1. የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ራዕይና ተልዕኮ
ራዕይ
ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር መልካም አስተዳደር የተረጋገጠበት ዲሞክራሲ የሰፈነበት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተወገዱበት የተቀላጠፈና የተፋጠነ አገልግሎት የሚሰጥበት ለኑሮ ምቹና ጽዱ ተመራጭና ሞዴል ክ/ከተማ ሆኖ ማየት፡፡
ተልዕኮ
የቂርቆስ ክ/ከተማን የገቢ አቅም በማጎልበት የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ማስወገድና ተገልጋይ ተኮር ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት፡፡
2. የቂርቆስ ክ/ከተማ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥና የህዝብ ብዛት
የቂርቆስ ክ/ከተማ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥና በከተማው እምብርት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሰሜን ከአራዳ፣ በደቡብ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በምስራቅ ከቦሌና ከየካ፣ በምዕራብ ከልደታ ክፍለ ከተማ ይዋሰናል፡፡ የክ/ከተማው ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 14.72ስ/ኪ/ሜ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ በዚህ የቆዳ ስፋት ላይ የሰፈሩት ነዋሪዎች ወንድ 103314 ሴት 117677 በድምሩ 220፣991 እንደሆነ ከቤቶችን ህዝብ ቆጠራ የተገኘው መረጃ ያስረገጣል፡፡
የቂርቆስ ክ/ከተማ በ11 የቀበሌ አስተዳደር እርክኖች የተዋቀረ ሲሆን ለኢንቨስትመንት የሚሆኑ ቦታዎች በውስጣቸው አካተው የሚገኙ ናቸው፡፡ በክ/ከተማው አስተዳደር ውስጥ የተለያዩ መንግስታዊና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን ለአብነትም የአፍሪካ ህብረት ዋና ጽ/ቤት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ይጠቀሳሉ፡፡
በክ/ከተማው የአንድነታችን መገለጫ የሆነውን ብሄራዊ ቤተመንግስትን ጨምሮ ከ16 ሀገራ በላይ ኤምባሲዎች የሚገኙትም በዚህ ክ/ከተማ ነው፡፡ በክ/ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ታላላቅና አለማቀፋዊ ደረጃቸውን የጠበቁ ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ይገኛሉ፡፡ከላይ ለአብነት ከተጠቀሱት በተጨማሪ ኤግዚብሽን ማእከል፤ የአዲስ አበባ ሙዚየምና መስቀል አደባባይ፣ ብሄራዊ ትያትርና አዲስ አበባ ስታዲዮም በዚሁ ክ/ከተማ ውስጥ መገኘታቸው በተጨባች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መናኸሪያ መሆኑን ያመለክታል፡፡