የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
ቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  
  HOME
  ቂርቆስ ዜናዎች
  አጫጭር ዜናዎች
  kirkos
  በክፍለ ከተማው የሚሰጡ አገልግሎቶች
  ዜና
  About Kirkos InformationOffice
  ቀበሌዎች
  ዜናዎቻችን
  ቂርቆስ ዜና
ዜናዎቻችን
 
 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የሚዘጋጅ የየቀኑ ዜናዎች

ነሐሴ 03 2002 ዓ.ም

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ለቴክኖሎጂ ሽግግር የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ተገለፀ፡፡በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ስር የተደራጀው ሀብታሙ ዘመናዊ የዳቦና የኬክ ማሽን ጠቅላላ የፈጠራ ውጤቶች ማህበር የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችና የቆሻሻ ገንዳዎችን እያመረተ መሆኑን ተመለክቷል፡፡
የተቋሙ ዋና ኃላፊ አቶ ሀብታሙ በላቸው እንደተናገሩት ማህበሩ በውጪ ሀገራት የተሰሩ የዳቦና የኬክ ማሽኖችንና ሽንኩርት መፍጫዎችን የሀገር ውስጥ ዕቃዎችን በመጠቀም ይሰራል፡፡ 7 የቆሻሻ ገንዳዎችንና 66 የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን ሰርቶ ለማስረከብ መዘጋጀቱን ነው አቶ ሀብታሙ የገለፁት፡፡
የቦታ ጥበት እንደገጠማቸው የሚናገሩት አንቀሳቃሹ የቦታ ችግሩ ቢቀረፍ ከዚህ የበለጠ መስራት እንደሚቻሉ ነው የተናገሩት፡፡

የወረዳ 10 የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ዳነቾ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት የተሰራው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎችና ሌሎች ማሽኖች በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መሰራቱ ዘርፉ ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ያሳያል ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሻፊም ይህንኑ ሀሳብ ይጋራሉበዘርፉ የተሰማሩ አንቀሳቃሾች የሚሰሯቸው የፈጠራ ውጤቶች የውጪ ምንዛሪን ለማስቀረትም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው በመግለፅ፡፡
ሪፖርተር

ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ነሐሴ 03 2002 ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 01;02;03;04;05;06;08ና10 ምክር ቤቶች 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን አካሄዱ፡፡

የወረዳ ምክርቤቶቹ ጉባኤያቸውን የ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ቃለጉባኤን በማፅደቅ የጀመሩ ሲሆን የ2002 በጀት ዓመትን የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት አዳምጠው ተወያይተውበታል፡፡
በወረዳ 01 በተካሄደው ምክር ቤት የ2002 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ሲቀረብ እንደተገለፀው የማስፈፀም አቅም ግንባታን እንደቁልፍ ተግባር በመውሰድና የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ትግበራ እንዲቀጥል በማድረግ ህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል ስራ ተከናውኗል፡፡
በወረዳው ለ579 ሰዎች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን 2 ማህበራትንም ሞዴል ማድረግ መቻሉን
ነው ሪፖርቱ ያመለክተው፡፡
ጉባኤው ወረዳዎቹ በትምህርት፤ዲዛይንና ግንባታ፤ በስራአስኪያጅ፤በወጣቶችና ስፖርትና ሌሎችም የስራ ዘርፎች የተሰሩ ተግባራት በዝርዝር ያቀረቡበት፤አባላት
ጥያቄዎቻቸውን ያነሱበትና ተገቢውንም ምላሽ ያገኙበት ነበር፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ 0913049933
ሐምሌ 26 2002 ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ስር የተደራጁ 4 የፓርኪንግ ኢንትፕራይዝ አባላት 1ኛ ዓመት ምስረታ በዓላቸውን አከበሩ፡፡
በወረዳ 8 ስር የተደራጁት ማህበራት 1ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን ባከበሩበት ወቅት የወረዳ 8 የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ሀብቱ 
የፓርኪንግ ስራው ከባለሀብቱ ይልቅ አንቀሳቃሾች ተደራጅተው እንዲሰሩት መደረጉና በስራው የተሰማሩ ግለሰቦች ሂሳባቸውን በቁጠባ መያዛቸው ውጤታማ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል፡፡  

የክፍለከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ዘሪሁን ታዬ እንደተናገሩት ደግሞ በክፍለከተማው በፓርኪንግ ስራ ላይ የተደራጁ 27 ኢንተርፕራይዞች ይገኛሉ፡፡
ከ630 በላይ አንቀሳቃሾች በዘርፉ እንደተሰማሩ የተናገሩት የስራ ሂደት ባለቤቱ በወር ከ500-850 ብር ክፍያ እንደሚያገኙም ገልፀዋል፡፡ ጽ/ቤቱ ስልጠናዎችንና ሌሎች ድጋፎችን በመስጠት ከጎናቸው እንደሚቆምም አረጋግጠዋል፡፡

በዓላቸውን በማክበር የነበሩት አንቀሳቃሾች በበኩላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ለዘርፉ ያላቸው ዝቅተኛ አመለካከትና በአንቀሳቃሾች በኩል ዘርፉ ውጤታማ አይሆንም የሚል ስጋት በ1ዓመት ጊዜ ውስጥ ያገጠሙ ችግሮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ዓመታት ግን የተሻለ ስራ በመስራት ከትራፊክ ፖሊሶች
ጋር በመቀናጀት የትራፊክ ማሳለጥና ፀጥታን የማስጠበቅ ስራችንን እናጠናክራለን ብለዋል፡፡ 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሐምሌ 26 2002 ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ግብር ለመክፈል የመጡ አንዳንድ ግብር ከፋዮች ግብር መክፈል በሀገራችን ላይ እየተሰሩ ያሉ የልማት ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑን ገለፁ፡፡
አቶ ብሩክ ካሳሁን ይባላሉ በክፍለ ከተማ ግብር ለመክፈል ከመጡ ግብር ከፋዮች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚት ከሆነ ግብርን መክፈል የህክምና ተቋማትና ሌሎች ህዝቡን ተጠቃ የሚዲርጉ ስራዎ እንዲስፋፉ ማስቻል ማለት ነው፡፡
በሌሎች ሀገራት የሚየውን ዓይነት እድገት ለማምጣት ግብር መክፈል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳው የተናገሩት ግብር ከፋዩ ግብር ለሀገር ያለው ጠቀሜታ በስፋት ባለመተዋወቁ ግብር ከፋዩ በግ
ዴታ እንጂ በፍቃደኝነት ለመክፈል አይፈልግም ብለዋል፡፡ 
ህብረተሰቡን የማስተማሩ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመጠቆም፡፡
አቶ ተክላይ የተባሉ ሌላኛው ግብር ከፋይ በበኩላቸው በርከታ በርካታ ግብር ከፋዮች የግብር መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ ሲል ይመጣሉ ይህ ደግሞ መጨናነቅንና ግዜ ማባከንን ስለሚያስከትል ቀደም ብለው በመክፈል ግዜያቸውን እንዲቆቡ መክረዋል፡፡
መክፈያ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኃላ ከሚጣለው ከፍተኛ መቀጫ ለመዳን በወቅቱ እንዲከፍሉ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሐምሌ 23 2002 ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለከተማ የወረዳ 9 ገቢዎች ጽ/ቤት በ2002 በጀት ዓመት ከ4ሚሊዮ
ን ብር በላይ በመሰብሰብ የዕቅዱን 95 በመቶ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡ለ2003 በጀት ዓመትም ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር ሀብቴ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ በ2002 በጀት ዓመት ከ5 ሚሊዮን 550 ሺ ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ከ4 ሚዮን 900 ሺ ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 95 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡
ገቢው የተሰበሰበው ከቦታና ቤት ግብር፤ከደሞዝ ገቢ ግብርና ከሌሎች የግብር ዓይነቶች መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዋ 35 ግብር ከፋዮችን የተጨማሪ እሴት ተመዛጋቢ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ጽ/ቤቱ በ2003 በጀት ዓመት ሊሰበስብ ያቀደው ከ11ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን ገቢው ከሌሎች የግብር ዓይነቶች በተጨማሪ አዳዲስ የቀን ገቢ ግምትና አዲስ ወደ ንግዱ ከሚገቡ ግብር ከፋዮች ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው ወ/ሮ አስቴር የገለፁት፡፡
በወረዳው የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ያለባቸውን ግብር ከሐምሌ1-
30 ድረስ መክፈል እንዳለባቸው ገልፀው ግብር ከፋዮች ወቅቱን ጠብቀው በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ሐምሌ 22 2002 ዓ.ም
በኤች.ይ.ቪና ስነተዋልዶ ትምህርት (በጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ) 
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር(ወወክማ) ጋር በመተባበር በኤች.አይ.ቪና ስነተዋልዶ ዙሪያ ወጣቶችን በማሰልጠን ላይ ነው፡፡ 
በክረምት የበጎ ፈቃድ መርህ ግብር ውስጥ ከተካተቱ ተግባራት መካከል በኤች.አይ.ቪ ኤድስና ስነተዋልዶ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት አንዱ ሲሆን የበጎ ፈቃድ ትምህርቱ በክፍለ ከተማው ትምህርት ቤቶች መሰጠት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ1000 በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወጣት ኤልያስ ወልዴ እንደገለፀው በኤች.አይ.ቪና ስነ ተዋልዶ ዙሪያ የሚሰጠው የአቻለአቻ ስልጠና እድሜያቸው ከ10-29 የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
የስልጠናው ዋነኛ አላማም ወጣቶች እርስበእርሳቸው በመወያየት በኤች.አይ.ቪና በስነተዋልዶ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት እንደሚያስችል መሆኑን ገልፃDል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫውን ይሰጡ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ወጣት ማህሌት አበበ በበኩሏ ስልጠናው የወጣቶችን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ የኤች.አይ.ቪን ስርጭት ለመግታት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፃለች፡፡
ትምህርቱን ሲከታተሉ የነበሩት ወጣት ስመኝና ወጣት አዱኛ ስልጠናው ጥሩ ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸው ገልፀው ወጣቶች በኤች.አይ.ቪና ተዛማጅ ችግሮች እንዳይጋለጡ እራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል ነው ያሉት፡፡ ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ትምህርት በአግባቡ እንዲተገብሩት በመጠቆም ጭምር፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ 0913049933

ሐምሌ 20 2002 ዓ.ም
የትምህርት ጉባኤ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2002 ዓ.ም ትምህርት ጉባኤውን አካሄደ፡፡
ጉባኤው በተካሄደበት ወቅት በክፍለከተማው የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን አመታዊ የትምህርትዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በተማሪ ትምህርት ጥመርታ፤በትምህርት ጥራት ፓኬጅ አተገባበርና በትምህርት ልማት ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎና የተማሪዎች ውጤት በሪፖርቶቹ ከተዳሰሱ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የተሻለ ደረጃ ያላቸው ተማሪዎችን ማበረታት፤አመራር ኮሚቴዎች በየትምህርት ቤቶቹ ክትትል ማድረጋቸውና በትምህረት ቤቶች መካከል ጥያቄና መልስ ውድድሮች መካሄዳቸው በየትምህርት ቤቶቹ ለተገኙ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ምክኒያቶቹ መሆናቸውም ተገልጧል፡፡
ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በመምህራን ክትትልና ድጋፍ መደረጉም ርዕሳነ መምህራኑ በሪፖርታቸው የገለፁት ነው፡፡
በክፍለ ከተማው በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የቤተ ሙከራ አለመሟላት፤የመፅሀፍት እጥረትና የኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል አለመኖር እንደችግር የቀረቡ ሀሳቦች ናቸው፡፡

ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
 
ሐምሌ 19 2002 ዓ.ም
 
የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት
በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የሚሰጠው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እንዳስደሰታቸው አንዳንድ ተማሪዎች ገለፁ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አብዮት እርምጃ ትምህርት ቤት የማጠናከሪያ ትምህርታቸውን በመከታተል የሚገኙ ተማሪዎች እንደገለፁት ወደ መደበኛ ትምህርት ከመግባታችን በፊት የምንወስደው የማጠናከሪያ ትምህርት የበጋ ትምህርታችንን ቀላል ያደርግልናል፡፡
መምህራኖቹ ወጣት በመሆናቸው የምንፈልገውን ጥያቄዎች በቀላሉ ማቅረብ እንችላለን ነው ያሉት ተማሪዎቹ፡፡ እነሱም በትምህርታቸው ጠንክረው ወደፊት በዚሁ የበጎ ፈቃድ ተግባር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው በመግለፅ፡፡
ከ8ኛ-11ኛ ክፍል የባይሎጂና የኬሚስትሪ ትምህርት በመስጠት ላይ ያለችው ወጣት መምህርት ኢትዮጲያ መንግስቱ በበኩሏ የበጎ ፈቃድ ትምህርቱ ያለንን እውቀት የማካፈል ባህል እንድናዳብር ያስችለናል ብላለች፡፡ ሌሎች ወጣቶች የበጎ ተግባሩ ተቋዳሽ እንዲሆኑም ወጣት ኢትዮጲያ መክራለች፡፡
በክፍለ ከተማው የበጎ ፈቃድ ተግባራቱ በ9 ጣቢያዎች ተከፋፍሎ እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለፀው ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የቂርቆስ ክፍለከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ዮሀንስ አለሙ ነው፡፡
ከ4ኛ-12ኛ ክፍል በሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ላይ 17 መምህራኖች ሲኖሩ ከ600 በላይ ተማሪዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡
በወጣቶች የበጎ ፈቃድ ስራዎቹ በማጠናከሪያ ትምህርት፤ስፖርት፤ችግኝ ተከላ ፤ፅዳት፤መልካም አስተዳደርና ሰብዓዊ መብት መሆናቸውንም ጨምሮ ገልጧል፡፡ 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ - 0913049933
ሐምሌ 19 2002 ዓ.ም
መልሶ ማልማት
አዲስ አበባን ለማልማት በሚደረገው ጥረት የልማት ተነሺዎችና የሚመለከታቸው አካላት ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በመልሶ ማልማት የሚነሱ አካባቢዎችን የማፅዳት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የወረዳው ዋና ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል፡፡ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ታምራት ተስፋዬ እንደተናገሩት በተለምዶ ሰንሻይን ጀርባ እየተባለ የሚጠራውን አካባቢ መልሶ በማልማት በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎችም እንደፍላጎታቸው ምትክ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደተሰጣቸው አመልክተዋል፡፡
አንዳንድ በአካባቢው በሚገኙ ቤቶች ለሶስተኛ ወገን ክራይ እየከፈሉ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦች ያለምንም ህጋዊ ማስረጃ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የተንቀሳቀሱ ግለሰቦች እንደነበሩ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ፡፡ ግለሰቦቹ ጥገኛ ነኝ በማለት ቤት ለማግኘት የይገባኛል ጥያቄ ማንሳታቸውን ተናግረዋል፡፡
 ህጋዊ መስረጃ ያቀረቡና ባለቤትነታቸውን ያረጋገጡ ባለይዞታዎችና በጥገኝነት የሚኖሩ ሰዎችም ምትክ ቤት ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡በመልሶ ማልማት ሂደቱ 3.2 ሄክታር መሬት የሚለማ ሲሆን 215 የሚሆኑ ቤቶች ይነሳሉ፡፡ ከነዚህም 166 የሚሆኑት የቀበሌ ቤቶች ሲሆኑ 40 የግል ቤቶችና 9 የኪራይ ቤቶች ቤት እንዲሁም መጠለያዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
እስካሁን በተደረገው ዘመቻም ከአንድ መቶ በላይ ቤቶች መነሳታቸው የተገለፀ ሲሆን ቀሪዎቹን ቤቶች የማንሳት ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ -0913278575

ሐምሌ 16 2002ዓ.ም
የቂርቆስ ክፍለከተማ ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት በ2002 በጀት ዓመት ከ11 ሺ በላይ ለሚሆኑ ስራ አጦች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ፡፡
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሻፊ እንደገለፁት በ2002 በጀት ዓመት ለ5,948 ሰዎች ቋሚ የስራ ዕድል ሲፈጠር ለ5,655 ስራ አጦች ድግሞ ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ጋር በጥምረት በመስራት አንቀሳቃሾቹ ከ16.5 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር እንዲያገኙ መደረጉን የገለፁት ኃላፊው 6,167 አንቀሳቃሾች በተፈጠረላቸው የገቢያ ትስስርም ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት ችለዋል ብለዋል፡፡
55 ሞዴል አንቀሳቃሾች ተመርጠው አስፈላጊው ድግፍና ክትትል ተደርጎላቸው ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ እንደሚገቡ አቶ ነስረዲን አስረድተዋል፡፡
በክፍለ ከተማው የጥርብ ድንጋይ ንጣፍ ስራ የታቀደውን ያህል ባይሆንም ዘርፉን የተቀላቀሉና ውጤታማ የሆኑ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን ገልፀው በዘርፉ ዙሪያ ያሉ የተዛቡ አስተሳሰቦችን መቀየር እንደቁልፍ ተግባር መያዙን ነው የገለፁት፡፡በ2003 በጀት ዓመት በ6ቱ የእድገት ተኮር የስራ ዘርፎች ከ5ሺ በላይ ለሚሆኑ ስራአጦች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ሐምሌ 15 2002ዓ.ም
 
የወጣት ማዕከል ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ተመለከተ፡፡ 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የወጣት ማዕከል በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ተመለከተ፡፡ማዕከሉ ሙሉ በሙሉ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው በጀት እንዲለቀቅም የግንባታው ሱፐርቫይዘሮች ጠይቀዋል፡፡
በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘው ባለ 2 ፎቅ ህንፃ ወጣት ማዕከል የግንባታው ተቆጣጣሪ መሀንዲስ አቶ ቴዎድሮስ ታጠቅ እንደገለፁት ግንባታው የተጀመረው በባለአደራው አስተዳደር ሲሆን በግብዓት አለመሟላት፤በጀት በወቅቱ አለመለቀቅና ቋሚ የሆነ ዲዛይን አለመኖር ማዕከሉ መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ እንዲዘገይ አስችሎታል፡፡
ግንባታውን ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚቻል የገለፁት መሀንዲሱ በበጀት መዘግየት ምክኒያት በታለመለት ጊዜ ላይጠናቀቅ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡በልስን ላይ ያለው ወጣት ማዕከል ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን በጀት የሚገኝበት መንገድ እንዲመቻች በመጠየቅ ጭምር፡፡
በወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ወጣቶችን በስፖርት የማሳተፍና የማልማት ኦፊሰር አቶ ጌቱ የማነህ በበኩላቸው የወጣት ማዕከሉ በጊዜው እንዲጠናቀቅ የተደረጉ ግፊቶች መኖራቸውን ገልፀው ማዕከሉ ሲጠናቀቅ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችንና የሰው ሀይል ለማሟላት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
ወጣት ማእከሉ የቤተመፅሀፍት፤ካፍቴሪያ፤የአይሲቲ ማዕከልና አዳራሽ እንደሚኖሩትም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ሐምሌ 11/2002
ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ
በቂርቆስ ክ/ከተማ በሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በ2002 ዓ/ም ዕቅድ ክንውንና በ2003 ዕቅድ ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት ተካሔደ፡፡
በወረዳዎቹ በተካሄደው ውይይት ላይ የየወረዳዎቹ ዓመታዊ ክንውን ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በአካባቢው ነዋሪዎች አስተያየት ተሰጠጥቶባቸዋል፡፡
በወረዳ 4 በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ላይ የወረዳው ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ንጉሱ እንደተናገሩት የወረዳው አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራት በህዝብ ማስገምገም ያስፈለገው ከ2002 ዕቅድ ክንውን ተነስቶ የ2003 ዓመተ ምህረትን የስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንዲያስችል ነው፡፡
የወረዳ 9 ህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ጸጋዬ ገ/ማሪያም በበኩላቸው በወረዳቸው በበጀት ዓመቱ የተከናወኑት የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት አበረታች ነበሩ፡፡ 4ኛው አገራዊ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን የአካባቢው ህብረተሰብ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም በወረዳዎቹ የተከናወኑት ተግባራት አበረታችና ተጠናክረው ሊቀጥሉ የሚገባ ቢሆኑም በጽዳት በጸጥታና መልሶ ማልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ትኩረት ሰጥቶ ማየት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ከተወያዮቹ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በወረዳ 4 በተካሔደው ውይይት የወረዳው ፖሊስ ዓመታዊ ክንውን ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን በህዝብ አስተያየት ተስጥቶበታል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም በወረዳ 6 7 እና ወርዳ10 ተመሳሳይ ውይይቶች ተካሂደዋል
ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
 ሐምሌ 1/2002
በመልሶ ማልማት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
መንግስት በየደረጃው ለሚያደርጋቸው ልማቶች የልማቱ ባለቤት የሆነው የህብረተሰብ ሙሉ ትብብሩን እንዲያደርግ ተጠየቀ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 08/09 እና ቀበሌ 10 መልሶ ማልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎና በመንገድ ልማት ከሚነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
በቀበሌ 08/09 በተደረገው ውይይት ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሰሀ ገ/እግዚአብሔር መንግስት በየደረጃው የሚሰራቸው የልማት ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በመሆኑም የልማቱ ባለቤት የሆነው ህብረተሰብም ልማቱን ለማፋጠን የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጠይቀዋል ፡፡ እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ በልማቱ ምክኒያት የሚነሱት ነዋሪዎች እንደየፍላጎታቸውና አቅማቸው በሚፈቅደው መሰረት በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በቀበሌ ቤቶች እንዲሁም የግል ባለንብረቶች ደግሞ እንደፍላጎታቸውና ይዞታቸው ምትክ ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡ 
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አንዳንድ ነዋሪዎች ባነሱት ጥያቄ መልሶ ማልማቱ መቼ ይጀመራል? መቼስ ይጠናቀቃል? ለግል ባለይዞታዎችና በንግድ ለተሰማሩ ምን ታስቧል? የሚሉና የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በዚህ ፕሮጄክት በክ/ከተማው ሊለማ የታቀደው መሬት 74 ሄክታር ሲሆን ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለንግድ ስራዎች ለማህበራዊ አገልግሎትና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማቶች እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
ሐምሌ 08 2002ዓ.ም
ምክር ቤት ጉባኤ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ፡፡ምክር ቤቱ የ2003 በጀት ዓመት የፋይናንስ ዕቅድ ሪፖርትንም ተወያይቶ አፅድቋል፡፡
ጉባኤው በገነት ሆቴል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው አፈጉባኤ አቶ እንግዳ አምዴ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የምክር ቤት አባላት በኮሚቴ በመንቀሳቀስ የ2002 ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፤ዴሞክራሲዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲያልፍ ከፍተኛ ጥረት አድረገዋል፡፡የምክር ቤት አባላት ህዝቡ የሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም በምርጫው ያሳዩትን መነሳሳት በልማትና መልካም አስተዳደር ላይም እንዲደግሙት አሳስበዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ የ2002 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ሲያቀረቡ እንዳሉት ደግሞ በበጀት ዓመቱ የቁልፍ ተግባራትን ከማከናወን ጎንለጎን የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናን በሙከራ ደረጃ በመተግበሩ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን አስረድተዋል፡፡
በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አማካኝነት ቲቢና ኤች.አይ.ቪን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የገለፁት ዋና ስራአስፈፃሚው በበጀት ዓመቱ ከ10ሺ በላይ ለሚሆኑ ስራአጦች የስራ እድል መፈጠሩንም ለምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል፡፡
ምክርቤቱ የ2ኛ መደበኛ ጉባኤን ቃለጉባኤንና አስቸኳይ ቃለጉባኤን እንዲሁም የ2003 በጀት ዓመት የፋይናንስ እቅድንና የ2002 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ተወያይቶ አፅድቋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ሐምሌ 01 2002 ዓ.ም
የጤና ኤክስቴንሽን ስልጠና 
በቂርቆስ ክፍለከተማ የቀበሌ20/21 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ለ4ወራት የሚቆይ ስልጠና ለቀበሌው ነዋሪዎች በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተመለከተ፡፡
በቀበሌው ከሚገኙት 6 የማሰልጠኛ ጣቢያዎች በአንዱ ስልጠናውን ስትሰጥ ያገኛት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ሲ/ር አምሳለ ልዑል እንደተናገረችው ስልጠናው በየቤቱ በሰበሰብነው መረጃ መሰረት በህብረተሰቡ ላይ የሚታዩ የጤና ችግሮች መነሻዎች የቆሻሻ አወጋገድ ችግር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡
ስልጠናው የቀበሌው ነዋሪዎች ጤናቸውን ለመጠበቅ አካባቢያቸውን ፅዱ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አመልክታለች፡፡
የቀበሌ20/21 የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብይ ጣሰው በበኩላቸው በከተማችን ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አንዱ በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ አማካኝነት የህብረተሰቡን ጤና መጠበቅ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ለ4ወራት በሚቆየው ስልጠና ስልጣኞች በየአካባቢያቸው የሚወስዱት ስልጠና በተግባር የተደገፈ በመሆኑ ያገኙትን ትምህርት በማዳበር ለሌሎች የቀበሌው ነዋሪዎች ያስተምራሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡
ስልጠናው ህብረተሰቡ ጤናውን እራሱ እንዲጠብቅ እንደሚረዳውም አመልክተዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሐምሌ 01 2002 ዓ.ም
በመልሶ ማልማት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
መንግስት በየደረጃው ለሚያደርጋቸው ልማቶች የልማቱ ባለቤት የሆነው የህብረተሰብ ሙሉ ትብብሩን እንዲያደርግ ተጠየቀ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 08/09 እና ቀበሌ 10 መልሶ ማልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎና በመንገድ ልማት ከሚነሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
በቀበሌ 08/09 በተደረገው ውይይት ላይ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሰሀ ገ/እግዚአብሔር መንግስት በየደረጃው የሚሰራቸው የልማት ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በመሆኑም የልማቱ ባለቤት የሆነው ህብረተሰብም ልማቱን ለማፋጠን የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጠይቀዋል ፡፡ እንደ ዋና ስራ አስኪያጁ ገለጻ በልማቱ ምክኒያት የሚነሱት ነዋሪዎች እንደየፍላጎታቸውና አቅማቸው በሚፈቅደው መሰረት በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በቀበሌ ቤቶች እንዲሁም የግል ባለንብረቶች ደግሞ እንደፍላጎታቸውና ይዞታቸው ምትክ ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡ 
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አንዳንድ ነዋሪዎች ባነሱት ጥያቄ መልሶ ማልማቱ መቼ ይጀመራል? መቼስ ይጠናቀቃል? ለግል ባለይዞታዎችና በንግድ ለተሰማሩ ምን ታስቧል? የሚሉና የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በዚህ ፕሮጄክት በክ/ከተማው ሊለማ የታቀደው መሬት 74 ሄክታር ሲሆን ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለንግድ ስራዎች ለማህበራዊ አገልግሎትና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማቶች እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
ሰኔ 30 2002ዓ.ም
የሴቶች ማህበር አባላት ውይይት
ሴቶች ሙስናን በመዋጋት ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተጠቆመ፡፡
የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ከፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንና ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር በስነምግባርና ፀረ-ሙስና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ብዙአለም ገበየሁ እንደተናገሩት የከተማው ሴቶች ማህበር በአስሩም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የሴቶች ማህበር አባላት በፀረ-ሙስናና ስነምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሚሰጠው አባላቱ በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ አስቦ ነው፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በየቀበሌዎቹ የሚታዩ የሙስናና የስነምግባር ችግሮችን ነቅሰው ማውጣትና መፍትሔውንም መወያየት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው የሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ ጌጤነሽ ጥላሁን በበኩላቸው ሙስናና ስነምግባር ችግር በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የእለት ተዕለት ስራዎች ላይ ይስተዋላልነው ያሉት፡፡ ችግሩን ለመዋጋት ሴቶች ሊያደርጉት ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችን ለተሳታፊዎች አስገንዝበዋል፡፡
ተሳታፊዎችም ሙስናን በተለያዩ የመልካም አስተዳደር ተግባራት የሚንፀባረቅ በመሆኑ ልንዋጋው ይገባል ብለዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ሰኔ 29 2002ዓ.ም
የሽልማት ስነስርዓት
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ከአዶኒስ የስራ አመራርና ንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠናና ማማከር አገልግሎት ጋር በመተባበር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ስልጠናውን ለተከታታሉ ሰልጣኞችም የሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደርጉት የቂርቆስ ክፍለከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሱራፌል አርአያ ሰልጣኞች በ9ቀናት ውስጥ የወሰዱትን ስልጠና በተግባር ለመተርጎም ያደረጉትን ጥረት አድንቀው ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
የክፍለ ከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሻፊ በበኩላቸው ለሀገራችን የባህል እድገት አስተዋፅኦ የሚያደርጉትን የጥልፍ ስራዎች መስራታችሁ ባህላችንን ጠብቀን እንድንቆይ ያደርገናል ብለዋል፡፡ 
በጋራ እንደሰለጠናችሁ ሁሉ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ ስራችሁን ውጤታማ አድርጉ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
አሰልጠኞችና ሰልጣኞች በጋራ በሰጡት አስተያየትም የጥልፍ ስራ በዝቅተኛ ወጪ መሰራት የሚችል ስራ በመሆኑ በርካቶች ዘርፉን ቢቀላቀሉ ውጤታማ ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡
ስልጠናው በባህላዊ አልባሳት የጥልፍ ስራና በመሰረታዊ የንግድ ክህሎት ላይ የተሰጠ ሲሆን በባህላዊ አልባሳት የጥልፍ ስራ የተሰማሩ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ 
ሰልጣኞችም የተዘጋጀላቸውን የሰርተፊኬት ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
091304933
ሰኔ 28 2002 ዓ.ም
ከተማችንን ጽዱ ለማድረግ ህብረተሰቡ ቆሻሻን በአግባቡ እንዲያስወግድ ተጠየቀ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ15/16 የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ከሸራተን አዲስ ሆቴል ልዩ ልዩ የፅዳት ቁሳቁሶችን በልገሳ አግኝቷል፡፡
የቆሻሻ መሰብሰቢያ ጋሪዎች፤የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች፤መጥረጊያዎችና የደንብ ልብሶች የሸራተን አዲስ ሆቴል ለቀበሌ15/16 በልገሳ ከሰጣቸው ቁሳቁሶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የቀበሌው ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ዳዊት ቀኖ እንደገለፁት የቆሻሻ ማፅጃ እቃዎቹ በከተማችን ብሎም በቀበሌያችን የሚታየውን ቆሻሻ በአግባቡ ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ህብረተሰቡ በቀበሌው የተለያዩ ስፍራዎች በሚቀመጡ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች አማካኝነት ቆሻሻውን እንዲያስወግድም አሳስበዋል፡፡
ለቀበሌው የተሰጡት የቆሻሻ ማፅጃ እቃዎች በ200 ሺ ብር ወጪ የተገዙ መሆናቸውን የተናገሩት የቀበሌው የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሉሀ በቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤውን ማስፋት ከጽ/ቤቱ የሚበቅ አንኳር ስራ መሆናኑን ነው የገለፁት፡፡
የቀበሌ 15/16 የፅዳት አገልግሎት ኬዝ ቲም ማናጀር አቶ በለጠ ጎቦ በበኩላቸው በአካባቢው ተተክለው አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉት የቆሻሻ ማጠራቀሚዎች ከአገልግሎት ብዛት ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን ገልፀው በአዳዲሶቹ መተካታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሰኔ 25 2002 ዓ.ም
የቀበሌ 10 የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ  
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ 10 የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት በ2002 በጀት ዓመት ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ፡፡47 ሰዎችን በቡድን በማደራጀት የዕቅዱን 92 በመቶ ማከናወኑንም ተመልክቷል፡፡
ወ/ሮ ህይወት ወ/አብ ይባላሉ በ2002 በጀት ዓመት የቀበሌው ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ስር ከተደራጁ አንቀሳቃሾች መካከል አንዷ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ጽ/ቤቱ 7 ሆነው ለመደራጀት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ በ20 ሺ 500 ብር ብርድ ስራቸውን አስጀምሯቸዋል፡፡
እንደነ ወ/ሮ ህይወት ሁሉ ለ47 በቡድን ተደራጅተው መስራት ለሚፈልጉት የቀበሌው ነዋሪዎች የዘርፉ ተጠቃሚ አድርገናል ያሉት ደግሞ የቀበሌው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ ጌጤነሽ ይርጋ ናቸው፡፡
እንደ ኃላፊዋ ገለፃ በበጀት ዓመቱ 51 ሰዎችን በቡድን ለማደራጀት ታቅዶ 41 ሰዎችን በቡድን በማደራጀት የዕቅዱን 92 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡ አንቀሳቃሾቹን ከማደራጀት ባለፈ ከ2ሚሊዮን 800 ሺ ብር በላይ ብድር እንዲያገኙ በማድረግ ለስራቸውን ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 3 ባዛሮች መዘጋጀታቸውን የሚናገሩት ኃላፊዋ ይህም የአንቀሳቃሾችን የገቢያ ችግር ለመቅረፍ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡  

ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

የከተማ ግብርና ስልጠና ለእናቶች ተሰጠ
ህብረተሰቡ የአመጋገብ ስርዓቱን የተመጣጠነ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለጤና ባለሙዎችና እናቶች ለ6 ቀናት የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግራቸው የከፈቱት የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ዶ/ር እታገኝ ጌታሁን እንደተናገሩት የእናቶችና ህፃናት ሞትን ለመቀነስ ሀገራችን መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ህፃናትን ለሞት ከሚዳርጉ ዋነኛ ምክኒቶች አንዱ የተመጣጠነ ምግብ አለማግኘታቸው መሆኑን በመገንዘብ ተሳታፊ እናቶች ልጆቻቸውን እንዴት መመገብ እንደሚችሉ ለማስተማር ታስቦ ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የከተማ ግብርና ኤክስቴንሽን የስራ ሂደት መሪ አቶ ደስታ ሎሬንሶ የከተማ ግብርናን ጠቀሜታ ሲያስረዱ እንዳሉት ደግሞ ዘርፉ በትንሽ ቦታ ላይ የተለያዩ አትክልቶችን በማብቀል ለምግብነት ለማዋል የሚስችል ነው፡፡ የዘርፉን ጠቀሜታ በመመልከት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ነው አቶ ደስታ የመከሩት፡፡
ስልጠናውን ሰጡት በክፍለ ከተማው የከተማ ግብርና የእንስሳትና ሰብል ምርት አያያዝ ባለሙያ ወ/ሮ አሰቡ ፀጋዬ ስልጠናው በተግባር የተደገፈ በመሆኑ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ምሰሶ ለሆኑ እናቶች መሰጠቱ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሰኔ 22 2002ዓ.ም
የመፅሀፍት ልገሳ ተደረገ
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ እንደሚጠይቅ ተጠቆመ፡፡
የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር 33 ሺ ብር የሚያወጡ 866 የማመሳከሪያ መፅሐፍትን ለጠመንጃ ያዥ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት በልገሳ ሰጥቷል፡፡
የጠመንጃ ያዥ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሔርጳሳ ጫላ እንደተናገሩት መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚያደረገው እንቅስቃሴ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴርም ያደረገው የመፅሀፍት ልገሳ ትምህርት ቤቱ ያለበትን የመፅሀፍት እጥረት በእጅጉ ያቃልለዋል ነው ያሉት፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤትን ወክለው ንግግር ያደረጉት አቶ ሐዱሽ ሐይሌ ምኒስቴር መ/ቤቱ ያደረገውን ድጋፍ አመስግነው የትምህርት ጥራት ፓኬጁን ስኬታማ ለማድረግ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል፡፡
የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴርን ወክለው መፅሀፍቶቹን ለት/ቤቱ ያስረከቡት የሚኒስቴር መ/ቤቱ የህዝብግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ኤፍሬም በበኩላቸው ልገሳውን ያደረገው የህፃናት የመማር መብትን በማስጠበቅ ረገድ ለሌሎች አርአያ ለመሆን አስቦ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የህፃናትን መብት ማስጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብን እንደሚሻ ጠቁመዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሰኔ 19/2002 ዓ.ም
የም/ቤት አባላት ችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡
በየደረጃው የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው የአካባቢን ደህንነት ያገናዘቡና ለተተኪው ትውልድ የሚተላለፉ እንዲሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊረባረብ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ የም/ቤት አባላት በፒኮክ መናፈሻ የችግኝ ተከላ ባካሄዱበት ወቅት የም/ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ እንግዳ አምዴ እንደተናገሩት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የአለምን ህዝብ በእጅጉ እያወያየ ያለና ችግሩም እየተወሳሰበ መምጣቱን ነው የገለጹት፡፡ከዚህም የተነሳ የአየር ንብረት መዛባትና የተፈጥሮ ሀብት መመናመን ችግሩን የባሰ አድርጎታል፡፡
በአዲስ አበባ መሃል የምትገኘው የቂርቆስ ክ/ከተማ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚገኙባት መሆኑና በርካታ ህዝብ የሚኖርበት መሆኑን የገለጹት አፈ ጉባኤው የወንዝ ዳርቻዎችና አረንጓዴ ቦታዎችም ከአረንጓዴ ይዞታቸው ውጪ በመሆን ለተለያዩ ግንባታዎች ለመኖሪያ ቤትና ለእንስሳት እርባታ እየዋሉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
በክ/ከተማው አካባቢ ጥበቃ ሴክተር የስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ አዳነች ወንጀሎ በበኩላቸው የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ትኩረት ሰጥቶ ሊንቀሳቀስበት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በየደረጃው ችግኞችን ከመትከል ባለፈም እየተንከባከቡ በማሳደግ የተገፈጥሮን ስነ ምህዳር መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የም/ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ሀጎስ ለምለም እንደገለጹት ደግሞ እያንድንዱ የህብረተሰቡ ክፍል አንድ ዛፍ ተክሎ ቢንከባከብ የአገሪቱን የደን ሀብት ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ እንደሚቻል አመልክተው የአካባቢው ነዋሪዎችም የተተከለውን ዛፍ በመንከባከብ እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
ሰኔ 19/2002 ዓ.ም
የም/ቤት አባላት ችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡
በየደረጃው የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው የአካባቢን ደህንነት ያገናዘቡና ለተተኪው ትውልድ የሚተላለፉ እንዲሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊረባረብ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ የም/ቤት አባላት በፒኮክ መናፈሻ የችግኝ ተከላ ባካሄዱበት ወቅት የም/ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ እንግዳ አምዴ እንደተናገሩት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የአለምን ህዝብ በእጅጉ እያወያየ ያለና ችግሩም እየተወሳሰበ መምጣቱን ነው የገለጹት፡፡ከዚህም የተነሳ የአየር ንብረት መዛባትና የተፈጥሮ ሀብት መመናመን ችግሩን የባሰ አድርጎታል፡፡
በአዲስ አበባ መሃል የምትገኘው የቂርቆስ ክ/ከተማ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚገኙባት መሆኑና በርካታ ህዝብ የሚኖርበት መሆኑን የገለጹት አፈ ጉባኤው የወንዝ ዳርቻዎችና አረንጓዴ ቦታዎችም ከአረንጓዴ ይዞታቸው ውጪ በመሆን ለተለያዩ ግንባታዎች ለመኖሪያ ቤትና ለእንስሳት እርባታ እየዋሉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
በክ/ከተማው አካባቢ ጥበቃ ሴክተር የስራ ሂደት አስተባባሪ ወ/ሮ አዳነች ወንጀሎ በበኩላቸው የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ትኩረት ሰጥቶ ሊንቀሳቀስበት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በየደረጃው ችግኞችን ከመትከል ባለፈም እየተንከባከቡ በማሳደግ የተገፈጥሮን ስነ ምህዳር መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የም/ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ሀጎስ ለምለም እንደገለጹት ደግሞ እያንድንዱ የህብረተሰቡ ክፍል አንድ ዛፍ ተክሎ ቢንከባከብ የአገሪቱን የደን ሀብት ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ እንደሚቻል አመልክተው የአካባቢው ነዋሪዎችም የተተከለውን ዛፍ በመንከባከብ እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
ሰኔ 17 2002 ዓ.ም
የሙያ ፈቃድና ሬጉላቶሪ ሽልማት ሰጠ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የሙያ ፈቃድና ሬጉላቶሪ ዋና የስራ ሂደት በጥራት ደረጃቸው የተሻለ አገልግሎት ለሚሰጡ የሬስቶራንቶች፤የመኝታ ቤቶች፤ የእንግዳ ቤቶችና ሆቴል ባለቤቶች ሽልማት ሰጠ፡፡
ሽልማቱ በተሰጠበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ገብሩ አስካል እንዳሉት በጽ/ቤቱ ውስጥ ካሉ 3 የስራ ሂደቶች አንዱ የሙያ ፈቃድና ሬጉላቶሪ ዋና የስራ ሂደት ሲሆን ሽልማቱ የተዘጋጀው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሁም ተወዳዳሪ ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡
በየተቋማቱ ተዘዋውረው ቁጥጥር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ሰራተኞችና ከአዲስ አባባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተወከሉ ዳኞች በበኩላቸው የመመዘኛ መስፈርቶቹ በአገልግሎት አሰጣጡ የእንግዳ መቀበያ፤የመፀዳጃና ምግብ ማዘጋጃ ቤቶች ንፅህና ከተቀመጡት መስርቶች መካከል መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በየተቋማቱ የሚታዩ መልካም ገፅታዎችን ከማበረታት ጎንለጎን በአገልግሎት አሰጣጣቸው ችግር ያለባቸውን የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ማሳሳባቸውን ተቆጣጣሪ ዳኞቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የተሻለ አገልግሎት ላሳዩ ተቋማት የዋንጫ፤የምስክር ወረቀትና የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933
ሰኔ 15 2002ዓ.ም
በኤች.አይ.ቪ ዙሪያ የማህበረሰብ ውይይት
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በኤች.አይ.ቪ አድስ ዙሪያ የማህበረሰብ ውይይት አካሄደ፡፡
ውይይቱ የተዘጋጀው ለቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት ምክኒያቶች፤ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ዜጎች የመድሃኒት አጠቃቀምና የበሽታው መከላከልና መቆጣጠር ሂደትን አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመወያየት ታስቦ ነው፡፡
ውይይቱ በኤግዚቢሽን ማዕከል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማይ ብርሀነ እንዳሉት ኤች.አይ.ቪ በሀገራችን እያደረሰ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመግታት በጉዳዩ ዙሪያ መወያየት አስፈልጓል፡፡የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የውይይቱ ተሳታፊዎች የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት የኤች.አይ.ቪ አድስ መከላከልና መቆጣጠር ወሳኝ የስራ ሂደት ባለቤት ሲ/ር ሳባ ካሳዬ በበኩላቸው ኤች. አይ.ቪ በሀገራችን መኖሩ ከተረጋገጠበት 28 አመታት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ዜጎች በከተማችን በርካታ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ይህም በግልፅነት አለመወያየት፤ለአጓጉ ሱሶች መጋለጥና ጥንቃቄ የጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ እራሱን መጠበቅ ይጠበቅታል ብለዋል፡፡
በእለቱ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሞክሮአቸውን ያስረዱ ሲሆን ለቫይረሱ ስርጭት መቀነስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ -- 0913049933
ሰኔ 14 2002 ዓ.ም
የሰፍሓ ዓመታዊ ጉባዔ ተካሄደ
በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበሌ 02/03 የሰላም ፍትህና አንድነት የትግራይ ተወላጆች ማህበር የማህበሩን ዓመታዊ ጉባኤ አካሄደ፡፡ አባላቱ የሐውዜንን ጭፍጨፋ 22ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓልም አክብረዋል፡፡
በዓሉ በዳይቬነትሪ ት/ቤት አዳራሽ ሲካሄድ የሀገር አቀፍ የሰፍሓ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ያይንሸት ተኮላ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የሰላም የፍትህና የአንድነት ማህበር ምርጫ 97ን ተከትሎ በትግራይ ተወላጆች የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ከተቋቋመ በኋላም የክልሉን ተወላጆች የፖለቲካ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ አንበሳ ባንክና አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያን በማቋቋም ማህበሩን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
የማህበሩ የቂርቆስ ክ/ከተማ ሊቀ መንበር አቶ ምዑዝ ገ/ህይወት በበኩላቸው ማህበሩ ሲመሰረት ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመተባበር የትግራይን ክልል ለማልማትና የክልሉን ተወላጆች በማህበራዊ ፖለቲካዊ ረገድ ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ዓላማ አድርጎ ለመንቀሳቀስ ነው ብለዋል፡፡
በዕለቱ በወረዳ 23 ለተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ወ/ሮ ብነሽ ዓባይ በእንግድነተ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡ ወ/ሮ ብርነሽ እንደተናገሩትም ማሕበሩ የክልሉን ተወላጆች ተጠቃሚ ለማድረግ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ማህበሩ ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችን በስፋት በማሳተፍም ሊጠናከር እንደሚገባው ወ/ሮ ብርነሽ አሳስበዋል፡፡
በእለቱ የሐውዜን ጅምላ ጭፍጨፋን 22ኛ ዓመት ለመዘከር የተዘጋጀ ሻማ የተለኮሰ ሲሆን በወቅቱ ለተሰዉ ሰማዕታትም የ1ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
ሰኔ 12 2002 ዓ.ም
የጤና ጽ/ቤት ስልጠና ሰጠ
የቂርቆስ ክፍለከተማ ጤና ጽ/ቤት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ወሳኝ የስራ ሂደት በክፍለከተማው ለሚገኙ ርዕሳነ መምህራንና ም/ርዕሰመምህራን በጤና ኤክስቴንሽን አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጣና ሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በጽ/ቤቱ የትምህርትና ጤና ኤክስቴንሽን ኬዝ ቲም አሰተባባሪ ሲ/ር ትዕግስት ምትኩ እንደገለፁት በሽታን መከላከል ላይ ያተኮረው የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ በትምሀርት ቤቶች፤በወጣት ማዕከላትና በማህበረሰቡ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል፡፤
ፓኬጁ በማህበረሰቡ ሲተገበር እያንዳንዱ ባለሙያ ከ500 አባወራዎችመካከል 60 ሞዴል አባዎራዎችን ይመርጣል የተመረጡትም ለተቀሩት ያስተምራሉ ብለዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊ ርዕሳነ መምህራንና ም/ርዕሳነመምህራንም የፕሮግራሙን ስኬታማነት ለማረጋገጥ ኮሚቴዎችን በማዋቀርና ለባለሙያዎቹ በራቸውን ክፍት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በጤና ጽ/ቤት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ወሳኝ የስራ ሂደት መሪ ሰ/ር ካሰች ጥበቡ አሳስበዋል፡፡
ከተሳታፊዎች ከተሰነዘሩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከልም 1ጤና ባለሙያ ለ500 አባወራዎች ማገልገል አስቸጋሪ አይሆንም ወይ፤ትግበራው ትምህርት ቤቶች ላይ ለምን ዘገየ፤ስልጠናው መሰጠቱ የላቀ ጠቀሜታ ስላለው ለፕሮግራሙ ሰኬታማነት ከባለሙያዎቹ ጋር ለመስራት ተዘጋጅተናል የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ -0913049933
ሰኔ 12 2002 ዓ.ም
ዓመታዊ የስፖርት ውድድር መዝጊያ በዓል ተካሄደ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስፖርት ም/ቤት ዓመታዊ የስፖርት መዝጊያ ፕሮግራሙን አካሄደ፡፡
      በኢትዮጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት ስፖርት ሜዳ በተካሄደው የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ በክፍለከተማው ከሚገኙ 11 ቀበሌዎች 9 ቀበሌዎች የስፖርት ልዑካን ተገኝተዋል፡፡
      ከታህሳስ 2002 ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ወራት ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር መረብ ኳስ፤እግር ኳስ፤አትሌቲክስና ጂምናስቲክን ጨምሮ በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች ውድድሩ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
    በስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ኢሳያሳ ታፈሰ እንደገለፁ ከአስራ አንዱም ቀበሌ የተውጣቱ ት በድምሩ 635 ስፖርተኞች በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡ ክፍለከተማው በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች 232 ወጣቶችን በመላው አዲስ አበባ የስፖርት ውድድር በማሳተፍ ከ10ሩ ክፍለ ከተሞች በ2ኛ ደረጃ ሊቀመጥ ችሏል፡፡
     የክፍለ ከተማው አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊና የስፖርት ም/ቤቱ ተወካይ አቶ አምላኩ ተበጀ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ወጣቶች መካከል ስፖርታዊ ውድድር መካሄዱ በወጣቶቹ መካከል የመቻቻልና የመከባበር መንፈስን በማስፈን የእርስበርስ ግንኙነትን ከማጠናከሩም በላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ጉልህ ቦታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
      በዕለቱ በተካሄደው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ስፖርታዊ ትርኢቶች የተካሄዱ ሲሆን በመዝጊያ ጨዋታ ለዋንጫ የቀረቡ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ በቅሎ ቤ/ት ቡድን መርከብን 3 ለ 0 በመርታት ዋንጫ አንስቷል፡፡ በተለያዩ ስፖርት ዓይነቶች የተሳተፉና ብልጫ ላስመዘገቡ የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ -0913278575
ሰኔ 12 2002 ዓ.ም
የህጻናት ቀን በዓል ተከበረ
ህጻናት ለወደፊት ኃላፊነት መሸከም የሚችሉና በራሳቸው የሚተማመኑ ሆነው እንዲያድጉ በየደረጃው የሚደረግላቸው እንክብካቤ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ተጠየቀ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበሌ 15/16 ሴቶችና ህጻናት ጉዳች ጽ/ቤት የአፍሪካ ህጻናት ቀንን አክብሯል፡፡
በዓሉ በተከበረበት ወቅት በክብር እንግድነት በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት ቀኖ እንደተናገሩት ህጻናት በራሳቸው እንዲተማመኑና በቀጣይ የሀገር ተረካቢነት ስሜት ተሰምቷቸው አእንዲያድጉ በየደረጃው የሚደረግላቸው እንክብካቤ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ፡፡
የቀበሌው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካዲስ ኃይሌ በበኩላቸው የህጻናት ጉዳይ የኢትዮጵያ ወይም የአፍሪካ ጉዳይ ባቻ ሳይሆን በዓለማቀፍ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል፡፡ በቀበሌያቸው በየወሩ ሁለት ጊዜ በህጻናት ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚወያይ የማህበረሰብ ውይይት እንደሚደረግና ከወላጅ ከት/ቤት ከእድርና ከአካባቢ ነዋሪዎች የተውጣጡ አባላት እንደሚሳተፉበት ገልጸዋል፡፡
ህጻናቱ የሚሰጣቸው ትኩረትና የሚደረገግላቸው እንክብካቤ ተጠናክሮ ሊቀጠል ይገባል የሚሉት ኃላፊዋ የህጻናት መዋያና ጊዜ ማሳለፊያ ቦታዎችም ትኩረት ሊሰጥባቸው እንደሚገባ ይገልጻሉ፡፡
ታሪኩ እንዳለ
-0913278575
11/10/2002
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ስርዓት ፆታን የማስረፅ ወሳኝ የስራ ሂደት በክፍለ ከተማና ቀበሌ አመራሮች የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅን አስተዋወቀ፡፡
የፓኬጁን አስፈላጊነት ያስረዱት በክፍለ ከተማው የሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ስርዓተ ፆታን የማስረፅ ወሳኝ የስራ ሂደት ባለቤት ወ/ሮ መሰረት አቡዬ እንዳሉት ፓኬጁ የሴቶችን ኢኮኖሚዊ፤ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማጎልበት የተለመ ነው፡፡
ፓኬጁ የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳተፊነት በፅሑፍ ከማቀመጥ ባለፈ የየሴክተር ጽ/ቤቶች ፓኬጁን በዕቅዳቸው ውስጥ እንዲያካትቱት ይጠቁማል ነው ያሉት፡፡
ፓኬጁ በሴቶች ላይ የሚደርሱ የሀይል ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በማስወገድ በ2020 ዓ.ም የሴቶችን እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የማድረግ እቅድ እንደያዘም ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል፡፡
ማህበረሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
 
ሪፖርተር
 
ራዚቃ ዲኖ
                   11/10/2002
 
የአፍሪካ ህጻናት ቀን ተከበረ
 
ህጻናት በአገራችን እየተገነባ ያለውን የዲሞክራሲ ስርዓት እየለመዱና በዲሞክራሲ ስርዓቱ ተጠቀሚ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ፣
በቂርቆስ ክ/ከተማ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክርስቲያንና ከራይት ቱ ፕሌይ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የአፍሪካ ህጻናት ቀን 19ኛ ዓመት በዓልን አከበረ፡፡
በዓሉ በተከበረበት ወቅት የክ/ከተማው ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት በቀለ እንደተናገሩት እንደ አውሮፐፓውያኑ አቆጣጠር በ1976 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት በህጻናት ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ያደረገበትን ቀን ለማሳሰብ ነው፡፡ የአፍሪካ ህጻናት ቀን ዘንድሮ በአገራችን ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የአፍሪካ ህጻናት ቀን ህጻናት እኛው ራሳችን እንንከባከባቸው መብታቸውን እናክብር በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡ ህጻናት በአገራችን እየተገነባ ያለውን የዲሞክራሲስርዓት እየለመዱ እንዲያድጉለየት/ቤቱ የህጻናት ፓርላማ በማቋቋም በየደረጃው እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ተወካይ አቶ ዮሐንስ ፈይሳ በበኩላቸው ህጻናት መብትና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉየምንረባረብበት ወቅት ነው ብለዋል፡፡ ህጻናቱ የነገ ሀገር ተረካቢነት ኃላፊነት የሚሸከሙ በመሆኑ ኃላፊነትን መሸከም የሚችሉ እንዲሆኑም መብታቸው ተጠብቆና ተገቢውን እንክብካቤ ተደርጎላቸው ማደግ ይገባቸዋል፡፡ እንደ አቶዮሐንስ ገለጻ፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
                                           11/10/2002
የአዲስ አበባ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የስነ ህዝብና ስነ ተዋልዶንዑስ የስራ ሂደት ለመምህራንና ተማሪዎች በስነህዝብ፣ ስነ ተዋልዶና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናውን በንግግራቸው የከፈቱት የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶጌታቸው ቢራቱ እንደተናገሩት ስልጠናው ለመምህራንና ተማሪዎች በስነህዝብ ስነተዋልዶና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ያደርገዋል፡፡
በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የስነ ህዝብና ስነ ተዋልዶንዑስ የስራ ሂደት አስተባባሪአቶዘሩ ይምራህ በበኩላቸው ስልጠናው በየካና ቂርቆስ ለሚገኙመምህራንና ተማሪዎች የሰጠ ሲሆን ይህም ተማሪዎች በአቻ ግፊት ለአጉል ሱሶች እንዳይሰጡና ከትምህርታቸው እንዳይደናቀፉያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
በስልጠናው የተሳተፉ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ትምህርት ወደየአካባቢያቸው ሲመለሱ ማስተማር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
በየክበባቱ የሚገኙ አባላት ልምዶቻቸውን አካፍለዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ


ሰኔ 22 2002ዓ.ም
 
በደንብ ማስከበር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ሰኔ 09/10/2002
  የከተማዋን ጸጥታ ለማስጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማስፈን በዘርረፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
  በቆርቆስ ክ/ከተማ የፍትህና ህግ ጉዳዮች ጽ/ቤት የደንብ ማስከበርና መቆጣጠር ዋና የስራ ሂደት ከአስራ አንዱም ቀበሌዎች ለተውጣጡ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የደንብ ማስከበር ሠራተኞች የፖሊስና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተወካዮች የተሳተፉበት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ 
  ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው በዚህ ስልጠና በህገ-ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ የመንገድ ላይ ልመና የመንገድ ላይ የመኪና እጥበትና በትራፊክ ህግ አተገባበር ዙሪያ ስልጠናው ትኩረት አድርጓል፡፡
  በክ/ከተማው የደንብ ማስከበርና መቆጣጠር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ በውቀቱ ገበየሁ እንደገለጹት በክ/ከተማው ለገሃርና ሜክሲኮ አካባቢዎች ከፍተኛ የጎዳና ላይ ንግድ ይካሄድባቸዋል፡፡ አንዳንድ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራትም በመንገዶች አካባቢ የመኪና እጥበት ሲያካሂዱ ተስተውሏል፡፡እነዚህን ተግባራት ለማስቀረትም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እንዲሰሩ ለማስቻል ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
  በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩት ወ/ሮ ሽዋዬ አባተ በበኩላቸው ለሁለት ቀናት ከተሰጠው ስልጠና ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይነትም ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
  አቶ ሰብስቤ ኃይሉ በቀበሌ 01/19 የደንብ ማስከበር ሰራተኛ ናቸው፡፡ የደንብ ማስከበር ስራ በአንድ አካል ብቻ ሊተገበር የማይችል በመሆኑ ከፖሊስ ከጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ከትራፊክ ፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ስራውን ማከናወን እንደሚገባ መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር ታሪኩ እንዳለ 
09 13 27 85 75  

 
ሰኔ 08 2002ዓ.ም
ቀበሌ 04 ዲዛይንና ግንበታ ጽ/ቤት

     በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ04 ዲዛንና ግንባታ ጽ/ቤት እያስመዘገባቸው ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች በሆነ መልኩ እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገለፀ፡፡
    የቀበሌው ዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት አንድ ባለ 4 ፎቅ ጤና ጣቢያ በ6.2 ሚሊዮን ብር የሚስገነባ ሲሆን የጥቃቅንና አነስተኛ ማምረቻና ማሳያ ባለ 4 ፎቅ ህንፃ በ2.3 ሚሊዮን ብር ይገነባል፡፡
   የቀበሌው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ በላይ እንደተናገሩት በጥር ወር 2002ዓ.ም የተጀመረው ጤና ጣቢያ 2ኛ ፎቅ ላይ ደርሷል፡፡ ጤና ጣቢያው ተገንብቶ ሲጠናቀቅም በተመላላሽ በማዋለድ በእናቶችና ህፃናት ጤና ዘርፍም የጎላ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
    የጥቃቅንና አነስተኛ የማምረቻና የማሳያ ህንፃውም እስከሚቀጥለው መስከረም 30/2003 ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት በሚሰራቸው የልማት ስራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጎልቶ መታየት አለበት ያሉት ኃላፊው የቀበሌው ነዋሪዎችም በራሳቸው ተነሳሽነት የልማት ኮሚቴ በማቋቋም በቀበሌው የፍሳሽ ማስወገጃ እየሰሩ እንደሚገኙ አመላካተው በጤና ጣቢው ግንባታ ወቅትም ጤና ጣቢያው የሚገነባበትን አካባቢ በመልቀቅ ምትክ ቦታ ተሰጥቷቸው የተነሱ ሰዎችን አመስግነዋል፡፡
ሪፖርተር
ታርኩ እንዳለ
ሰኔ 08 2002ዓ.ም
ምርጥ አፈፃፀም በ05/06/07
    በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ 05/06/07 ባለፉት 9ወራት ምርጥ አፈፃፀም በማስመዝገብ ከአስራአንዱም ቀበሌዎች የአንደኝነት ደረጃን አገኘ፡፡
    በምርጥ አፈፃፀም ከተመረጡ 2 ክፍለ ከተሞችም ቂርቆስን በመወከል ለፌደራል ተሞክሮውን አቅርቧል፡፡
    የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ05/06/07 ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ጌታቸው መኮንን እንደገለፁት ቀበሌው የሚሰጣቸው አገልግሎቶችን ጥራት ያላቸው ለማድረግ የዳታ ቤዝ ስርዓት መጀመሩ፤የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በዞን መከፋፈሉና ኮከብ ሰራተኞችን መሸለሙ ለምርጥ አፈፃፀም ያበቁት ስራዎች ናቸው፡፡
    በዚህም በወሳኝ ኩነቶች ከተካተቱ አገልግሎቶች በተጨማሪ ያልተጠኑ አገልግሎቶችን ለይቶ በመስጠቱ ነዋሪውን በተሻለ ሁኔታ ማገልገል ችሏል ብለዋል፡፡
    ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ስራዎችንም ሰርቶ ለአገልግሎት እንዲበቁ ማድረጉን የገለፁት ስራአስፃሚው በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና አሰባሰብ ስዎችም ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት፡፡
   ለመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጡ ስኬታማነት መፃፍና ማንበብ ለማይችሉ ተገልጋዮች 3ዓይነት ቀለም ካርዶችን በማዘጋጀት አስተያየታቸውን እንደሚቀበሉ ነው አቶ ጌታቸው ያስረዱት፡፡አስተያየቶቹም በየጊዜው በቴክኒክ ኮሚቴው ተሰብስበው አስፈላጊው እርምት ይወሰድባቸዋል ብለዋል፡፡
የጀመሩትን ምርጥ አገልገሎት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመግለፅ ጭምር፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
ሰኔ 08 2002ዓ.ም
04 ገቢዎች ጽ/ቤት
      በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ04 ገቢዎች ጽ/ቤት ባለፉት 11 ወራት ከ3ሚሊዮን 900 ሺ ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
    ካፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ1ሚሊዮን 3ሺ763 ብር ብልጫ እንዳለውም ተገልፃDል፡፡
    በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ 04 ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ተክሌ እንደተናገሩት ቀበሌው ከ5ሚሊዮን 900ሺ ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ከ3 ሚሊዮን 900 ሺ ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 67 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡
    ገቢው የተሰበሰበው ታክስ ነክ፤ታክስነክ ካልሆኑና የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ ከታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች ከ2 ሚሊዮን 500 ሺ ብር በላይ በመሰብሰብ ከሌሎች የታክስ አይነቶች ብልጫውን ይይዛል ብለዋል፡፡
    በቀበሌው በተዋቀሩ የገቢ ግብረ ሀይልና የዳሳሽ ኮሚቴዎች አማካኝነት በመኪናና በበራሪ ፅሑፎች ቅስቀሳ በመደረጉ ካለፈው ዓመት የተሻለ ገቢ መሰብሰቡን ነው ወ/ሮ ገነት የገለፁት፡፡
    በቀበሌው 30 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 46 ግብር ከፋዮች መመዝገብ መቻሉን ገልፀው የግብር ከፋዩን ግንዛቤ ለማጎልበትም በትምህርት ስርፀት የስራ ሂደት አማካኝነት ሰፋፊ መድረኮችን አዘጋጅተን ተወያይተናል ብለዋል፡፡
    የኪራይ ገቢ ግብር፤የደሞዝ ገቢ ግብርና የውጪ ሰሌዳ ማስታወቂያ ገቢ ግብር በ2003 ዓ.ም ጽ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው ገቢዎች መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ

የግንቦት 20 በዓል በክ/ከተማ ደረጃ ተከበረ
 
    የግንቦት 20 ድል የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን ቋንቋቸውንና እሴቶቻቸውን ለማሳደግ መልካም አጋጣሚ እንደፈጠረ ተገለጸ፡፡

     በቂርቆስ ክተማ የግንቦት 20 19ኛ ዓመት የድል በዓል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በዓሉ በገነት ሆቴል ሲከበር የክ/ከተማው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊና የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግርማይ ብርሀነ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በብዙ መስዋዕትነት የተገኘው የግንቦት 20ን ድል ተከትሎ በአገራችን ለተከታታይ ዓመታት የምጣኔ ኃብት እድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡የአገራችን የዲሞክራሲ ተቋማት እያደጉና እየፈረጠሙ በሚገኙበት በዓሁኑ ወቅት በዓሉ መከበሩም ዕለቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
       የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢያ ራያ በበኩላቸው የግንቦት 20 ድል በአገራችን የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋቸውንና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል፡፡ የግንቦት 20ን ድል ተከትሎ የአገራችን ዜጎች ኃሳባቸውንና አመለካከታቸውን በነጻ የመግለጽ መብት አግኝተዋል፡፡ ድሉን ተከትሎ የተመሰረተው መንግስትም የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ በመንደፍ አገሪቱ ያደገችና የበለጸገች እንድትሆን ከፍተኛ ጥረት በማድረጉ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት የምጣኔ ኃብት እድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
      በዕለቱ በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀ የሻማ መለኮስና የዳቦ መቁረስ ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን በትግሉ ወቅት ለተሰዉ ሰማዕታትም የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡
 
ሪፖርተር
 
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
              ግንቦት 30 2002 ዓ.ም
 
ፍትህ ጽ/ቤት አበረታች ተግባር መፈጸሙን ገለጸ፡፡
 
     በጎዳና ላይ ንግድ የህገወጥ ግንባታ ቁጥጥርና በጸጥታ አጠባበቅ እንዲሁም የህግ የበይነትን በማረጋገጥ ስራ ላይ አመርቂ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የቂርቆስ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
     የቂርቆስ ክ/ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደቦጭ በተለይ ለክ/ከተማው ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት በክ/ከተማችን የጎዳና ላይ ንግድና ህገወጥ ግንባታ በስፋት የሚካሄድባቸውን ቦታዎች በመለየት መፍትሄ የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
     በዚህም በዕያንዳንዱ ቀበሌ የደንብ ማስከበር ቁጥጥር ተደርጎ በ150 የጎዳና ላይ ነጋዴዎች በያንዳንዳቸው 60 ብር መቀጮ ከ9ሺ ብር በላይ ገቢ ተደርጓል ለ759ያህል ሰዎችም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡
      በጎዳና ላይ ንግድ ለተሰማሩ ግለሰቦች የመሸጫ ቦታ እንደተዘጋጀ የገለጹት ኃላፊው ተግባሩን ከስሩ ለማስወገድም ጽ/ቤቱ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለጻ በየቀበሌው የጸጥታ ምክር ቤቶች ተቋቁመው ጸጥታውን ለማስጠበቅ ከፖሊስና ህብረተሰቡ ጋር በመተባበር እየሰሩ ይገኛሉ ህገወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብሩን እንዲያደርግም አቶ ሰለሞን ጠይቀዋል፡፡ 
  ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
09 13 04 99 33
ግንቦት 30 2002 ዓ.ም
             
የግንቦት 20 በዓል በቀበሌዎች ተከበረ
 
    የግንቦት 20 19ኛ ዓመት በዓል በቂርቆስ ክ/ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎች በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
    በዓሉ በቀበሌ 08/09 በተከበረበት ወቅት የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ ሉሌ እንደተናገሩት ብሔር ብሔረሰቦች በቋቋቸው መናገር እንዲሁም ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የማይችሉበት አስከፊ ስርዓት ለመገርሰስ ውድ ህዝቦች ህይወት መስዋዕት በማድረጋቸው ዛሬ ላለንበት የሰላም የዲሞችራሲና ልማት ሂደት አብቅተውናል ብለዋል፡፡በ19 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የተደረጉ የመልካም አስተዳደር ልማቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በዓንድነት እንዲሰራ አቶ ኃይሉ ጥሪያቸውን አቅርቀበዋል፡፡
      በቀበሌዎቹ በተከበረው በዓል ላይም ይህንኑ ዓይነት መልዕክቶች የተንፀባረቁ ሲሆን ድሉን የሚያስታውሱ የግጥም ስራዎች ለታዳሚዎች ቀርበዋል፡፡
 
ሪፖርተር
 ራዚቃ ዲኖ
09 13 04 99 33
   
 
 ግንቦት 30 2002 ዓ.ም
ግንቦት 24 2002ዓ.ም
የወጣቶች ማህበር ስልጠና ሰጠ 
       የቂርቆስ ክፍለከተማ ወጣቶች ማህበር ዶት ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባባር ለማህበሩ አባላት በቢዝነስ ልማት፤ህይወት ክህሎትና መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና ሰጠ፡፡
      የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማህበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ዮሀንስ አለሙ እንደገለፀው በስልጠናው ከ500 በላይ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን አለማውም የወጣቶችን በህይወት ክህሎትና በቢዝነስ ልማት እንዲሁም ኮምፒውተር እውቀታቸውን ከፍ ለማድረግ ነው፡፡
     በዚህም ወጣቶች ላሉባቸው መሰረታዊ ችግሮች መፍትሔውን እራሳቸው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ነው ያለው፡፡ በክረምት መርሀ ግብርም የአሁኑን ስልጠና ጨምሮ ወጣቶች በመልካም አስተዳደር ፤በችግኝ ተከላ፤ፅዳትና ስፖርት እንዲሳተፉ ለማድረግ ታቅዷል እንደ ወጣት ዮሀንስ ገለፃ፡፡
      የስልጠናው ተሳታፊ ወጣት ያሬድ መልኩና ወጣት ሮዚና ወርቁ ስልጠናው ቢዝነስ ላይና ህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ስራን በራሳችን ፈጥረን ለመስራት የሚያስችለንን ግንዛቤ ያስገኛል ብለዋል፡፡ ስልጠናውን ላላገኙ ወጣቶችም እንዲሰጥ በመጠየቅ ጭምር፡፡
      ስልጠናውን የሰጡት በዶት ኢትዮጵያ የስልጠናዎች አሰልጣኝ ዶ/ር ሳሙኤል ክብሩ በበኩላቸው ወጣቶች በቂ ስልጠና ካገኙ የተሻለ ስራዎችን መስራት እንደሚችሉ በማሰብ ስልጠናውን መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
     ስልጠናው ለ3 ወራት የሚቆይ መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞች የራሳቸውን ቢዝነስ ዕቅድ እንዲያወጡ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡ 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ 0913049933
ግንቦት 24 2002ዓ.ም
የጤና ጽ/ቤት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዙርያ ስልጠና ሰጠ
     የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዋና የስራ ሂደት ለ3ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
       የስልጠናው ተሳታፊዎች ከየቀበሌዎቹ የተውጣጡ የጤና ኤክስቴነሽን ሱፐርቫይዘሮችና የበጎ ፈቃደኞች ናቸው፡፡
    ስልጠናውን በንግግራቸው የከፈቱት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ዶ/ር እታገኝ ጌታሁን እደተናገሩት የኤች.አይ.ቪ ኤድስን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው እንቅስቃሴ በተለይ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ትምህርት በመስጠትና የህክምና አገልግሎት ስራ ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡
      ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ዜጎች በተለያዩ የህክምና ተቋማት የህክምናና የመድሀኒት አቅርቦት እንደሚሰጥ ገልፀው በቤት ለቤት ማስተማር ስራው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለመሰማራት የተዘጋጁት በጎ ፈቃደኞች ለፕሮግራሙ ስኬታማነት እያደረጉ ያሉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡
     በክፍለ ከተማው የጤና ጽ/ቤት የኤች.አይ.ቪ አድስ መከላከልና መቆጣጠር ዋና የስራ ሂደት መሪ ወ/ሮ ሳባ ካሳዬ በበኩላቸው የስልጣናው ተሳታፊዎችከህብረተሰቡ የወጡ በመሆናቸው ከስልጣናው በኋላ ለ3ወራት ያህል የየቀበሌዎቹ ነዋሪዎችን በማስተማር ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ የፕሮግራሙን ጠቀሜታ በመገንዘብ ለበጎ ፈቃደኞቹ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ነው ወ/ሮ ሳባ የጠየቁት፡፡  
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ 0913049933


ግንቦት 18 2002ዓ.ም
 
BSC- automation ስልጠና
  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የማስፈፀም አቅም ግንባታ ጽ/ቤት የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና ተግባራዊ እያደረጉ ላሉ ጽ/ቤቶችና ቀበሌ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት የማስፈፀም አቅም ግንባታ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኑሩ ጅብሪል እንደተናገሩት ስልጠናው የተዘጋጀው ሰልጣኞች በሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና ተግባራዊ ከሚደረጉት ደረጃዎች መካከል አንዱ በመሆነው አውቶሜሽን ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡
የአውቶሜሽን ስልጠናውን የወሰዱና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚስዱ ሰልጣኞች በስልጠናው እንደተሳተፉ የገለፁት የስራ ሂደት አስተባባሪው በአሰራሩ ላይ የሚታዩ ብዥታዎችን ለማጥራትም የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን ከተከታተሉ ሰልጣኞች መካከል የቀበሌ08/09 አቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ማሞ በበኩላቸው ስልጠናው የተሰጠው በሙከራ ትግበራ ላይ ባለንበት ወቅት በመሆኑ በትግበራው ላይ ያሉ ችግሮችንና መልካም ልምዶችን የምናይበት ነው ብለዋል፡፡
ሌላዋ የስልጠናው ተሳታፊና የቀበሌ 08/09 የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አስተባባሪ ወ/ሪት እፀገነት ደመቀ በበኩሏ ስልጠናው የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና አንድ አካል የሆነው አውቶሜሽን ላይ ያተኮረ ሲሆን አሰራሩን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ያደርገዋል ነው ያለችው፡፡
ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ግንቦት 15 2002 ዓ.ም
ዜና ምርጫ
ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 19 ስር የሚገኙ የቀበሌ04 የምርጫ ጣቢያ ታዛቢች፤የእጩ ወኪሎችና መራጮች ገለፁ፡፡
በየምርጫ ጣቢያዎቹ ተዘዋውረን ካነጋገርናቸው የምርጫ ታዛቢዎች መካከል መምሬ ሺበሺ ፍሰሀ እንደገለፁት ከድምፅ አሰጣጡ በፊት ለምርጫው አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንና ኮሮጆውን ፈትሸን ቦዶ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ የምርጫው ሂደትም ፍፁም ግልፅነት የተሞላበትና ሰላማዊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በቀበሌው የምርጫ ጣቢያ 4 የኢህአዴግ እጩ ወኪል አቶ ዘለቀ በበኩላቸው ምርጫውን ለመምረጥ የሚመጡ መራጮች ያለምንም ግፊት በነፃነት እየመረጡ እንደሚገኙ አስተውለናል፡፡
የምርጫ ካርዷ ጠፍቶባት የቀበሌ መታወቂያዋና የመራጮች መዝገብ ተመሳክሮ እንደመረጠች የገለፀችልን መራጭ መቅደስ እናቱ የነበረውን የምርጫ ሂደት ጥሩ እንደነበር ገለፀች፡፡
በምረጫ ጣቢያው ሊመርጡ የመጡ ሌሎች መራጮችም ምርጫው ሰላማዊና ነፃ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ 
በወረዳ 19 ቀበሌ 04 ስር 11 የምርጫ ጣቢዎች የሚገኙ ሲሆን በቀበሌውም 4ሺ 331 መራጮች ለመራጭነት የሚስችላቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡ 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ- 0913049933
መኮንን ነጋሽ- 0913047596
ግንቦት 15 2002ዓ.ም
በቂርቆስ ክ/ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ ድምጹን በሰላማዊ መንገድ እየሰጠ ይገኛል፡፡
በየምርጫ ጣቢያዎቹ የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈጻሚዎች ከማለዳው 10፡30 ሰዓት ጀምረው ነው ወደ ስራ የገቡት፡፡ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶና የድምጽ መስጫ ፖስተሮች ኮሮጆዎች በታዛቢዎች ፊት ከተከፈቱ በኋላ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች ቃለ ጉባዔ ተፈራርመዋል፤ ለመራጮችም መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ መራጮች እንደየ ቅደም ተከተላቸው ድምጽ መስጠት የጀመሩት፡፡
ወጣት በድሩ ኸይሩ የተባለው የቀበሌ 17/18 መራጭ እንደተናገረው እርሱ በመምረጡ የሚመርጠው ፓርቲ አሸናፊ ሊሆን እንደሚችል ያምናል፡፡የእያንዳንዱ ሰው ድምጽም ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ወጣት በድሩ የተናገረው፡፡
አቶ ኃይሉ በርሔ በስራ ምክኒያት ክፍለ ሀገር ነበሩ፡፡ የመራጭነት መብታቸውን ለመጠቀም ትናንት ማምሻውን ከክ/ሀገር መጥተዋል፡፡ ዛሬ በማለዳ በመነሳት ነው በቀበሌ 01/19 በሚገኘው አብዮት እርምጃ ት/ቤት የምርጫ ጣቢያ የተገኙት፡፡ እርሳቸውም በመምረጣቸው በሀገሪቱ ለውጥ ይመጣል ብለው እንደሚያምኑ አቶ ኃይሉ ተናግረዋል፡፡
በቀበሌ 15/16 የምርጫ ታዛቢ የሆኑት ወ/ሮ አበበች እሸቴ እንደገለጹት እስካሁን ያለው የምርጫ ሂደት ሰላማዊና ግልጽ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
እኛም ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ምርጫው በሁሉም ጣቢያዎች በሰላም እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ
0913278575
ግንቦት 15 2002ዓ.ም
በዛሬው ዕለት የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንደነበር አንዳንድ መራጮችና የምርጫ ታዛቢዎች ገለጹ፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 10 እና 11/12 የሚገኙ የተለያዩ መራጮችና የምርጫ ታዛቢዎች እንዲሁም የፓርቲ ተወካዮች ታዛቢዎች እንደተናገሩት ምርጫው ሰላማዊና ግልጽ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ውሏል፡፡
በወረዳ 21/22 ምርጫ ጣቢያ 1 መኢአድን ወክለው ምርጫውን ሲታዘቡ ያገኘናቸው አቶ ያሬድ አበራ እንደገለጹልን የምርጫው ሂደት ከሌሊት 10፡30 ጀምረው ሲታዘቡ ቆይተዋል በታዛቢነት በቆዩባቸው ሰዓቶች ሁሉ ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል በዚህ መልኩ በተካሄደው የምርጫ ሂደት ያሸነፈውም ሆነ የተሸነፉ ፓርቲዎች ለህዝብ ድምጽ መገዛት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ 
ወ/ሮ መብራት ኃይሉና ወጣት ጌታቸው በደዊ የተባሉት መራጮች በበኩላቸው በሰላማዊ መልኩ ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በምርጫው ሂደትም መደሰታቸውን ገልጸዋል በዚህ ሁኔታ የመረጡት ፓርቲ ቢያሸንፍ የሚደሰቱ ቢሆንም ቢሸነፍ ደግሞ የብዙሃኑን ድምጽ ማክበር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በወረዳ 21/22 የምርጫ ጣቢያ 1 ኃላፊ ወ/ሮ ይኩኑ ወርቅ ታደሰ እንደተናገሩት ምርጫው የህዝብ ታዛቢዎችና የእጩ ተወዳዳሪ ተወካዮች በተገኙበት የተጀመረ ሲሆን መራጮች በከፍተኛ ቁጥር ወደ ጣቢያው በመምጣት ድምጻቸውን ሰጥተዋል በድምጽ አሰጣጥ ሂደቱም የገጠማቸው ችግር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
በምርጫ ሂደት ማሸነፍና መሸነፍ የተለመደ ነው ያሉት ኃላፊዋ የተሸነፉ ፓርቲዎችም የህዝቡ ድምጽ እንዲከበር ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡  
  ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ
0913278575
ግንቦት 15 2002ዓ.ም
መራጮችም ሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት በፀጋ መቀበል እንደሚገባቸው በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 18 ድምፃቸውን የሰጡ መራጮች ገለፁ፡፡
አቶ ደረጄ አባተ ይባላሉ በወረዳ 18 ምርጫ ጣቢያ 3 ድምፃቸውን ሰጥተው ሲወጡ እንደገለፁልን ከሆነ ድምፃቸውን የሰጡት ያለምንም ተፅዕኖና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው፡፡ የምርጫው ውጤትም ሲገለፅ የትኛውም መራጭ ሆነ የፖሊቲካ ፓርቲ በፀጋ ሊቀበለው ይገባል ነው ያሉት፡፡ 
በወረዳ 18 መድረክን ወክለው ምርጫውን የታዘቡት አቶ በቀለ ዲሳሳ በበኩላቸው በምርጫ ጣቢያው ሰላማዊና ነፃ በሆነ መልኩ ህዝቡ ድምፁን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ ይፋ የሚያደርገውን ውጤት በመቀበል ረገድም የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ መራጩ ህዝብ ውጤቱን ሊቀበለው ይገባል ነው ፡፡
በምርጫው ላይ እመጫት ሴት መሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ የሺእመቤት ደመቀም በምርጫው በመሳተፌ ለወደፊት ይመራኛል ብዬ የምለውን ፓርቲ ለመምረጥ ችያለሁ ብለዋል፡፡
በምርጫ ጣቢያዎች ከሀገር ውስጥ ከሲቪክ ማህበራትና ነዋሪዎች ከተወከሉ ታዛቢች በተጨማሪ አውሮፓ ታዛቢዎች ቡንም ምርጫውን ሲታዘቡ ለማየት ችለናል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
መኮንን ነጋሽ

በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 20 እና 21/22 ምርጫ ክልል አራተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ከማለዳዉ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የምርጫ ታዛቢዎች ና አስፈፃሚዎች በተገኙበት የድምጽ አስጣጥ ስነ ስርዓት ያለ ምንም እንከን እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ለምርጫዉ የምያስፈልጉ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ መሟላታቸዉና የድምጽ መስጫ ኮሮጆ ባዶ መሆኑ ከተረጋገጠ በኃላ መራጩ ህዝብ ተራውን ጠብቆ ይበጀኛል የሚለውን ፓርቲ እንዲመርጥ ተደርጓል፡፡
በቀበሌ 08/09 የወረዳ 20 ምርጫ ጣብያ አስተባባሪ የሆኑት አቶ መኮንን ገ/ስላሴ እንደተናገሩት ከምርጫ ቦርድ የተላከላቸውን ቁሳቁስ ኮሮጆን ጨምሮ ለታዛቢዎችና ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ካሳዩ በኃላ ቃለ ጉባኤ በመፈራረም ማለዳ 12 ሰዓት ላይ የድምጽ አሰጣጥ እንደጀመሩ ገልፀው እስካሁን ባለው ሂደት ምርጫው ፍጹም በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በዚሁ ምርጫ ጣብያ የህዝብ ታዛቢ የሆኑት አቶ ተመስገን ኃ/ስላሴ እንደተናገሩት ምርጫው በደንቡ መሰረት እየተካሄደ መሆኑን ከገለፁ በኃላ ዘጠኝ የሚሆኑ መራጮች ካርድ ስለጠፋባቸው መታወቂያቸው መዝገብ ላይ ከሰፈረው ማስረጃ ጋር በማመሳከር ትክክለኛ ሆኖ ስለተገኘ እንዲመርጡ ተደርጓል ብለዋል፡፡ 
ድምጻቸውን ሲሰጡ ካገኘናቸው መካከል ወ/ሮ ፀዳለ ከበደ እንደተናገሩት ከምርጫ አስፈጻሚዎች በተሰጣቸው መግለጫ መሰረት ያለምንም ተፅእኖ ይበጀኛል ያሉትን ፓርቲ መርጠዋል፡፡ እንደ ወ/ሮ ፀዳለ በምርጫው የተሸነፈ ፓርቲ የህዝብ ውሳኔን ተቀብሎ ካሸነፈው ፓርቲ ጋር ለአገር እድገት መስራት አለበት ይላሉ፡፡ 
ወጣት መሳይ ተክለወልድ በበኩሉ አንድ ድምጽ ትልቅ ዋጋ እንዳለው በመገንዘብ ድምፁን ለሚፈልገው ፓርቲ እንደሰጠ ተናግሯል፡፡ ወጣቱ የምርጫ ጣብያዎች ቁጥር በመጨመሩ በወረፋ ሳይጉላላ መምረጥ በመቻሉ መደሰቱንም ገልጿል፡፡
በመጨረሻም በክ/ከተማው በሚገኙ የምርጫ ጣብያዎች 116,483 ህዝብ ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ መውሰዱን ለማወቅ ተችሏ፡፡
ሪፖርተር
አምሳሉ ታደሰ
ግንቦት 15 2002ዓ.ም
4ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን በቀበሌ02/03 የቀድሞ ቀበሌ35 ወረዳ 18 የህዝብ ታዛቢዎች፤የእጩዎች ወኪሎችና መራጮች ገለፁ፡፡
በወረዳ 18 ቀበሌ35 የምርጫ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ውቡ ዳኛው እንደገለፁት ለምርጫው አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ኮሮጆዎች፤የምርጫ ወረቀቶችና ሌሎች ግብዓቶች መሟላቱን በቃለ-ጉባኤ በመፈራረም ስራቸውን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ጀመረዋል፡፡ በምርጫ ጣቢያ 3 ላይ ያልተስታከካለ ቃለጉባኤ በመኖሩ መዘግየት ከመታየቱ በስተቀር ምርጫው በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀበሌው ምርጫ ጣቢያ 1 መርጠው ሲወጡ ያገኘናቸው መራጭ ወ/ሮለምለም ገብሬና ወ/ሪት አባይነሽ ለገሰ እንደተናገሩት ደግሞ ከጠዋቱ ለመምረጥ በመጡበት ጊዜ አንስቶ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም የማንም ተፅእኖ ያልነበረበት ነው ብለዋል፡፡
በምርጫ ጣቢያዎች ዕጩዎችን ወክለው የተገኙና በምርጫጣቢ 4 በታዛቢነት እስልምና ከሀይማኖት ተቋም የተወከሉ ታዛቢ ሼህ መሀመድ ኑርዘይድ በበኩላቸው ምርጫውን ለመታዘብ መምጣታቸውን ገልፀው እስካአሁን ያሉ ሂደቶች ሁሉ ምርጫው በዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ገልጣ ለምረጫ አስፈለጊ የሆኑ ግብዓቶች መሟላታቸውን በቃለጉባኤ በመያዝ ስራቸውን እንደጀመሩ ገልፀዋል፡፡
በወረዳ አስራ ስምንት 52 የምርጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ 31ሺ 331 መራጮች ተመዘገበዋል፡፡ በቀበሌ 02/03 ብቻ 12ሺ 430 መራጮች ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል፡፡ በየምርጫ ጣቢያዎቹ የመድረክ፤የመአህድና የኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ ወኮሎች የተገኙ ሲሆን ከሲቪክ ማህበራት፤ከሀይማኖት ተቋማትና ነዋሪዎች የተወከሉ ታዛቢዎችም ተገኝተዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
መኮንን ነጋሽ
ግንቦት 14/2002
የምርጫ ጣቢያዎች ቅድመ ዝግጀት ማጠናቀቃቸውን ገለጹ

በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 18 እና የወረዳ 15 ምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች ለምርጫ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ የመረጮች መዝገቦች ድምጽ መስጫ ፖስተሮች ቀለሞች እንዲሁም የተለያዩ የምርጫ ቁሳቁሶች ወደየምርጫ ጣቢያዎቹ ተሰራጭተዋል፡፡
የወረዳ 18 ምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ታደሰ አጽበሃ ቁሳቁሶቹ ለየምርጫ ጣቢያዎቹ ሲያሰራጩ እንደተናገሩት በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የሚስጥር ድምጽመስጫ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ቀለሞችመዝገቦችና ኮሮጆዎች ሙሉ በሙሉ ለሁሉም ጣቢያዎች ተከፋፍለዋል፡፡
የወረዳ 15 የምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ታዲዎስ አምዴ በበኩላቸው የምርጫው ሂደት የተሳካ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ተጠናቀዋል በወረዳው በሚገኙ 42 የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች ተሰራጭተዋል የሚስጥር ድምጽ መስጫ ቦታዎ ተዘጋጅተዋል፡፡
በወረዳ 18 የምርጫ ታዛቢ የሆኑት ወ/ሮ የዘርንሽ አስፋው እንደተናገሩት የምርጫ ቁሳቁሶቹ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ በታዛቢዎች ፊት መሆኑን ተናግረው እስካሁን ያለው ሂደትም ግልጽና ተጠያቂነት የሞላበት አሰራር መሆኑን ተናጋረዋል፡፡
በየምርጫ ጣቢያው የሚገኙ የምርጫ ጣቢያ ኃላፊዎችና ታዛቢዎችም ምርጫውን ለማስፈጸም ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡
መራጮች በነገው ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምረው በየጣቢያው በመገኘት ድምጽ መስጠት የሚችሉ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡  
ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ


ግንቦት 12 2002ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለከተማ የቀበሌ11/12 ጽ/ቤት ተመረቀ፡፡
በቀበሌ ጽ/ቤቱ ምርቃት ስነስርዓት ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቀበሌ 11/12 የዲዛይንና ግንባታ ሬጉላቶሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሳ ራህመቶ ቀበሌው የመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥን ተግባራዊ ባደረገባቸው ጊዜያት በኪራይ ይገለገል እንደነበር አስተውሰው የራሱን ጽ/ቤት መገንባቱ አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በግንባታው የተሳተፉት የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ደግሞ ለግንባታው በጥራትና በጊዜው መጠናቀቅ አስተዋፅኦ እንዳበረክቱ የገለፁት ኃላፊው የቀበሌው መገንባት የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ያደረገውን አስተዋፅኦ ያሳያል ነውያሉት፡፡
የቀበሌ 11/12 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ስዩም ሽመልስ በበኩላቸው በሰኔ 14 2001 ዓ.ም መሰረቱ ተጥሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት መብቃቱ በየደረጃው የነበሩት አመራሮች የኮንስትራክሽን ሰራተኞችና ነዋሪው ባደረጉት እንቅስቃሴ በመሆኑ ነዋሪው ያሳየውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ቢያ ራያ ባደረጉት ንግግር እንዳሉትም የቀበሌው ነዋሪ የሚፈልገውን ተገልጋይ ተኮር አሰራር አጠናክረው መቀጠል የአስታዳደሩ ሰራተኞችና አመራሮች ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
የቀበሌ ጽ/ቤቱን የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙኘት ኃላፊ አቶ ሬድዋ ሁሴን የቀበሌው ጽ/ቤት መገንባት ለበርካቶች የስራ ዕድል የፈጠረው የጥቃቅንና አነስተኛ ውጤት በመሆኑ መንግስት ለቀረፀው የጥቃቅንና አነስተኛ ፓኬጅ ውጤታማነት የሚሳይ ነው ብለዋል፡፡ 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933  
11/09/02ዓ.ም.
ኢህአዴግ ብዙሃኑን የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረጉን ገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 21/22 ምርጫ ክልል ኢህአዴግን ወክለዉ የቀረቡ እጩ ተወዳዳሪ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 13/14 ከህብረተሰቡ ጋር በገነት ሆቴል አዳራሽ የመዝጊያ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄዱ፡፡
በቅስቀሳዉ ወቅት አቶ ሰለሞን እንደገለፁት በኢህአዴግ የሚመራዉ መንግስት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ በመፍታት የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችለዋል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ሰለሞን ገለጻ በከተማችን የሚታየዉን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተሰሩ ሲሆን እንዲሁም የስራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ ብዙ ዜጎች በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፍ ተሰማርተዉ ትልቅ እምርታ አሳይተዋል፡፡
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማይ ብርሃነ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ኢህአዴግ የህዝቡን የዴሞክራሲ ስርዓት ጥማት ለማርካት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስገንዝበዉ የተጀመሩት የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸዉ ሰፊዉ ህዝብ ከኢህአዴግ ጎን እንዲሰለፍ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል፡፡ 
አንዳንድ የቅስቀሳዉ ታዳሚዎች አስተያየታቸዉን እንደሰጡት ኢህአዴግ በርካታ በአይን የሚታዩ የልማት ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ አስታዉሰዉ ስለዚህም የበለጠ የልማቱ ተጠቃሚ ለመሆን ግንቦት 15 በሚካሄደዉ ምርጫ ኢህአዴግን ለመምረጥ እንደተዘጋጁ ና ምርጫዉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸዉን ለመወጣት መዘጋጀታቸዉን ገልፀዋል፡፡
ሪፖርተር
አምሳሉ ታደሰ

  ግንቦት 11 2002ዓ.ም

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 20/21ና የ17/18 ቀበሌ ነዋሪች ኢህአዴግን በመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
የድጋፍ ሰልፉን ያካሄዱት በቀበሌው የሚኖሩ ነዋሪዎች፤የወጣት አደረጃጀቶችና ሌሎች የየቀበሌዎቹ ነዋሪች ናቸው፡፡
የድጋፍ ሰልፉን በ20/21 ነዋሪዎች ሲያካሂዱ በወረዳ 18 የሚወዳደሩትን የኢህአዴግ እጩ ተወዳዳሪ ኢንጂነር አለማየሁ ተገኑ ኢህአዴግ ለሰላምና ለልማት የቆመ በመሆኑ ህዝቡ ኢህአዴግን እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በካዛንቺዝ አካባቢ እየተዟዟሩ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ የገለፁት የ17/18 ቀበሌ የወጣት የሴቶች አደረጃጀቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል በጥርብ ድንጋይ ስራ ላይ የተሰማራቸው ወጣት እንዳለች ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ባዘጋጀልኝ የስራ ዘርፍ ውጤታማ በመሆኔ ኢህአዴግን እምርጣለሁ ብላለች፡፡
በወረዳ 15 የሚወዳሩት የኢህአዴግ እጩ ወ/ሮ በላ|ይነሽ ተክላይም የወጣቶችንና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖሊቲካዊ ችግሮች የሚፈታውን ኢህአዴግን እንዲመርጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በሁለቱም ቀበሌዎች የነበሩት ሰልፈኞች መጪው ዘመን ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው፤ ኢህአዴግ ልማት ነው፤ ስራ አጥነትና ድህነትን በመቅረፍ ላይ ያለውን ኢህአዴግ እንምረጥ የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933 
ግንቦት 11 2002ዓ.ም
ኢህአዴግ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄደ
  የተጀመረውን የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መራጩ ህብረተሰብ ኢህአዴግን እንዲመርጥ ተጠየቀ፡፡
  የቂርቆስ ክ/ከተማ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በክ/ከተማው የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ ቅስቀሳው የተካሄደው ከክ/ከተማው ኢህአዴግ ጽ/ቤት በመነሳት በክ/ከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ነው፡፡
በተመሳሳይ ዜናም በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበሌ 08/09 በወረዳ 20 እና 23 የሚወዳደሩ የኢህአዴግ እጩዎች ወ/ሮ ብርነሽ አባይና ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከቀበሌው ነዋሪዎች ጋር ተዋውቀዋል፡፡ 
  በቄራ አደባባይ በተካሄደው የቅስቀሳ ፕሮግራም ላይ የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ ሉሌ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ኢህአዴግ ወደ ምርጫው ሲገባ ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆንና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒ ማድረግ እንደ መንግስት የያዛቸው ዓላማዎች ሲሆኑ እንደ ተወዳዳሪ ፓርቲ ደግሞ በምርጫው አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ማሸነፍ የሚሉ አላማዎችን ይዞ ነበር የተነሳው፡፡
  የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞ በበኩላቸው ድርጅታቸው ኢህአዴግ ትክክለኛ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመንደፍ ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ወጣቶችና ሴቶችም በፖለቲካ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድርጅታቸው ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡
  የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች እስካሁን ያሳዩትን አጋርነት የምርጫ ካርዳቸውን ለኢህአዴግ በመስጠት እንዲያረጋግጡ ወ/ሮ አስቴር ጠይቀዋል፡፡ 
ሪፖርተር 
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75

ግንቦት 09 2002ዓ.ም 
የነዋሪዎች ፎረም
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ፎረም 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ፡፡

ፎረሙ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኃ/ማሪያም እንደተናገሩት የነዋሪዎች ፎረም አባላት በሀገሪቷ ልማት፤መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ሁሉ ምርጫው ሰላማዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ እንዲሆንም ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡

የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ችግሮችም እንዳይፈጠሩ ከነዋሪዎች ጋር በህብረት ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት፡፡

የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነ ብርሀነ በበኩላቸው በ5ዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በየትምህርት ቤቶችና በሌሎች አካባቢዎች የፀጥታ ምክር ቤቶች መዋቀራቸውን ገልፀው ይህም ምርጫውን ሰላማዊ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡

የፎረሙ ስራ አስፈፃሚ አባልና የመልካም አስተዳደር ሰብሳቢ አቶ ምኡዝ ገ/ህይወት እንዳሉትም ፎረሙ በሀገሪቷ ለሚካሄዱ የልማት ተግባራት ቀጣይነት ምርጫው ፍፁም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማድረግ በስፋት ተንቀሳቅሷል ነው ያሉት፡፡

ፎረሙን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ስለምርጫው ሰላማዊነት የሚገልፅ ባለ7 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
0913049933

ግንቦት 07 2002ዓ.ም
የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቀበሌ13/14 ኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች በግንቦት 15 2002 ዓ.ም ምርጫ ማራጩ ህዝብ ኢህአዴግን እንዲመርጥ ቀሰቀሱ፡፡
 
በቅስቀሳው የኢህአዴግን የምርጫ ምልክት የሚያሳዩ በርካታ መኪናዎችና መፈክሮች የነበሩ ሲሆን አባላቶቹ ኢህአዴግን መምረጥ ልማትን መምረጥ ነው፤ኢህአዴግን መምረጥ የተጀመሩ ልማቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማስቻል ነው፤የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ በቀበሌው ቀጣና በማዟዟር የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂደዋል፡፡
 
በተመሳሳይም በወረዳ 18 የሚወዳደሩት የኢህአዴግ እጩ ኢ/ር አለማየሁ ተገኑ በቀበሌ 20/21 ለሚኖሩ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡን ቅስቀሳ ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት ኢህአዴግ ብሔር ብሔረሰቦች በሰላም በመከባበርና በመተሳሰብ እንዲኖሩ አስችሏል፤በየጊዜው የሚመረቁና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የሀይል ተቋማት የኢህአዴግን የልማት መስመር ያሳያሉ ብለዋል፡፡
 
ኢህአዴግ ቢመረጥ የተጀመሩት የልማት መልካም አስተዳደርና ሰላም በሀገራችን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያስችላል ብለዋል፡፡ ህዝቡ ድምፁን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ በመጠየቅ ጭምር፡፡
 
በእለቱ ከምርጫ ቦርድ የተወከሉ አካለትም ታዛቢዎች በምርጫው እለት ሊያደደርጉት ስለሚገባቸው ስነምግባሮች አስረድተዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
ቀን 06/09/02
የቂርቆስ ክፍለከተማ ግብርና ኤክስቴንሽን በዘርፉ በመስራት ላይ ላሉና መሰማራት ለሚፈልጉ አካላት ለ5 ቀናት የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ ስልጠናው የዘርፉን ጠቀሜታና ምንነት የማስገንዘብ ታለመ መሆኑም ተገልፃDል፡፡
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የከተማ ግብርና ኤክስቴንሽን የስራ ሂደት መሪ አቶ ደስታ ሎሬንሶ የዘርፉን ምንነትና ጠቀሜታ ሲያስረዱ እንደገለጹት የከተማ ግብርና በትንሽ ቦታ ብዙ ምርት የማምረት ዘዴን በመከተል የሚሰራ የአዝርዕት፤የአትክልትና የእንስሳት እርባታ ተዋፅኦ ልማት ነው፡፡
 
እንደ አቶ ደስታ ገለፃ የከተማ ግብርና ዘርፎች የአትክልት የአዝርዕትና የፍራፍሬ ልማት፤የእንስሳት እርባታ ተዋፅኦ የአፈርና ውሀ ጥበቃ የደን ልማትና የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ሲሆኑ በከተማም የምግብ እህል ዋጋን ለማረጋገት ይረዳሉ ብለዋል፡፡
 
ዘርፉን ለማጠናከር መንግስት ለስራው የሚያስፈልጉ ቦታዎችንና ስልጠናዎችን ማዘጋጀት እንዳለበት ጠቁመው ለህብረተሰቡና ለአንቀሳቃሾች የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
በክፍለ ከተማው የከተማ ግብርና ኤክስቴንሽን የእንስሳት እርባታ ተዋፅኦና መኖ ልማት ኦፊሰር ወ/ሮ አልማዝ ታደሰ በበኩላቸው ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በዶሮ፤የወተት ከብትና የንብ እርባታ አሰራር ላይ ነው ብለዋል፡፡
 
ለዘርፉ ውጤታማነት የግንዘቤ ማስጨበጫዎችን ከመስጠት ባሻገር የምክር አገልግሎት መስጠትና ቦታዎችን የማመላከት ስራ እየሰሩ እንደሚገኙም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
 
ሪፖርተር
 
ራዚቃ ዲኖ    0913 04-99-33       
ቀን 06/09/02
ኢህአዴግ የጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ፡፡መራጩ ህዝብ ኢህአዴግን በመምረጥ እንዲተባበርም ተጠይቋል፡፡
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 15 የሚወዳደሩ የኢህአዴግ እጩ ተወዳዳሪ ወ/ሮ በላይነሽ ተክላይ ከቀበሌ 17/18 ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
 
በውይይቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውጭ ግንኙነት ኃላፊና በም/ቤት የህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በነበሩት ስርዓቶች የአገራችን ህዝብ መሪውን የመምረጥ መብት አልነበረውም፡፡ ያለ ምርጫውና ያለ ፍላጎቱ በጉልበት የበላይነት ያላቸው መሪዎች ለበርካታ አመታት ሲያስተዳድሩት ቆይተዋል በዚህም የህዝቡን መብት ያለገደብ ሲረግጡ መቆየታቸውን ነው ወ/ሮ አልማዝ የተናገሩት፡፡
 
በወረዳ 15 ኢህአዴግን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚወዳደሩት ወ/ሮ በላይነሽ ተክላይ በበኩላቸው ኢህአዴግ በስልጣን በቆየባቸው 18 አመታት በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ድጅታቸው በተለይም ከ1993 ዓ.ም ወዲህ በመንገድ ልማት በቤቶች ግንባታና እንዲሁም በገጠር በግብርና ዘርፎች በርካታ አበረታች ተግባራትን ፈጽሟል ብለዋል፡፡
 
በእለቱ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው በማለት ደማቅ የጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡
 
ሪፖርተር
 
ታሪኩ እንዳለ
 
09 13 27 85 75
ግንቦት 05 2002ዓ.ም
የቂርቆስ ክፍከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር ተወያየ፡፡ነዋሪዎች በመመሪያዎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ የሚያጎለብት ውይይት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በቂርቆስ ክፍለከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመሬት ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከተማ በቀለ እንደተናገሩት አዲስ አበባ ደረጃዋን የጠበቅችና የአለም አቀፍ ገፅታን የተላበሰች ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ በተጨማሪ ህጋዊነት ያላቸውንን የሌላውን ይዞታዎች ስርዓት የሚያስይዝ መመሪያ አውጥቷል፡፡
 
እንደ አቶ ከተማ ገለፃ በክፍለ ከተማችን ሰነድ አልባ ይዞታዎች ከ4 ሺ በላይ ሲሆኑ በንጉሱ ግዜ የነበሩትን ካርታዎች ጨምሮ ከ7ሺ በላይ መሆናቸውን ገልፀው ለነዚህ ይዞታዎች አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብና ህጋዊ ካርታ ለመስጠት ለመኖሪያ ቤቶች ትንሹ 75 ካሬ.ሜትር ሲሆን ለድርጅቶች ደግሞ 150 ካሬ ሜትር ነው ብለዋል፡፡
ይህም በቀድሞው መመሪያ ካርታ ለመስጠት 150 ካሬሜትር ይጠይቅ የነበረውን ወደ 75 ካ.ሜ ዝቅ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የክፍለከተማው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነ ብርሀነ በበኩላቸው በመመሪያው ዙሪያ የተዛባ አስተሳሰቦችን ለመቅረፍ የሚያስችል ውይይት በመሆኑ ነዋሪው ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በግልፅ እንዲወያይ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ከነዋሪዎችም በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን እኛን በመመሪያው ዙሪያ በማወያየታችሁ ተደስተናል፤በአንዳንድ ቀበሌዎች ላይ የመረጃ ስራ ሲሰራ ከቦታው እንነሳለን የሚል ስጋት አለን፤የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 
አስተዳደሩ በሰጠው ምላሽም በአንዳንድ ቦታዎች የሚደረጉ ጥናቶች በአካባቢው የሚገነቡ ግንባታዎች ለማጣራትና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታን በማስመልከት መሆኑን ገልፃDል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብም የከተማ አስተዳደሩ የሚያወጣውን ደንቦችና መመሪያዎች ከነዋሪዎች ጋር የሚያወያየው ነዋሪውን ያላሳተፈ ልማት ውጤታማ እንደማይሆን በማመኑ ነው ብለዋል፡፡ነዋሪዎችም ይህን ተገንዝበው ከአስተዳደሩ ጋር በጥምረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ- 0913049933
 
ግንቦት 04 2002 ዓ.ም
የቻርተር ስምምነት
    በቂርቆስ ክፍለከተማ የቀበሌ08/09 አስተዳደር የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናን በማስመልከት የስምምነት ቻርተር ከ6ጽ/ቤቶች ጋር ተፈራረመ፡፡
በ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ምርጥ አፈፃፀም ላሳዩ ፈፃሚዎችም ሽልማት ሰጥቷል፡፡
    የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘና ቻርተሩን ከስድስቱ ጽ/ቤቶች ጋር የተፈራረሙት የቀበሌው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኃይሉ ሉሌ እንደተናገሩት ተገልጋይ ተኮር የሆነውን የመሰረታዊ የአሰራር ለውጥ የሚያጠናክረና ለውጡ ያልደረሰባቸውን ሂደቶች የሚተካ ስርዓት ነው የሚዛናዊ የስራ አመራር ውቴት ምዘና፡፡
     በዚህም አገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሰብ ለማገልገል ፈፃሚው የተሳካ ስራ የሚሰራበት ነው ብለዋል፡፡
    የአዲስ አበባ አስተዳደር አቅም ግንባታ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሩ ሰሙር በበኩላቸው ስርዓቱ ስትራቴጂ ዪካሄድበት፤የሚተገበርበትና የሚመዘንበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አመራሩና ፈፃሚው በቁርጠኝነት ከተንቀሳቀሱ አገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሰብ የበለጠ ማርካት ይቻላል ነው ያሉት፡፡
   የተጀመረው መልካም አስተዳደርና ልማት እንዲቀጥልም ግንቦት 15 የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን ሰራተኞች የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ ዘሩ ጠይቀዋል፡፡
    በእለቱ የሚዛናዊ የስራ አመራር ውጤት ምዘናን ለመተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ቻርተር በዋና ስራ አስፈፃሚውና በስድስቱ ጽ/ቤት ኃላፊዎች መካከል የተፈረመ ሲሆን በ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ምርጥ ለሆኑና ዝውውር ላገኙ ፈፃሚዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
04/09/2002
 
የደኢህዴን 17ኛ ዓመት በዓል ተከበረ
    ኢህኢዴግ ለልማት ለመልካም አስተዳደርና ለሰላም በትጋት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡
   በቂርቆስ ክ/ከተማ የቀበሌ 04 የደኢህዴን ኢህአዲግ አባላትና ደጋፊዎች ደኢህዴን የተመሰረገበትን 17ኛ ዓመት በዓል አክብረዋል፡፡
    በሀዊ ሆቴል በተከበረው በዓል ላይ የቀበሌው የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ይደነቅ ቢተው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም የኢህአዴግ ጽኑ አቋም በመሆኑ ድርጅታቸው በትጋት እንደሚሰራ ነው አቶ ይደነቅ የተናገሩት፡፡
    የቀበሌው ደኢህዴን ኢሀዲግ ተወካይ ወ/ት መቅደስ መለሰ የድርጅቱን መልዕክት ሲያቀርቡ እንደገለጹት ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የስልጣን ጥያቄና የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንዲመልስ ለበርካታ ዓመታት የመረረ ትግል አድርጓል፡፡ የተጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ሰላም ወዳድ ወገኖች ሁሉ ኢህአዴግን በመምረጥ አጋርነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል፡፡
    በእለቱ የብአዴን የኦህዴድና የህወሃት አጋር ድርጅቶች የአጋርነት መግለጫ ያቀረቡ ሲሆን በአገራችን የተጀመረውን ልማት መልካም አስተዳደርና ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከደኢህዴን ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
   የብሄር ብሄረሰቦች ባህላዊ አለባበስና ውዝዋዜዎችም ለእይታ ቀርበዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
ግንቦት 03 2002ዓ.ም
 
     በቂርቆስ ክፍለከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የደንብ ማስከበርና መቆጣጠር ወሳኝ የስራ ሂደት በአስራአንዱም ቀበሌዎች ለሚገኙ የደንብ አስከባሪዎች፤ፖሊስ አካላትናለየቀበሌዎቹ ፍትህ ጽ/ቤት ሰራተኞች በምርጫ ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡
     ሰልጣኞች ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲያልፍ የድርሻውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም ተጠቁሟል፡፡
    ስልጠናውን በንግግራቸው የከፈቱት የክፍተካመው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደቦጭ እንደተናገሩት በሀገራችን በመካሄድ ላይ ያሉት የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ሰላም አስፈላጊ ነው፡፡
       በመሆኑም ህገ-ወጥ ተግባራትን ከማስቆም ጎን ለጎን ሰላምና ፀጥታን በማስከበር እረገድ የደንብአስከባሪዎችና የፖሊሶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ግንቦት 15 የሚካሄደው ምርጫም በሰላም እንዲጠናቀቅ በስፋት ሊንቀሳቀሱ እንደሚባ ጠቁመዋል፡፡
       ስልጠናውን የሰጡት በፍትህ ጽ/ቤት የደንብ ማስከበርና መቆጣጠር የስራ ሂደት ባለቤት አቶ በእውቀቱ ገበዩ በበኩላቸው የደንብ ማስከበር ስራው በ6 የህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የሚያተኩር ሲሆን ከህገ-ወጥ ተግባራቱ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ሰላምን የማደፍረስ ስራዎችን መቆጣጠር ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
     የደንብ አስከባሪዎች ከሌሎች አካላት ጋር ተቀናጅተው በህገ-ወጥ ተግባራት ላይ እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ፡፡
 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
 
ግንቦት 03 2002ዓ.ም
 
በቂርቆስ ክፍለከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የደንብ ማስከበርና መቆጣጠር ወሳኝ የስራ ሂደት በአስራአንዱም ቀበሌዎች ለሚገኙ የደንብ አስከባሪዎች፤ፖሊስ አካላትናለየቀበሌዎቹ ፍትህ ጽ/ቤት ሰራተኞች በምርጫ ዙሪያ የግማሽ ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡
     ሰልጣኞች ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲያልፍ የድርሻውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም ተጠቁሟል፡፡
    ስልጠናውን በንግግራቸው የከፈቱት የክፍተካመው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደቦጭ እንደተናገሩት በሀገራችን በመካሄድ ላይ ያሉት የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ሰላም አስፈላጊ ነው፡፡
     በመሆኑም ህገ-ወጥ ተግባራትን ከማስቆም ጎን ለጎን ሰላምና ፀጥታን በማስከበር እረገድ የደንብአስከባሪዎችና የፖሊሶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ግንቦት 15 የሚካሄደው ምርጫም በሰላም እንዲጠናቀቅ በስፋት ሊንቀሳቀሱ እንደሚባ ጠቁመዋል፡፡
     ስልጠናውን የሰጡት በፍትህ ጽ/ቤት የደንብ ማስከበርና መቆጣጠር የስራ ሂደት ባለቤት አቶ በእውቀቱ ገበዩ በበኩላቸው የደንብ ማስከበር ስራው በ6 የህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የሚያተኩር ሲሆን ከህገ-ወጥ ተግባራቱ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ሰላምን የማደፍረስ ስራዎችን መቆጣጠር ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
    የደንብ አስከባሪዎች ከሌሎች አካላት ጋር ተቀናጅተው በህገ-ወጥ ተግባራት ላይ እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ፡፡
 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
ግንቦት 01 2002 ዓ.ም
በምርጫ ዙሪያ የንግዱ ማህበረሰብ ተወያየ
4ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፤ፍትሃዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ በሚሆንበት ዙሪያ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተወያዩ፡፡
 
ውይይቱ በብሔራዊ ቲያትር አደራሽ በተካሄበደት በወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 15 የሚወዳሩትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ተክላይ እንደተናገሩት በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት የሀገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት ባደረገው እንቅስቃሴ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡
 
በዕዝ ኢኮኖሚ የሚመራውን የንግድ ስርዓት በነፃ ገቢያ በመለወጥ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ድረስ ያሉ ባለሀብቶች በነፃነት የሚሰሩበት የገቢያ ስርዓት ተዘርግቷል ብለዋል፡፡
 
ከ1983 በፊት የግል ባለሀብት እንደልቡ በግሉ መስራት እንደማይችል ያስታውሱት ኃላፊዋ በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ልማታዊ ባለሀብቶች በሀገሪቷ ልማት ውስጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ በማድረግ ላይ ነው ያሉት፡፡ኢህአዴግን በመምረጥ ልማቱንና እድገቱን እንዲያቀጥሉት በመጠየቅ ጭምር፡፡
 
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ ሰብሳቢ አቶ መላኩ በዙ በበኩላቸው 1984 4 የነበረው የባለሀብቶች ቁጥር በ2002 ዓ.ም ከ17 ሺ 800 በላይ መድረሱን ተናግረው ይህም የሚያሳየው መንግስት ለባለሀብቱ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ ነው ብለዋል፡፡
 
ከንግዱ ማህበረሰብም በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን ለባለሀብቶች እየተደረገ ያለው እገዛ ቢቀጥል፤መንግስት የሰራውን ልማት ህዝቡ እንዲያውቀው ማድረግ አለበት የሚሉት ሀሳቦች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 
ሚያዚያ 30 2002ዓ.ም
 
ወጣቶች በመፋጠን ላይ ያለውን የወጣቶች ዘርፍ ብዙ ተጠቃሚነት ለማስቀጠል ኢህአዴግን እንዲመርጡ የማዕድንና ኢነርጂ ሚ/ር ኢ/ር አለማየሁ ተገኑ ጠየቁ፡፡
 
በወረዳ 18 የሚወዳደሩት የማዕድንና ኢነርጂ ሚ/ር ኢ/ር አለማየሁ ተገኑና የአ/አ ከተማ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኃ/ማሪያም ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02/03 ወጣቶች ሊግ አባላት ጋር የተወያዩ ሲሆን የክፍለ ከተማው የትግራይ ተወላጅ ወጣቶችም በምርጫው ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
 
በቂርቆስ ክፍለከተማ የኢህአዴግ ጽ/ቤት የፖለቲካል ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቀለ ጉዲሳ እንደተናገሩት ውይይቱ 4ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የወጣቶች ሚና ለማስገንዘብና በምርጫው ስኬታማነት በኢህአዴግ የተያዙ 3 ግቦችን ከወጣቶችን ጋር ለመወያየት ታስቦ ነው፡፡
 
በወራዳ 18 የሚወዳዳሩት የማዕድንና ኢነርጂ ሚ/ር ኢንጂነር አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ወጣቶች ለውትድርና ብቻ በመጠቀም አስከፊ ተግባር የፈፀመውን የደርግ ስርዓት ለማስወገድ በጥንካሬ የታገሉት ወጣቶች ናቸው ብለዋል፡፡
 
ወጣቶቹ በከፈሉት መስዋዕትነት የተገኘውን ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስቀጠል ደግሞ ወጣቶች ኢህአዴግን በመምረጥ ሊያረጋግጡት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኃ/ማሪያም ይህንኑ ነው ያረጋገጡት በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ባለሀብቶች በሀገሪቷ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ለውጪ ንግድ ውጤታማነት እንዲሰሩ አድርጓል በማለት፡፡
 
ወጣቱም የኢህአዴግን ፖሊሲዎች ጠንቅቆ በማወቅ ምክንያታዊ መራጭ መሆን እንደለበት አስገንዝበዋል፡፡
 ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
ሚያዚያ 30 2002ዓ.ም
 
አዲሱ ካቢኔ የልማት ስዎችን ጎበኘ
 
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አዲስ የተዋቀረው ካቢኔ በክፍለ ከተማው እየተገነቡ ያሉትን የልማት ስራዎችን ጎበኘ፡፡
 
የወጣት ማዕከላት የጤና ጣቢያ ግንባታ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ወርክ ሾፕና የቀበሌ ማዕከል ግንባታዎች የተጎበኙ ሲሆን የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላት በማጠናከር መልካም አስተዳደርን እውን ማድረግ እንደሚቻል ተገልጻEል፡፡
 
የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢያ ራያ ከጉብኝቱ በኋላ አንደገለፁት በክፍለ ከተማው አዲስ የተዋቀረው ካቢኔ በክፍለ ከተማው የሚገነቡ ግንባታዎች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማወቅና ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ለመወሰን አንዲቻል ነው ጉብኝት የተደረገው፡፡ ከጉብኝቱ በኋላም በግንባታው ስራ ላይ መጓተት የሚስተዋልባቸውን ስራዎች ችግር በመለየት በወቅቱ እንዲጠናቀቁ ይደረጋል ብለዋል አቶ ቢያ ፡፡
 
በክፍለ ከተማው የዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤ የግንባታና ክትትል ንዑስ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሙሰማ ሙሳ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ ካለፈው ዓመት የተዛወሩና በዚህ ዓመት የተጀመሩ በቅርቡ ተጠናቀው አንደሚመረቁ ገልፀዋል፡፡ የተቀሩት 14 ፕሮጀክቶችም እስከ ጥቅምት 2003 ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ አቶ ሙሰማ አስረድተዋል፡፡
 
በክፍለ ከተማው የጤና ማዕከላት ወጣት ማዕከላት ትምህርት ቤቶችና የቀበሌ ማዕከላት በስፋት በማስገንባት በቀጣይ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አቶ ቢያ ገልፀዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
 
 ሚያዝያ 27/2002
 
 
የቂርቆስ ክፍለከተማ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን አካሄደ፡፡
 
ምክር ቤቱ 6 ጽ/ቤት ኃላፊዎችን ከስልጣን ያወረደ ሲሆን የ8 ጽ/ቤት ኃላፊዎችን ሹመትም አፅድቋል፡፡
 
ጉባኤው በተካሄደበት ወቅት የቂርቆስ ክፍለከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር እንግዳ አምዴ እንደገለፁት ምክር ቤቱ አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ያስፈለገው በሀገራችን በሚካሄደው 4ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመወያያትና የአንዳንድ ጽ/ቤት ኃላፊዎችን ሹም ሽረት ለማፅደቅ ነው፡፡
 
የክፍለከተማው የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ኪዳነ ብርሀነ እንዳሉት ደግሞ ምርጫ 2002 በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ የምክርቤት አባላት ሚና ከፍተኛ መሆን አለበት፡፡የመራጮች ምዝገባን በሰላም መጠናነቅ ያስወሱት አማካሪው የምክር ቤት አባላትና ህብረተሰቡ በፅጥታ ጉዳይ ላይ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
 
የምክር ቤቱን ሁለተኛ አጀንዳ ያቀረቡት የክፍለከተማው የመንግስት ተጠሪ አቶ ብርሀኑ ታደሰ እንዳሉት በክፍለከተማው በግዢ ስራ ላይ በሙስና የተጠረጠሩትን የፀረ ሙስና ኮሚሽን በእስር እንዲቆዩ ካደረጋቸው ግለሰቦች በተጨማሪ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ሊናራቸው ይችላል ብሎ ያላቸውን የጽ/ቤት ኃላፊዎች ከሷል፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቱ እነዚህ የጽ/ቤት ኃላፊዎች የአቅም ውስንነት አለባቸው የላቸውን ጨምሮ ክሱ ከኃላፊነታቸው ጋር አስቸጋሪ ይሆናል በማለቱ ከስልጣን እንዲወርዱ ሲወስን በምትካቸውና የተጓደሉ የጽ/ቤት ኃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል፡፡
 
በዚህም አቶ ቢያራያን ዋና ስራአስፈፃሚ፤አቶ ሰለሞን ደቦጭን ም/ዋናስራአስፈፃሚና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ፤አቶ አምሳሉ ተበጀን የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ፤አቶ ኪዳነማሪያም አረጋዊ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ፤አቶ ነስረዲን ሽፋ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ፤አቶ ጥበቡ በቀለን የንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ፤አቶ ቃሲም ተሾመን የዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊና ወ/ሮ እመቤት በቀለን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በማድረግ ሾሟል፡፡
 
ምክር ቤቱ የባህልና ቱሪዝም፤የጤና ጽ/ቤትና የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃለፊዎችን ለመሾም አስፈላጊውን ጥናት እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፡፡
 
ሪፖርተር
ራዚቃ ዲኖ
 
ሚያዚያ 27 2002ዓ.ም
 
 
 
የኢህአዴግ ዕጩ ከአባላትና ደጋፊዎቻቸው ጋር ተወያዩ
የወጣቱን ጉልበት ለሽብርተኛነትና ለሁከት ሊጠቀሙ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህዝቡ ሊከለክላቸው ይገባል ተባለ፡፡
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 08/09 የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ከወረዳ 20 ዕጩ ተወዳዳሪ ወ/ሮ ብርነሽ አባይ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
 
በአዲስ አበባ ቄራዎቻ ድርጅት አዳራሽ በወረዳ 20 ኢህአዴግን ወክለው የሚወዳደሩት ወ/ሮ ብርነሽ አባይ የድርጅታቸውን ዓላማና ማኒፌስቶ ለአባላት ሲያስተዋውቁ እንደተናገሩት ኢህአዴግ በ97 በአዲስ አበባ በህዝብ የተነፈገውን ድምጽ መነሻ በማድረግ በመላው አገሪቱ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል ውዥንብር በመንዛት ወጣቱን ለጥፋት ለመዳረግ የተናቀሳቀሱ ኃይሎች እንደነበሩ አስታውሰው በ2002 ምርጫም በተመሳሳይ መንገድ ስልጣን ለመያዝ የሚያኮበኮቡ ኃይሎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
 
ወጣቱን ትውልድ በጥፋት መስመር በማሰለፍ የአገሪቱን ሰላም ሊያደፈሪሱ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህብረተሰቡ ሊያቆማቸው ይገባል ብለዋል፡፡
 
የቀበሌው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ ሉሌ በበኩላቸው በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍንና ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የቀበሌው ነዋሪ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረግ ይተበቅበታል፡፡ በአካባቢው በህገወጥ መንገድ በመንቀሳቀስ ስልጣን ለመያዝ የሚታገል ማንኛውም ፓርቲ ህዝቡ ሊከላከለው እንደሚገባ አቶ ኃይሉ አሳስበዋል፡፡
በዕለቱ በግንባሩ አባላትና ደጋፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ወ/ሮ ብርነሽ አባይ ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75  

 
 
የቀበሌ 13/14 ነጋዴዎች በምርጫ ዙሪያ ተወያዩ
ሚያዝያ 24/2002
 
የ2002 አገር አቀፍና የክልል ም/ቤት አባላት ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የንግዱ ህብረተሰብ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባው ተገለጸ፡፡
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 13/14 የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ምርጫው ሰላማዊ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
 
በአሥታራ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የውይይት ፕሮግራም ላይ የቀበሌው ነጋዴዎች ተወካይ አቶ እስፓጋዱስ ስዩሜ እንደተናገሩት ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የንግዱ ማህበረሰብ ፍላጎት ነው፡፡ ሰላም ባለበት ነጋዴው ነግዶ ማትረፍ የሚችልና ንግዱን በአግባቡ የሚመራ በመሆኑ ነጋዴው ህብረተሰብ በአገሪቱ ሰላም እንዲኖር ግፊት ያደርጋል ብለዋል፡፡
 
የክ/ከተማው ንግድና ኢንዱስተሪ ልማት ጽ/ቤትና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ  ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አስፋው በበኩላቸው ነጋዴው ህብረተሰብ የተስተካከለ የግብይት ስርዓት እንዲኖረው ሰላማዊ አካባቢ ያስፈልጋል፡፡ለዚህም የንግዱ ማህበረሰብ ከመንግስት ጎን በመቆም ለሰላሙ ሊታገል ይገባል ብለዋል፡፡
 
ነጋዴዎቹ በግብር አሰባሰብና በተጨማሪ እሴት ታክስ አወሳሰን ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን የአዲስ አበባ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ተክላይ መልስ ሰጥተውበታል፡፡
 
በእለቱ በወረዳ 21/22 የሚወዳደሩ የኢህአዴግ እጩ ተወዳዳሪ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ራሳቸውን አስተዋውቀዋል በትውውቁ ወቅት አቶ ሰለሞን እንደተናገሩት የኢህአዴግ ፖሊሲ ትንንሹን የንግድ ህብረተሰብ በማበረታታት ወደ ትልልቅና መካከለኛ ነጋዴነት እንዲገቡ የሚያደርግ ፖሊሲ ነው ብለዋል፡፡
 
ነጋዱዎቹ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ጥረት ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ሪፖርተር
ታሪኩ እንዳለ
09 13 27 85 75
 
                                                                       
የማዕድንና ኢነርጂ ሚ/ሩ ከባለሀብቶች ጋር ተወያዩ
ሚያዝያ 23 2002
 
በአገሪቱ የተጀመረውን ምቹ የኢንቭስትመንት ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ልማታዊ ባከለሃብቱ ኢህአዴግን እንዲመርጥ ተጠየቀ፡፡
 
በቂርቆስ ክ/ከተማ ቀበሌ 02/03የሚኖሩ ባለሀብቶች ከማዕድንናኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አለማየሁ ተገኑ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይቱ ወቅት ባለሀብቶቹ ለሚኒስተሩ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ የነዳጅ ማዕድን ፍለጋው በተጠናከረ መልኩ አልተከከናወነም፤የአዲስ አበባ የውሃ ችግር መቼ ይፈታል?የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረትና የመሳሰሉ ጥያቄዎችየተነሱ ሲሆን ኢንጂነር አለማየሁ በሰጡት ምላሽም የነዳጅ ፍለጋው በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ መሆኑንና ወደፊትም ፍለጋው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ የውሃ ችግርን በተመለከተም የከተማዋን የውኃ ችግር ለመፍታት የተለያ የውሃ ማጣሪያግድቦችን በመገንባትችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረትን በተመለከተም በቅርቡ የጣና በለስ ፕሮጄክት ስራ ሲጀምር ችግሩ እንደሚቃለል ሚንስተሩ አብራርተዋል፡፡
 
በቀበሌ 02
 
 
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  
  ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
መምረጥ የዜግነት መብት ነው!
 
Facebook 'Like' Button  
 
 
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free