስጎብኝነት ሥነ - ምግባርን በተመለከተ በባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ልማትና ቅርስ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት የሆኑት አቶ ገብሩ አስካል እንደተናገሩት ቀጣይነት ያለው የቱሪስት ፍሰት እንዲኖር የአስጎብኝ አካላት የአስጎብኝነት ሥነ - ምግባርንና መርሆን በተከተለ መልኩ መሥራት እንዳለባቸው በመጥቀስ የተረጋጋና  ወጥ የሆነ የቱሪዝም ሥርዓት ማጎልበት እንደሚገባቸውና ተጠያቂነት ከማስፈን አንፃር በማህበር መደራጀታቸውንና የሥራ ፈቃድ መውሰዳቸው መልካም ጅማሮ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

በስልጠናው ወቅት አቶ ገብሩ አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት የሥራ ፈቃድ ያላቸውና በማህበር የተደራጁ አስጎብኝ እንደመሆናቸው ሰልጣኞቹ የአገር ገፅታ ግንባታን በተመለከተ ከፍተኛ አደራ እንደተጣለባቸው በመግለፅ ህገ - ወጥ የሆኑ በቱሪዝም ዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ከመቅረፍ አንፃር በቀጣይ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንደተመቻቸ ነው የተናገሩት፡፡

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በማህበር የተደራጁ ቢሆንም ነገር ግን ከቢሮው ጋር ተቀራርቦ ከመሥራት አኳያ ክፍተቶች እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ግን በተመቻቸው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የሚጠበቅባቸውን ተግባርም ለመወጣት በትጋት እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡


ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ህዳር 15 2003 ዓ.ም.

 የቢኤስሲ ሰነድ ስምምነት ተደረገ

በቂርቆስ ክፍለከተማ ሴክተር ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የወረዳ ዋና ስራአስፈፃሚዎች የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን  ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የሰነድ ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት የክፍለ ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምላኩ ተበጀ እንደተናገሩት የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና ስራዎችን ቆጥሮ የመስጠትና የመቀበል አሰራርንና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ነው፡፡ በዚህም ጽ/ቤቶቹ ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት የሚስችላቸውን የሰነድ ስምምነት አድርገዋል ብለዋል፡፡

ስምምነቱ በ3 የተከፈለ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ዋና ስራአስፈፃሚ ከሴክተር ጽ/ቤቶችና ከወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ያደረጉት የስምምነት ሰነድ ፊሪማ እንዲሁም የክፍለ ከተማው አቅምግንባታ ጽ/ቤት ከወረዳዎች አቅምግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ያደረጉት የስምምነቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት ስድስት የክፍለ ከተማው ጽ/ቤቶች እንደሆኑ ገልፀው የቀሩት ጽ/ቤቶች ለሰራተኞቻቸው ስልጠናዎችን ከሰጡ በኋላ የሰነድ ስምምነቱን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የክፍለከተማው ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ በበኩላቸው የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት ጽ/ቤቶች ለውጡን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት አመራሮች  ለውጡን ለመተግበር የሚያስችሉ ግብዓቶችን በማሟላትና ፈፃሚዎች ስልጠናዎችን እንያገኙ በማድረግ  እንደሚተገብሩት ገልፀዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ህዳር 15 2003 ዓ.ም

የወረዳ 03 የጤና ኤክስቴንሽን ሞዴል አባወራዎች

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 ጤና ጽ/ቤት በጤና ኤክስቴንሽን የሰለጠኑ 163 ሞዴል አባወራዎችንና እማዎራዎችን በኤዶም ገነት አዳራሽ አስመረቀ፡፡

የምርቃት ሥነ - ሥርዓቱን በንግግራቸው የከፈቱት የወረዳ 3 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደስታ በላይ እንደተናገሩት አባዎራዎቹ የተመረቁት ሀገራችን የ5 ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ላይ ባለችበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡

በዚህም በቀጣዩ ዓመታት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን በመፍጠር የታቀደው ዕቅድ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን ደጉ በበኩላቸው የተመረቁት 163 ሞዴል ሠልጣኝ አባወራዎች ለአራት ወራት መሰልጠናቸውን ገልፀው የተሰጣቸው ሥልጠና በተግባር ማዋል እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

መንግሥት የቀረፀውን በሽታ መከላከል ፖሊሲ ስኬታማ ለማድረግ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በጋራ ለሠሩት አባዎራዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ደግሞ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ ናቸው፡፡

በዕለቱ በስልጠናው ወቅት ጥሩ እንቅስቃሴ ላሳዩ ሞዴል አባወራዎችና እማወራዎች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ፕሮግራሙን የተመለከቱ የኪነ - ጥበብ ሥራዎችም ቀርበዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ህዳር 15 2003 ዓ.ም.

ህዳር 15 ቀን 2003 ዓ.ም.

የፅዳት ሥራ በወጣቶች

 የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣት ማህበርና ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በመተባበር በክፍለ ከተማው የወንዝ ዳርቻዎችና በቆሻሻ ሥፍራዎችን በማፅዳት ላይ መሆኑን ተመለከተ፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣት ማህበር ፀሐፊና የፅዳት አስተባባሪ ወጣት መድህን አርአያ እንደተናገረችው የፅዳት ሥራው በክፍለ ከተማው የሚገኙ የወንዝ ዳርቻዎችና በቆሻሻ የተሸፈኑ ሥፍራዎችን ማፅዳት ሲሆን ለ46 ሥራ አጥ ወገኖች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡

የፅዳት ሥራው ጥቅምት 21 እንደተጀመረ የተናገረችው ወጣት መድህን በፅዳት ዘመቻው 298 ሜትር ኪዮብ ቆሻሻ ማስወገድ እንደተቻለ ገልፃለች፡፡የመኪና እጥረቱ ቢቀረፍልን ከዚህም በላይ ማፅዳት እንደሚቻል ገልፃ የተፀዱ ቦታዎችን ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ንፅህና እንዲጠብቅላቸውም ነው ጥሪዋን ያቀረበችው፡፡

በእስራኤል ጋራዥ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፅዳት ሥራውን ሲያከናውን ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ግዛቸው በበኩሉ ባገኘው የሥራ ዕድል መደሰቱን ገልፆ ወጣቶች ሥራ ሳይንቁ ከሠሩ ውጤታማ መሆን ይችላሉ ብሏል፡፡

ወ/ሮ ሎሜ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪም በአካባቢው ከፍተኛ የፅዳት ችግር እንደነበረበት አስታውሰው ፅዳቱ መደረጉ እንዳስደሰታቸው ነው የገለፁት፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ህዳር 15 2003 ዓ.ም.

ህዳር 15 2003 ዓ.ም

በመልሶ ማልማቱ 12 ሄክታር ይለማል ተባለ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማና የወረዳ1 አስተዳደር ከወረዳ1 የቀድሞ ቀበሌ27 ነዋሪዎች ጋር በመልሶ ማልማቱ ዙሪያ የመጀመሪያ ውይይቱን አካሄደ፡፡በመልሶ ማልማቱ 12 ሄክታር መሬት እንደሚለማም ታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለመልሶ ማልማቱ ከተመረጡ ክፍለከተሞች አንዱ የቂርቆስ ክፍለከተማ ነው፡፡ በክፍለከተማው ለኑሮ አመቺ ያልሆኑና በአካባቢው በሚሰሩ የልማት ተግባራት ምክኒያት በመልሶ ማልማቱ እያለማ ይገኛል፡፡

በወረዳ 1 በቀድሞ ቀበሌ 27 የሚኖሩ ነዋሪችንም በመልሶ ማልማቱ ውስጥ በማካተት ነው በመወያየት ላይ የሚገኘው፡፡ ውይይቱ በጠመንጃ ያዥ ት/ቤት አዳራሽ ሲካሄድ ነዋሪዎቹ ከነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል፤- ክፍለከተማው ለመልሶ ማልማቱ ለምን ተመረጠ፤አቅመ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎችስ ምን ታስቧል፤መልሶ ማልማት ማለት ምን ማለት ነው የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የወረዳው ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ተስፋዬ በበኩላቸው በመልሶ ማልማቱ 12 ሄክታር መሬት የሚለማ ሲሆን 257 የግል፤የቀበሌና የኪቢአድ ቤቶች በመልሶ ማልማቱ የሚነሱ ቤቶች ናቸው ብለዋል፡፡ በወረዳው 2 የመልሶ ማልማት ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው  ከነዋሪዎቹ የተውጣጡ ኮሚቴዎች በማዋቀር ነዋሪዎቹ ያለ እንግልት የሚገባቸውን የመኖሪያ ስፍራ እንደሚያገኙም ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ህዳር 11 2003 ዓ.ም

የእድሮች ህብረት ለችግረኛ ህፃናት ለገሰ

በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 5 የእድሮች ህብረት ለ200 ወላጅ አልባላና ችግረኛ ህፃናት የትምህርት መሳራያዎች፤የት/ቤት ዩኒፎም፤ጫማና ሳሙናዎችን በልገሳ ሰጠ፡፡

 

የወረዳ 5 እድሮች ህብረት ም/ሰብሳቢ አቶ አሰፋ ሸንቁጤ እንደተናገሩት ህብረቱ በወረዳው የሚገኙ 6 እድሮችን በአንድ በማሰባሰብ የተመሰረተ ህብረት ነው፡፡

 

የእድሮች ህብረቱ እንደተለመደው የሞተን ከመቅበር ባለፈ በወረዳው ለሚገኙ ችግረኛና ወላጅ አልባ ህፃናት ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ ከመንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር የትምህርት መሳሪያዎችንና ቁሳቁሶችን ለመለገስ ችሏል ብለዋል፡፡

 

የእድሮች ህብረቱ በቀጣይ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የትምህርት እድል እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱን ተናግረው ሌሎች እድሮችም የህብረቱን አርአያ መከተል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
የትምህርት መሳሪያዎቹን ከወሰዱት ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በበኩላቸው የእድሮች ህብረቱ ለልጆቻቸው ባደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቻን ገልፀው ሌሎች እድሮችም የዚሁን አላማ እንዲከተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ 

 

 

ህዳር 10 ቀን 2003 ዓ.ም.

    የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ፡፡

ምክር ቤቱ በወረዳ 9 ሁለገብ ወጣት ማዕከል ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የክፍለ ከተማው ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ሀዱሽ ኃይሌ እንደተናገሩት መንግሥት ሀገራችንን በሚቀጥሉት ሃያ ዓመታት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ለማሳለፍ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ይህ ዕቅድ በትግበራ ዘመኑ መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ያስችላታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህን ወደ ተግባር መለወጥ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አካላት እና የሕዝብ ቢሆንም በተለይ የምክር ቤት አባላት ሕዝቡ በጣለባቸው አደራ ሳቢያ ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ በዚህም ዕቅዱን ለመተግበር የላቀ ጥረት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በጉባዔው የ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባዔን ያፀደቀ ሲሆን የክፍለ ከተማውን 2003 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርትንም አዳምጧል፡፡

የሩብ ዓመቱን ሪፖርት ያቀረቡት የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ በሪፖርታቸው ላይ እንዳመለከቱት በሁሉም ጽ/ቤቶች አበረታች ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በተለይም የገቢዎች ጽ/ቤት የሩብ ዓመት ክንውን የላቀ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ አቶ ቢያ በሪፖርታቸው ላይ በመልሶ ማልማት የሚነሱ ነዋሪዎችን በማሳመን ከቦታው እንዲነሱ ከማድረግ አኳያ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ ያለው አመራር ተቀናጅቶ የሚፈለገውን ያህል አለመሥራት በድክመት የተስተዋለ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው የቀጣዩንም ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫ አመላክተው ለስኬቱ ግንባር ቀደም ሆኖ የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የምክር ቤት አባላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል፡፡

በምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ በሕዝብ ተሳትፎ የሚሠሩ ሥራዎች በክፍለ ከተማው ዲዛይንና ግንባታ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ቃሲም ተሾመ የቀረበ ሲሆን በጉባዔው ላይ የምክር ቤት አባላቱ ላነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አስፈፃሚ አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

     ህዳር 09 ቀን 2003 ዓ.ም. 

በፅዳት ዘመቻ ዙሪያ መግለጫ ተሰጠ
ህብረተሰቡ ቆሻሻን በአግባቡ እንዲያስወግዱ ጥሪ ቀረበ፡፡ 

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤትና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤቶች ህዳር 12 በሚካሄደው የፅዳት ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ጽ/ቤቶቹ ህዳር ሲታጠን ቀንን በማስመልከት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የክፍለ ከተማው ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መክብብ ማሞ እንደተናገሩት በየዓመቱ ህዳር 12 የሚከበረው የፅዳት ዘመቻ ላይ ቆሻሻን በማቃጠል ከማክበር ይልቅ ቆሻሻን በመሰብሰብና ሊሰራው ለተቋቋሙ ማህበራት በማስረከብ እንዲከበር ለማድረግ ታስቧል፡፡

በዚህም ከወጣት ማህበር ጋር በመተባበር ከጥቅምት 20 - ህዳር 20 የሚቆይ የፅዳት ዘመቻ በማካሄድ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ወንዞች በመፅዳት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ በአሥራ አንዱም ወረዳዎች 47 ማህበራት የፅዳት ሥራ እየሠሩ እንደሚገኝም ነው  አቶ መክብብ የገለፁት፡፡

በክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የአካባቢ ግንዛቤና ኢንስፔክሽን ኦፊሰር        አቶ በራሁ ደመወዝ በበኩላቸው ህዳር ሲታጠን ቆሻሻን የማስወገድ ባህላችንን የሚያዳብር ቢሆንም ቆሻሻን በማቃጠል የሚደርሰው የአካባቢ ብክለትና የጤና ችግር ግን ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ ቆሻሻን በሚያስወግድበት ወቅት ቆሻሻ ሀብት መሆኑን ተገንዝቦ የተሰበሰቡ ቆሻሻዎች ለማህበራት በማስረከብ ጤናውንና አካባቢውን ከብክለት እንዲጠብቅ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

 

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

                       ህዳር 08 2003 ዓ.ም

የብአዴን 30ኛ ዓመት ምስረታ በወረዳዎች ተከበረ

የብአዴን አባላት ጀግኖች ታጋዮች በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኘውን ልማት፤ሰላምና ዴሞክራሲ የማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡

የብአዴን 30ኛ ዓመት ምስረታ በዓል በቂርቆስ ክፍለከተማ በሚገኙ አስራአንዱም ወረዳዎች በልዩልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

በዓሉን በፓናል ውይይት ያከበሩት የብአዴን አባላትና አጋር ድርጅቶች ሲሆኑ በዓሉ በተከበረበት ወቅት እንደተገለፀው ጀግኖች በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኘውን ሰላምና፤ዴሞክራሲ የአሁኑ ትውልድ ልማትንና እድገትን ለማረጋገጥ ሊጠቀምበት ይገባል፡፡ በመሆኑም ሀገራችን ድህነትን ድል ለመንሳት የምታደርገውን እንቅስቃሴ የብአዴን አባላት

በዓሉ በወረዳ 02 በተከበረበት ወቅት የወረዳው አፈጉበኤና የብአዴን ፀሐፊ አቶ ካሳሁን ታደሰ እንደተናገሩት የ30ኛ ዓመቱን የብአዴን ምስረታ በዓል በወረዳው የፅዳት ዘመቻዎችና የፓናል ውይይቶችን በማካሄድ እየተገበረ ይገኛል፡፡

በሀገሪቷ ያለውን ድህነትና ኃለቀርነት ታሪክ ለማድረግ የብአዴን አባላት ሌሎች የአማራ ብሔር ተወላጆችን በማስተባበር ሊቀንቀሳቀሱ ይገባል ነው ያሉት፡፡

የወረዳው ነዋሪ የብአዴን አባላት በሰጡት አስተያየትም የብአዴን 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ከማክበር ባሻገር በሀገራችን የወጣውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት በስፋት ለመንቀሳቀስ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

በእለቱ የብአዴንን የትጥቅ ትግል የሚያሳይ ጥናታዊ ፊልም ለታዳሚዎች ቀርቧል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ህዳር 08 2003 ዓ.ም

የልማት ኮሚቴዎቹ ከአስተዳደሩ ጋር ተወያዩ

መንግስት ከሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት ጎን ለጎን የህብረተሰቡን አቅም ተጠቅሞ ልማትን ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10፤3ና 2 አስተዳደር አካላት በየቀጠናው ከተዋቀሩት የልማት ኮሚቴ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

 ውይይቱ በወረዳ 10 በተካሄደበት ወቅት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ሰይፉ እንደተናገሩት  በከተማዋ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የህብረተሰቡን ጉልበት፤ገንዘብና እውቀት ለመጠቀም በሚያስችለውን እቅድ ዙሪያ በየቀጠናው ከተዋቀሩ የልማት ኮሚቴ አባላት ጋር መወያየት አስፈልጓል፡፡

በየቀጠናው 15 የኮሚቴ አባላት በመምረጥ የየቀጠናውን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ የልማት እቅድ እንደሚያወጡ ገልፀው ልማቱ  ኮሚቴዎቹ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎች ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ አስተዳደሩ ከጎናቸው መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ የልማት ኮሚቴዎች በሰጡት አስተያየት ደግሞ መንግስት የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ ከህብረተሰቡ ጋር ለመስራት ማቀዱ ሊበረታታ ይገባል፤ህብረተሰቡ በየአካበባው ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በስፋት ሊንቀሳቀስ ይገባል የሚሉና ውይይቱ በልማት ስራ ውስጥ ለምንደርገው እንቅስቃሴ አቅም ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ህዳር 08 2003 ዓ.ም

በኤች.አይ.ቪና ሥነ - ተዋልዶ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 የወጣት ሊግ ከክፍለ ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤትና ከመድሃን አክስት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከ60 በላይ ለሆኑ ወጣቶች በኤች.አይ.ቪና ሥነ - ተዋልዶ ዙሪያ የሦስት ቀን ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የሥልጠናው አዘጋጅና አስተባባሪ የሆኑት የወረዳ 4 የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ወጣት ዮሐንስ ገብሬ እንደተናገሩት ዕድሜያቸው ከ15 – 29 ዓመት የሆናቸውን ወጣቶች በአጠቃላይ የማህበረሰብ ውይይት በኤች.አይ.ቪ እንዲሁም በሥነ - ተዋልዶ ዙሪያ ከመድሃን አክት ጋር በመተባበር በአጠቃላይ በወረዳው ካሉ የወጣት ፎረምና ፌዴሬሽን የተውጣጡ ወጣቶች እንደሆኑ ነው የተናገሩት፡፡

የወረዳው የኢህአዲግ ወጣት ሊግ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ኃይሌ እንደተናገሩት ምንም እንኳን ሥልጠናው በአጭር ጊዜ የተካሄደ ቢሆንም ነገር ግን ወጣቱ በንቃት ሥልጠናው ላይ መሳተፉን ጠቅሰው በቀጣይም ወደ ተግባር እንዲገቡና ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ እንዲተገብሩት አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ሥልጠናውን በገንዘብ በመደገፍ ስኬታማ እንዲሆኑ ያላሰለሰ ጥረት ላደረጉት ለአዲስ አበባ ቃለ - ሕይወት መድሃን አክትስ ጽ/ቤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊ ወጣት ኢየሩሳሌም ታደሰ በሰጡት አስተያየት ማህበረሱቡ ከዚህ ቀደም ስለ ኤች.አይ.ቪ ሳይሰማ ቀርቶ ሳይሆን በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ ባለማግኘቱ የተነሳ ነው ችግሩ በሚፈለገው ያክል ሊቀረፍ ያልቻለው፡፡ ስለዚህም እንደዚህ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እንደዚህ ያሉትን ሥልጠና አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ያገኙትን ግንዛቤ ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚተጉ ገልፀዋል፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

  ህዳር 04 2003 ዓ.ም

 

የቢኤስሲ ስልጠና ለክፍለ ከተማው አመራሮችና ፈፃሚዎች ተሰጠ

ሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናን አስመልክቶ ለ2ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለቂርቆስ ክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮችና ፈፃሚዎች በመሰጠት ላይ ነው፡፡

ስልጠናውን በፕላዝማ የሰጡት የአዲስ አበባ አቅም ግንባታ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሩ ማሩ እንደተናገሩት ስልጠናው የመሰረታዊ አሰራር ሂደት ለውጡ ያላሟላቸው ስራዎች ተለይተው አዳዲስ የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው፡፡

የተቀናጀ የለውጥ መሳሪያዎቹ በአመለካከት፤ግብዓት አጠቃቀምና በክህሎት የዳበረ ፈፃሚና አመራር በማብቃት ህብረተሰቡ የሚፈልገውን የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባር ለማፋጠን የሚያስችሉ መሆናቸውንም ነው የገለፁት፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምላኩ ተበጀ በበኩላቸው በክፍለከተማው ቁጥራቸው ወደ 2500 የሚጠጋ ሰልጣኞች በ42 ቡድኖች ተከፋፍለው እየሰለጠኑ እንደሚገኙ ነው ያስታወቁት፡፡

በሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና ስርዓቱ ስራዎችን ቆጥሮ የመስጠትና የመቀበል አሰራርን፤ስትራቴጂንና ራዕይ ያለው ስራን የሚተገብር በመሆኑ የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጡን የሚጢናክር ነውም ብለዋል፡፡

በተወሰኑ ወረዳዎችና ሴክተር ጽ/ቤቶች ሙከራ ትግበራው እንደተካሄደ አስታውሰው ወደ ሙሉ ትግበራው ለመግባት የሚያስቸሉ የትግበራ ሰነዶች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ሰልጣኞች የለውጥ መሳሪያዎቹን ውጤታማ ለማድረግ መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም በመግለፅ ጭምር፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ህዳር 03 ቀን 2003 ዓ.ም.

በኮብልስቶን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

          የመንግሥት የረጅምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተቋማት የጎላ ድርሻ እንዳላቸው ተገለፀ፡፡

      በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ላሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች በኮብልስቶን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

 

      የክፍለ ከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ሉሌ የሥልጠናውን ዓላማ አስመልክቶ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት ወጣቱን በኮብልስቶን ዙሪያ ለማሠልጠን ተሞክሯል ነገር ግን በአመለካከት ደረጃ አዋጭ መሆኑን አለማወቅ ይህም ወደ ሥልጠና አለመምጣት ከሠለጠኑም በኋላ የመጥፋት አዝማሚያ ይታይ እንደነበር አስታውሰው የዚህም ችግር ዋነኛ ማጠንጠኛው የአስተሳሰብ ችግር ስለሆነ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ይህ ሥልጠና እንደተዘጋጀ ነው የገለፁት፡፡

      በተጨማሪም ሠልጣኙ ከሥልጠናው በኋላ ገቢውን በማሳደግና ከሚያገኘው ገቢ የቁጠባን ባህል እንዲያጎለብት አሳስበዋል፡፡

      የሥልጠናው ተሳታፊና የወረዳ 4 ነዋሪ ወጣት መልካሙ ዋለ እንደተናገረው ሥልጠናው በኮብልስቶንና ዲሞክራሲ ፅንስ ሀሳብ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዳስገኘለት በመግለፅ በቀጣይ ያገኘውን ሥልጠና ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚተጋ ነው ያረጋገጠው፡፡ በተመሳሳይም የወረዳ 8 ነዋሪ ወጣት አብዮት ታፈሰ እንደተናገረችው ሥልጠናው ያለባቸውን ችግር እንዴት መቅረፍ እንዳለባቸው ግንዛቤ እንደፈጠረላት ነው የገለፀችው፡፡ 

ሪፖርተር

- ብሩክ ሎቤ

ህዳር 1 2003 ዓ.ም

የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሰራተኞችና የወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊዎች ከቂርቆስ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር የልምድ ልውውጥ አደረጉ፡፡ በጽ/ቤቱ የሁለቱንም ኬዝ ቲሞች የስራ እንቅስቃሴም ጎብኝቷል፡፡

የልምድ ልውውጡ የተዘጋጀው በጉለሌ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የተመራው የልዑካን ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰሩ ስራዎችን በመጎብኘት በሁለቱ ክፍለከተሞች የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ታስቦ ነው፡፡

የጉለሌ ክፍለከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻው ተፈራ ከጉብኘቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት እንዳሉት በቂርቆስ ክፍለከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባደረግነው የልምድ ልውውጥ የሁለቱም ቡድን ሰራተኞች ባለው ሰው ሀይል ተጠቅመው በቡድን በመስራት ያሳዩት ትብብር ሊበረታታ የሚገባ ነው፡፡

በጽ/ቤቱ ራሱን የቻለ የምስልና ድምፅ ማቀናበሪያ ማሽን አለመኖርና የባለሙያዎች እጥረት መኖር እንደክፍተት የሚገለፅ መሆኑን ተናግረው የቢሮ አቀማመጡም መስተካከል እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

የልምድ ልውውጡን ያደረጉት የጉለሌ ክፍለከተማ ሰራተኞችም ከልምድ ልውውጡ አመራሩ ከሰራተኛው ጋር ተናቦ መስራቱ መገንዘባቸውን ገልፀው ከክፍለ ከተማው የተገኘውን ተሞክሮ በክፍለከተማቸው ለመተግበር አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

     ህዳር 1 2003 ዓ.ም

በህዝብ ተሳትፎ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ተሰራ

ህብረተሰቡ በአቅሙና በጉልበቱ በየአካባቢው የሚታዩ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት ከመንግስት ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡ በቂርቆስ ክፍለከተማ የወረዳ 8 ነዋሪዎች የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ አስገንብተዋል፡፡

 15 ሺ ብር ወጪ ተደርጎ የተሰራውና 90 ሜትር ርዝማኔ ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ 13 ሺ ብሩ ከአንድ ግለሰብ በተገኘ ብር ሲሆን ቀሪ 2 ሺ ብሩ ደግሞ ከህብረተሰቡ በተዋጣ ገንዝብ የተሰራ ነው፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዩ በተመረቀበት ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘርዓይ ካህሳይ እንደተናገሩት መንግስት የህብረተሰቡን አቅምና ጉልበት በመጠቀም የነዋሪዎችን ችግር ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዩ መገንባቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

በዚህ የተጀመረውን የልማት ስራ ለማስቀጠል ህብረተሰቡ ርብርብ እንዲያደርግም ነው ዋና ስራ አስፈፃሚው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዩን በከፍተኛ ወጪ ያሰሩት የወረዳው ነዋሪ አቶ ህይወት መልኩ በበኩላቸው ቦዩ ከመሰራቱ በፊት ከፍተኛ የፍሳሽ ችግር እንደነበር አስታውሰው የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዩ መሰራት ለአካባቢው ንፅህና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያያትም አካባቢው ከፍተኛ የፍሳሽ አወጋገድ ችግር እንዳለበት ተናግረው ከመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በየአካባቢው የሚታዩ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታትና መሰል የልማት ስራዎችን ለማከናወን  እንደተዘጋጁ አረጋግጠዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

የቂርቆስ ክፍለከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

     ህዳር 1 2003 ዓ.ም              

 

 23/03/2003

የጤና ኤክስቴንሽን ሞዴሎች ተመረቁ

በጤና ኤክስቴንሽን በሞዴልነት የተመረጡ አባወራዎች የቤተሰቦቻቸውንና የራሳቸውን ጤና በመጠበቅ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ስኬታማ ለማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 4 ጤና ጽ/ቤት ለአራት ወራት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ዙሪያ ያሰለጠናቸውን ከ340 በላይ ሞዴሎችን አስመረቀ፡፡

በአጎና ሲኒማ አዳራሽ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይሉ ፀጋዬ እንደተናገሩት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ሞዴል የተባሉት ቤተሰቦች የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ጤና በመጠበቅ ፕሮግራሙን ስኬታማ ለማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡

ተመራቂ ሞዴል የሆኑት አቶ ካሳሁን መኮንን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ ያገኙት ስልጠና ብዙ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀው ወደፊትም ከቤታቸው እስከ ጎረቤታቸው የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም ሌላኛው ሞዴል ተመራቂ ወ/ሮ አበባየሁ ነጋሽ እንደተናገሩት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ ያገኙት ስልጠና ብዙ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው በመግለጽ ከዚሁ ስልጠና ባገኙት ግንዛቤ ሶስት ልጆቻቸውን የኤች አይ ቪ ምርመራ እንዳስመረመሯቸው ገልፀው ወደፊትም ከቤታቸው እስከ ጎረቤታቸው ድረስ ያገኙትን ልምድ ለማካፈል እንደሚተጉ ነው የገለፁት፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቡ

ጥቅምት 22 2003 ዓ.ም

የወጣቶች ሊግ ውይይት ተካሄደ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ለጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሽ አባላት የተዘጋጀ ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

የክፍለ ከተማው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ወጣት ሙሉቀን ሰብስቤ እንደተናገረው ይህ ኮንፈረንስ የተዘጋጀው ከዚህ ቀደም ተደራጅተው ነገር ግን በአፈፃፀም በርካታ ችግሮች ያሉባቸውን የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሽ ወጣቶችን ችግር ለመፍታትና  ሌሎች ፍላጎት ያላቸው ወጣቶችን ለማደራጀት ነው ፡፡

በተመሳሳይም ከተለያዩ አደረጃጀቶች ነፃ ከሆኑ ወጣቶች ጋር በኪራይ ሰብሳቢነት ዙሪያ ውይይት መካሄዱን ታውቋል፡፡ በዚህም ውይይቱ ላይ በሁለት ዙር ከ1000 በላይ  ወጣቶች መገኘታቸውን  ነው የተገለፀው፡፡

የስልጠናው ተሳታፊ ወጣት አበበ ሀይሌ እንደገለፀው ደግሞ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተደራጅተን እየሰራን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን ከአፈፃፀም አኳያ ብዙ ችግሮች ያሉብን እንደሆነና አሁን ግን በወጣቱ ኮንፈረንስ የሀሳብና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ምቹ አጋጣሚ ፈጥሮልናል ብሏል፡፡

ሌላዋ የስልጠናው ተሳታፊ ወጣት ህይወት አስፋው በበኩሏ በፓርኪንግ ስራ ላይ ተደራጅታ እየሰራች ሲሆን ከትራፊክና ከፖሊስ አባላት ጋር በቦታ ምክኒያት ግጭት እንዳጋጠማት በውይይቱ ችግሩ ይቃለላል ብለን እናስባለን ብላለች፡፡

ሪፖርተር

ብሩክ ሎቤ

ጥቅምት 21 2003 ዓ.ም

የጎዳና ተዳዳሪ የነበሩወጣቶን የወጣትማህበሩ የስራ ለማሰራት እያደራጀ ነው

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወጣት ማህበር ከክፍለከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤትና ፅዳት አስተዳደር ጋር በመተባበር ከ80 ለሚበልጡ ስራ አጥ ወገኖች የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ፡፡

የቂርቆስ ክፍለከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጉ እድሉ በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ሀገራችን ካሏት ሀብቶች አንዱ የሰው ሀይል ነው፡፡ ይህ የሰው ሀብት ደግሞ ወጣቱ በመሆኑና የሀገሪቷን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድም ስኬታማ እንዲሆን ወጣቶች ያላቸውን ጉልበትና እውቀት መጠቀም አለባቸው ብለዋል፡፡በዚህም የወጣቱ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችንም በቀላሉ መቅረፍ እንደሚቻል ነው የገለፁት፡፡

ወጣት ሂክማ የተባለች የስራ ዕድሉ ተጠቃሚ በሰጠችው አስተያየት ደግሞ ምንግስት ለስራ አጥ ወገኖች እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ ነው ብላለች፡፡ራሷንና ሀገረሯን ለመለወጥ መዘጋጀቷንም ገልፃለች፡፡

ሌላው የስራ እድሉ ተጠቃሚ ወጣት   ይህንኑ ሀሳብ ይጋራል ከዚህ ቀደም የጎዳና ተዳዳሪ እንደነበርና በተሰጠው የስራ እድል ህይወቱን ከዚህ በተሸለ ለመምራት መዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡

ወጣቶቹን በኮብልስቶን፤ በፅዳትና ደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ስራዎች ላይ ለማሰራት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፀው ደግሞ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሞቴ አባልና የክፍለ ከተማው ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ዮሀንስ አለሙ ነው፡፡ ወጣቱ እንዳለው በተፈጠረው የስራ እድል ወደ ከገቡት ውጪ ከ300 በላይ ወጣቶችን ለማሳተፍ ተቅዷል፡፡ ይህም ለወጣቶቹ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ ይሆናል ብሏል፡፡

ሪፖርተር----- ራዚቃ

ጥቅምት 21 2003ዓ.ም

 

በኤች.አይ.ቪና ስነተዋልዶ ዙሪያ ውይይት ተደረገ  

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ከክፍለከተማው ጤና ጽ/ቤት በኤች.አይ.ቪና ስነተዋልዶ ዙሪያ ከክፍለ ከተማው ወጣቶች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የውይይት መድረኩ በተዘጋጀበት ወቅት እንደተገለፀው ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በሀገራችን መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የበርካታ ወጣቶችን ህይወት ቀጥፏል፡፡ ወጣቱም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል ስለቫይረሱ በቂ እውቀት ቢኖረውም የስርጭቱን መጠን ግን መቀነስ አለመቻሉን ከመድረኩ ለማወቅ የተቻለው፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በሰጡ አስተያየት ደግሞ በሽታው ካለበት የስርጭት መጠን መቀነስ ያልቻለው ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩት ግለሰቦች ከጠባቂነት ማላቀቅ ባለመቻሉ ነው፤ህፃናት ላይ የሚደርሰውን የአስገድዶ መደፈር አደጋ መቆጣጠር ስላልተቻለ ነው የሚሉና በፃታ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት ሴቶችን ወደ ሌላ የስራ ዘርፍ እንዲገቡ አለመደረጉ ነው የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ከ200 በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ

ጥቅምት 21 2003ዓ.ም

ፖሊስና ህ/ሰቡ በጥምረት ሊሰሩ ይገባል ተባለ

በሀገራችን የተረጋገጠውን ሰላምና፤ዴሞክራሲ ለማስቀጠል ፖሊስና ህብረተሰቡ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የፖሊስ መምሪያ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውኑን ለክፍለከተማው ነዋሪዎች አቀረበ፡፡

ህዝባዊ ውይይቱ በኤግዚብሽን ማዕከል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት የቂርቆስ ክፍለከተማ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደቦጭ እንደተናገሩት ሀገራችን ያቀደችውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ሰላም አስፈላጊ ነው፡፡

በሀገሪቷ ያለውን ሰላምና ፀጥታ ለማስከበር ፖሊስ መንግስትና ህብረተሰቡ በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት፡፡ የእቅድ ውይይቱም ፖሊስ ፀጥታውን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳየት ያስችላል ብለዋል አቶ ሰለሞን፡፡

የክፍለከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አሳዬ አምባዬ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንዳሉት ደግሞ ከዚህ ቀደም በክፍለከተማ ደረጃ ብቻ የሚሰሩ የወንጀል መከላከል ስራዎች ወደ ጣቢያ በመውረዳቸው ህብረተሰቡ በቅርቡ አገልግሎቱን ለማግኘት ችሏል፡፡

ከአስተዳደር አካላት ጋር በመተባበርም ከ512 በላይ የሚሆኑ የጫትና ሺ ቤቶች ላ እርምጃ መወሰዱንም አመልክተዋል፡፡ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በጥምረት በመስራትም የሀገቷን ሰላም እንዲያስጠብቅ ጥሪቸውንም አስተላፈዋል፡፡

የክፍለተማው ነዋሪችም በሌሊት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ፖሊስ ክትትል ቢዲርግባቸው፤የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖች ከወንጀል ነፃ ለማድረግ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ቢደረግ የሚሉና ከፖሊስ ጋር በጋራ ለመስራት ተዘጋጅተናል የሚሉ አስተያያቶችን ሰንዝረዋል፡፡

ሪፖርተር ራዚቃ ዲኖ                     

 ጥቅምት 19 2003 ዓ.ም

 

የወረዳ 8 ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ውይይት አካሄደ

 

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በወረዳው ከሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር በጎዳና ላይንግድና አካባቢ ፀጥታ ዙሪያ ተወያየ፡፡

 

ውይይቱ በወረዳ8 ሁለገብ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ8 ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃፊ አቶ ሰፊው ምስጋናው እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗና ክፍለከተማችንም የመዲና እንደመሆኗና ክፍለከተማችንም የመዲናዋ እንብርት በመሆኗ ደረጃዋን የጠበቀች መሆን ይጠበቅባታል፡፡

በዚህም የከተማዋን ደረጃ ዝቅ የሚያደርጉ የጎዳና ላይ ንግድና በእግረኛ መንገድ ላይ የሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማስቆም በወረዳው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል፡፡በንግዱ ማህበረሰብም በህጋዊነት የያዘውን የንግድ ስፍራ ብቻ መጠቀም ለትራፊክ ፍሰቱ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ነው ያሉት፡፡

የካዛንቺዝ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር ግርማ ደመቀ በበኩቸው በአዲሱ የትራፊክ ህግ መሰረት የህገወጥ የጎዳና ላይ ንግድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የትራፊክ ፍሰቱን የተቃና ለማድረግ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ህጋዊ መንገድን ተከትለው ሊነግዱ እንደሚገባ ገልፀው ወንጀልን ለመከላከልም ከአስተዳደሩ ጋር በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰንዝረው ከመድረክ ምላስ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ/ብሩክ

ጥቅምት 19 2003 ዓ.ም

የክፍለከተማው አስተዳደር በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ

የቂርቆስ ክፍለከተማ አስተዳደር የአስተዳደሩን የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በየደረጃው ከሚገኙ የክፍለከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ገመገመ፡፡

በቂርቆስ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነማሪም አረጋዊ የየጽ/ቤቶቹን የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ሲቂርቡ እዳሉት በሩብ ዓመቱ በጠየና፤በትምህርት፤በገቢ፤በጥቃቅንና አነስተኛና ሌሎችም ዘርፎች አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

በዚህም በጤናው ዘርፍ የቲቪ በሽታን አስከፊ ገፅታ ለማስተማር በየጤና ጣቢዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጥና አክሞ ማዳን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በአስአንዱም ወረዳዎች ለሚገኙ ት/ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን በኢንፍሉዌንዛ ክትባት ዙያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፡፡

 

በክፍለከተማው በልማቱ ከሚነሱ ነዋሪዎች ጋር በልማቱ ዙያ በርካታ ውይይቶች ተካሂደው የምትክ ቦታና የኮንዶሚኒየም እጣ የማውጣት ስራ መሰራቱን ነው በሪፖቱ የተገለፀው፡፡

በሩብ ዓመቱ ካጋጠሙ ችግሮች መካከልም የግዢ ስርዓቱን ቀልጣፋ ለማድረግ የተደረገ ጥረት አለመኖር፤የኪረይሰብሳቢነት አመለካከት ጨርሶ አለመወገድም ይገኙበታል፡፡

የክፍለከተማው ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ በበኩቸው አመራሩ በከተማ ደረጃ በቁልፍ የተያዙ ተግባራትን ከግብ ለማድረስ የተጠናከረ ጥረት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

የኪራይሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ ጠፍቶ የልማታዊ አስተሳሰብ እዲኖርም ብርቱ ጥረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል አቶ ቢያ፡፡

ሪፖርተር

ራዚቃ/ብሩክ

 
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ 0913278575
 
መስከረም 12 2003ዓ.ም
የኤች.ኤን.ዋን ክትባት ስልጠና ተሰጠ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የጤና ማጎልበትና በሽታ መከላከል ዋና የስራ ሂደት በኤች.ዋን.ኤን.ዋን ክትባት ዙሪያ ለወረዳ ጤናና ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ለትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም ለወላጅ ተጠሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
ኤች.ኤን.ዋን ክትባት በኤች.ዋን.ኤን.ዋን ቫይረስ ለተያዙ ግለሰቦች የሚሰጥ ክትባት ሲሆን በሽታው በትንፋሽ የሚተላለፍና በዋናነት ነፍሰጡር እናቶችን የሚያጠቃ ነው፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የከተማ ጤና ኤክስቴንሽንና የጤና አጠባበቅ ትምህርትና የመረጃ ስርፀት ኦፊሰር ሰ/ር ትዕግስት ምትኩ እንደገለፁት በሽታው በአፍሪካ ብቻ በ35 ሀገሮች ላይ የታየ ሲሆን የ168 ሰዎችን ህይወትም ቀጥፏል፡፡
በሽታው በኢትዮጲያ ያደረሰው የሞት አደጋ እንደሌለ የገለፁት ኦፊሰሯ በትምህርት ቤቶች ላይ ክትባቱ መሰጠቱ የቫይረሱን ስርጭት በእጅጉ ይቀንሰዋል ነው ያሉት፡፡
በክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት የጤና ማጎልበትና በሽታ መከላከል ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ እንድሪያስ አልጋነህ በበኩላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫው የትምህርቱ ማህበረሰብ በቫይረሱ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡  ክትባቱ ለኤርፖርት ሰራተኞች፤ፖሊሶች፤ለጤና ድርጅት ባለሙዎችና ነፍሰጡር እናቶች እየተሰጠ እንደነበር አስታውሰው ለቫይረሱ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመቱት ህፃናት በመሆናቸው ክትባቱን በትምህርት ቤቶች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ አስታውቀዋል፡፡
ሰልጣኞች ክትባቱ ያለውን ፋይዳ ተገንዝበው ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተማር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡በእለቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ   0913049933
መስከረም 11/2002
የጤና ኤክስቴንሽን ትግበራ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡
በከተማ እየተተገበረ ያለው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በነዋሪዎች ጤና አጠባበቅ ላይ ለውጥ እይሳየ መምጣቱ ተገለጸ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 4 ጤና ጽ/ቤት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ፓኬጅ አንድ አካል በሆነው የኤች አይ ቪ ኤድስ የፈቃደኝነት የምክርና የምርመራ አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ፡፡
የምክርና የምርመራ አገልግሎቱ በወረዳው ግቢ ውስጥ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ460 በላይ ሰዎች ይመረመራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የክ/ከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር ካሰች ጥበቡ እንደተናገሩት የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጁን ተግባራዊ ለማድረግ በሁለተት ዙር የሰለጠኑ 120 ያህል የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በክ/ከተማው ተመድበው መረጃ የማሰባሰብ ስራቸውን አጠናቀዋል፡፡ የተመደቡት ነርሶችም እያንዳንዳቸው ስድሳ ሞዴል አባወራዎችን በመለየት የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጁን በተመለከተ ለሞዴሎቻቸው ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡እስካሁን በተደረገው ትግበራም አበረታች ለውጦች እየታዩ እንደሚገኙ ሲ/ር ካሰች ተናግረዋል፡፡
የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በኃይሉ ጸጋዬ በበኩላቸው የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ተግባራዊ መደረጉ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ክፍተኛ የግንዛቤ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡የፓኬጁ አንዱ አካል የሆነው የኤች አይ ቪ ኤድስ የምክርና የምርመራ አገልግሎትም በወረዳው እንዲሰጥ በማድረግ ፈቃደኛ የሆኑና ሞዴል አባወራዎች እንዲሁም ወጣቶች በምርመራው እንዲጠቀሙ ተደርጓል፡፡
ወ/ሮ ንግስቲ ገ/ህይወት በወረዳው ሞዴል ተብለው የተመረጡ ሲሆን የቤት አያያዛቸው የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀማቸውና ኑሯቸው በተማሩት ትምህርት መሰረት መቃኘታቸውን ይገልጻሉ፡፡
በእለቱ ኤች አይ ቪ ኤድስ የምክርና የምርመራ አገልግሎት ሲያደርጉ ያገኘናቸው አቶ ገ/ሚካኤል ገበየሁና ወ/ሮ እጅጋየሁ መልኬ እንደገለጹት በጤና ኤክስቴንሽን ትምህርቱ ካገኙት ግንዛቤ ተነስተው የኤች አይ ቪ ምርመራ ለማድረግ መነሳሳታቸውን ይገልጻሉ፡፡ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙም በኑሮአቸው የሚታይ ለውጥ እያመጣ እንዳለ አብራርተዋል፡፡    
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
መስከረም 10/2002
በቂርቆስ ክ/ከተማ የመዝናኛ ክበብ ተመረቀ
በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 8 የህዝብ ባላደራ ቦርድ በነባር ቀበሌ 27 ካዛንቺስ አካባቢ ያሰራውን የህዝብ መዝናኛ ክበብ አስመረቀ፡፡
መዝናኛ ክበቡ ከአንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር የሚሆነው ከቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡
ክበቡን መርቀው የከፈቱት የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘርዓይ ካህሳይ እንደተናገሩት መዝናኛ ክበቡ በዓካባቢው መከፈቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ለወጣቶች የሚኖርው ጠቀሜታ በቀላል የሚገመት አይደለም፡፡በመሆኑም የወረዳው አስተዳደር ለባላደራ ቦርዱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የመዝናኛ ክበቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገሰሰ አበበ በበኩላቸው መዝናኛ ክበቡ የአካባቢውን ነዋሪ ህብረተሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ የምግብ የመጠጥና የካፍቴሪያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ካዛንቺስ የንግድና የከፍተኛ እንቅስቃሴ አካባቢ መሆኑን ያብራሩት ስራ አስኪያጁ በአብዛኛው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን የመዝናኛ ፍላጎት ለማሟላት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የባላደራ ቦርዱ የሂሳብ ሹም የሆኑት ሻምበል ብርሀኑ ይልማ ስለ ክበቡ በሰጡት ማብራሪያ በወረዳው የሚገኙ ሁሉም ነባር ቀበሌዎች የየራሳቸው መዝናኛ ክበብ ሲኖራቸው ቀበሌ 27 በመባል የሚታወቀው ነባር ቀበሌ ብቻ የራሱ መዝናኛ ክበብ ሳይኖረው ቆይቷል፡፡ ባላደራ ቦርዱ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦችንና የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አቅርቦቶችን ለአካባቢው ነዋሪዎች በማቅረብ ከሚያገኘው ገቢ ለትምህርት የውስጥ ለውስጥ መንገድና በተለያዩ የልማት ስራዎች ይሳተፋል፡፡ አሁንም ከክበቡ በሚገኘው ገቢ ባላደራ ቦርዱ የነባር ቀበሌዎችን ልማት የማገዙን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ


መስከረም 10 2002 ዓ.ም
የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ
ሀገርዓቀፍ የሰንደቅ አላማ ቀንን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና በአዲስ አበባ ስታዲየም በደማቅ ስነስርዓት ተከበረ፡፡
የኢትዮጲያዊያን የተጋድሎ አርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን ድህነትን ድል በመንሳት ለቀጣዩ ትውልድ በኩራት እናወርሳለን! በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዓል ላይ የምስራቅ ጎህ ርዕሰ መምህር አቶ ዝናቡ ሐጎስ እንደተናገሩት 3ኛውን የሰንደቅ አላማ ቀን ስናከብር በሀገራችን ፌደራላዊና ዴሞክራሲያዊ አንድነት በመፍጠር የጋራ መግባባታችንን ለማጠናከር ቃል መግባት ይጠበቅብናል፡፡
ቀኑ ተመፅዋችነትን በማስወገድ የሰንደቅ ዓላማችንን ክብር የምንጠብቅበት መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መምህሩ ተማሪዎች በትምህርታቸው በመበርታት ለሀገራቸው እድገት እንዲተጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሰንደቅ አላማ ቀኑን በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኝነተው ካከበሩ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ደግሞ አባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማውን ለማውረስ  ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል እኛም በትምህርታችን የተሻልን በመሆን ለሀገራችን እድገት የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡
በዓሉ ከጠዋቱ 4፤30 ሰንደቅ ዓላማውን በመስቀል ስነስርዓት ተጠናቋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ /ታሪኩ እንዳለ
መስከረም 08 2002 ዓ.ም
የየወረዳዎች አስቸኳይ ምክር ቤት አካሄዱ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ2፤4ና 7 ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባኤቸውን አካሄዱ፡፡
የወረዳዎቹ ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤያቸውን ያካሄዱት የ2003 መሪ ዕቅድን ከምክር ቤት አባላት ጋር ለመወያየትና አዳዲስ ሹመቶችን ለማፅደቅ ታስቦ ነው፡፡
በየወረዳዎቹ ጉባኤዎች በተካሄዱበት ወቅት እንገተገለፀው ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላት የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የየወረዳዎቹ የ2003 መሪ ዕቅድም በሀገሪቷ የታቀደው የ5ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽ ዕቅድ አንዱ አካል መሆኑን ነው መሪ ዕቅዱን ያቀረቡት የየወረዳዎቹ ዋና ስራአስፈፃሚዎች ያስገነዘቡት፡፡
እቅዱ ገቢ፤ትምህርት፤ጤና፤ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም፤መሬትና ጥቃቅንና አነስተኛን እንደቁልፍ ተግባር ይዞ የተቀረፀ መሆኑም ተገልጧል፡፡
አንዳንድ የወረዳ 7 የምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት ደግሞ ዕቅዱ ሊያሰራ የሚችል መሆኑን ገልፀው ለስኬታማነቱ የምክር ቤት አባላት በስፋት ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
መስከረም 6/2002 ዓ.ም
የሲቪል ሰርቪስ ተግብራትን በማጠናከርና ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ልማትና መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር የ2003 ዓ.ም ጥቅል እቅዱን ለግንባር ቀደም ፈጻሚዎች አስተውቋል፡፡
ውይቱ ሲካሄድ የክ/ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የፍትህና ህግ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደቦጭ እንደተናገሩት በ2002 ዓመተ ምህረት የስራ ዘመን በተደረገው የአፈጻጸም ግምገማ ደካማ ጎኖችን በመለየት ከላይ እስከታች ባሉ አመራሮችና ፈጻሚዎች የእርምት እርምጃ ተወስዷል፡፡
በ2003 ዓ.ም የስራ ዘመንም በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፎች በሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ተግባራት በትምህርት በገቢና በመሬት አስተዳደር ዘርፎች የተጠናከረ ስራ ለመስራት ታቅዷል፡፡ በየሶስት ወሩም የአፈጻጸም ግምገማ በማድረግ መታረም የሚገባቸውን ደካማ ጎኖች በማረም ጠንካራ ጎኖችን በማስፋፋት እርማት ይደረጋል፡፡
ፋጻሚ ሰራተኞች የአገልጋይነት ስሜት ኖሯቸው አገልግሎት ፈላጊው ህብረተሰብ የሚፈልገውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በእቅዱ ዙሪያ ውይይት መደረጉ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ተገልፃDል፡፡
አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የ2003 እቅዱ ሊያሰራ በሚችል መልኩ የተቀረጸ መሆኑን ገልጸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና አንዳንድ የህዝብ ተቋማትን እንዲሁም የህብረተሰቡን ሙሉ አቅም ለልማት ለመጠቀም የተያዘው ዕቅድ በይበልጥ ሊዳብር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ግንባር ቀደሞችን በማወያየት የተጀመረው የ2003 ዓ.ም እቅድ ውይይት በቀጣነትም ከነዋሪዎች ከወጣቶችና ከሴቶች ፎረሞችና አደረጃጀቶች እንዲሁም የክ/ከተማው ምክር ቤት አባላትም በእቅዱ ላይ እንደሚወያዩ ከክ/ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75


03/13/2002
የወጣቶች የክረምት ስፖርት ውድድር ማጠቃለያ
 
   በየደረጃው የሚሰጡ ስፖርታዊ ስልጠናዎችና ልምምዶች በአገሪቱ ቀጣይነት ያላቸው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ተገለፀ፡፡
   በቂርቆስ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽቤት ለሁለት ወራት ሲካሄድ የቆየው የክረምት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ስፖርታዊ ውድድር የማጠቃለያ በዓል ተካሂዷል፡፡
   ፕሮግራሙ ሲካሄድ የክ/ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጉ እድሉ    እንደተናገሩት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቶች በአካባቢያቸው የሚታዩ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ያላቸውን ጊዜና ጉልበት እውቀት ተጠቅመው ለአገራቸው የሚያበረክቱት በጎ አስተዋፅኦ ነው ብለዋል፡፡
    የክ/ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምላኩ ተበጀ በበኩላቸው ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ከአልባሌ ቦታ ተቆጥበው በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መታቀፋቸው አካላዊ አእምሮአዊና መንፈሳዊ ጥንካሬያቸውን ለማጎልበት ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡
    በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ በሩጫ ውድድር የተሳተፉት ወጣት አዲስ መላኩ እና ወጣት ህይወት ገ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ወጣቶች በክረምቱ ወቅት የስፖርት ስልጠና መሰጠቱ ወጣቶቹን በአካልና በአዕምሮ ጠንክረው በቀጣይነት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
    ስፖርታዊ ውድድሩ በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች ለሁለት ወራት ሲሰጥ የቀቆየ ሲሆን ከ1300 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሰልጥነውበታል፡፡ በዕለቱም የቴኳንዶ የቅርጫት ኳስ አትሌቲክስና የቴኒስ ጫወታ ትርዒቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን በውድድሩ ለተሳተፉ ስፖርተኞችና አሰልጣኞች የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
 ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
03/13/2002
የሩዋንዳ ዘማቾች ማህበር ለታጋይ ቤተሰብ እርዳታ አደረገ
   ወላጆቻቸው በጦርነት የተሰውባቸው ቤተሰቦችን በመደገፍ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ማገዝ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
    በቂርቆስ ክ/ከተማ የሩዋንዳ ዘማቾች ማህበር በጦርነት ለተሰዉ ታጋይ ቤተሰቦች የትምህርት ቁሳቁስ እርዳታ አድርጓል፡፡
    ዕርዳታው ለተማሪዎቹ በተሰጠበት ወቅት የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ገ/መድህን አርአያ እንደተናገሩት ማህበራቸው ድህነትን ጦርነትንና አለመግባባትን ለመታገል ለአፍሪካ መስዋዕትነት በከፈሉ አባላት የተቋቋመ ነው፡፡ አፍሪካ የመቻቻል የሰላም የፍቅርና ለዜጎቿ የተመቸች እንድትሆን ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጥረት ማህበራቸው እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡
     የማህበሩ አባላት በትግል ወቅት የተሰዉ ጓዶቻቸውን ልጆች ተንከባክቦ ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ ካላቸው በመቀነስ ለ2003 የትምህርት ዘመን የመማሪያ ቁሳቁስ አበርክተውላቸዋል፡፡
    የኢፌድሪ ትምህርት ሚ/ር ተወካይ አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ማህበሩ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው በዕለቱ እርዳታ የተደረገላቸው ተማሪዎች የወላጆቻቸውን ጀግንነት እያሰቡ ለትምህርታቸው ትልቅ ትኩረት እንዲሰጡ አደራ ብለዋል፡፡
     የታጋይ ቤተሰቦች የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አምሳሉና ተማሪ ሚኪያስ ደረጀ ማህበሩ ባደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
    አርቲስት ይነበብ ታምሩ በኪነጥበብ ሙያ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተመሳሳይ የበጎ ስራ አድራጎትን በመደገፍ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
ጳጉሜ 01 2002 ዓ.ም
የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አወጡ
 
      በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በሸራተን ማስፋፊያ ፕሮጀክት ከሚነሱ የልማት ተነሺዎች መካከል የጤና ችግር ላለባቸውና አቅመ ደካማ እንዲሁም አካል ጉዳተኛ የሆኑ የልማት ተነሺዎች የኮንዶሚኒየም እጣ አወጡ፡፡
      በቂርቆስ ክፍለከተማ የመሬት ልማት ባንክና ከተማ ማደስ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ሳላህ እንደገለፁት ፕሮግራሙ በ9 ሳይቶች ላይ በሚገኙ የመጀመሪያው ወለሎች ላይ ለሚገቡ የልማት ተነሺዎች የሚደረግ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ነው፡፡
     በሸራተን ማስፋፊያ ከሚነሱ ነዋሪዎች መካከል በአቅመ ደካማ ለሆኑና የጤና ችግር ላለባቸው ሲሆን በማስፋፊያው ከሚነሱት ነዋሪዎች መካከል 92 የሚሆኑ ነዋሪዎች እየተስተናገዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
     እጣ ያወጡት ነዋሪዎች በክፍለ ከተማው ቤቶች ማስተላለፍ ጋርናመሬት ልማት ባንክ ጽ/ቤት ጋር ሰርተፊኬት በመውሰድ በሚያወጣው ማስተወቂያ አማካኝነት መመዝገብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ህብረተሰቡ ለልማቱ ያሳየውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው አቶ ጀማል የጠየቁት፡፡
     አንዳንድ እጣ ያወጡ የልማት ተነሺዎች ከሰጡት አስተያየት መካከል ልማቱን በመደገፍ በተሰጠን ቤት ለመኖር ተዘጋጅተናል፤ቤቱ ከቤተሰቦቻችን ቁጥር ጋር አይመጣጠንም፤ካሬ ሜትሩ ጠባብ ነው የሚሉና ቅድመ ክፍያው በሁለት ግዜ እንድንከፍል ቢደረግልን የሚሉት ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
የወጣቶች ሊግ ጉባዔ ተካሄደ
 ነሐሴ 30/2002
    ወጣቶችን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች እንዲሳተፉ ማድረግ የተጀመሩትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡
    በቂርቆስ ክ/ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የኢህአዴግ ወጣት ሊግ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ተካሂዷል፡፡
     በወረዳ 4 በተካሔደው ጉባዔ የወረዳው የኢህአዴግ ወጣት ሊግ ሰብሳቢ ወጣት ዮሐንስ ገብሬ እንደተናገረው ሊጉ በተጠናቀቀው 2002 ዓመተ ምህረት በርካታ አበረታች ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ምርጫ 2002 ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጎላ ስራ ሰርተቷል ፡፡ ወጣቱ በነቂስ ወጥቶ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ ከማድረግና በምርጫ ዕለትም ይበጀኛል ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመርጥ የመቀስቀስ ስራ ሰርቷል፡፡
      በወረዳ 7 በተካሄደው የወጣት ሊግ ጉባዔ የወረዳው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ክንፉ እንደተናገሩት ወጣቱን አሰባስቦ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲያደርግ በማገዝ በአገራችን የተጀመረውን የልማት የዲሞክራና የመልካም አስተዳደር ጅምር አጠናክሮ ማቀጠል ይቻላል ፡፡
      ወጣቱን ያገለለ እድገት ቀጣይነት ሊኖረው አይችልም ያሉት አቶ ዮሴፍ ጤናማ የሆነ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ ወጣቱን አስተባብሮ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት ፡፡
      በተመሳሳይም በወረዳ 1 እና በወረዳ 8 የወጣቶች ሊግ ጉባዔ የተካሄደ ሲሆን የ2002 ዓመተ ምህረት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2003 ዓመተ ምህረት ዕቅድ ለአባላት ቀርቦ ተወያየውተው አጽድቀዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
0913278575
 

 
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  
  ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
መምረጥ የዜግነት መብት ነው!
 
Facebook 'Like' Button  
 
 
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free